1 of 31

���������������������������������������������

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ

ሰኔ 2017 ዓ.ም

2 of 31

መግቢያ/መነሻ ሁኔታ

  • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በኋላ የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል፣
  • ዘርፉን የበለጠ ለማጠናከር
  • በዘርፉ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን
  • የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እንቅስቃሴ የህዝብና የአገርን ጥቅም ባረጋገጠ መልኩ እንዲሆን ለማድረግ

3 of 31

ማሻሻያ ድንጋጌዎች

የአዋጁ አንቀጽ 8 ተሰርዞ በአዲስ አንቀጽ 8 ተተክቷል፡-

አንቀጽ 8፡- የቦርድ አባላት

ቦርዱ በሚከተለው ሁኔታ የሚሰየሙ ሰባት አባላት(በነባሩ 11 የነበረው) ይኖሩታል፦

  • በፍትሕ ሚኒስትሩ የሚሰየሙ አራት የመንግስት ተቋማት ተወካዮች፤
  • በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት የሚሰየሙ ሁለት ተወካዮች፤ እና
  • በፍትሕ ሚኒስትሩ የሚሰየም በሲቪል ማህበራት ዘርፍ እውቀትና ልምድ ያለው ባለሙያ፡፡
  • የቦርዱ ሰብሰቢ በፍትሕ ሚኒስትሩ የሚሾም ይሆናል፤
  • የቦርዱ ሰብሰቢ የሥራ ዘመን አራት ዓመት እንዲሁም የሌሎች ቦርድ አባላት የሥራ ዘመን ሦስት ዓመት ሲሆን ለአንድ ተጨማሪ የሥራ ዘመን እንደገና ሊሰየሙ ይችላሉ፤
  • የቦርድ አባላት ሥራቸውን ከየትኛውም ተፅዕኖ ነጻ በመሆን በቅንነትና በታማኝነት የማከናዎን ግዴታ አለባቸው።

4 of 31

ማሻሻያ

የአዋጁ አንቀፅ (59)(የምዝገባ ጥያቄን ስላለመቀበል) (1)(መ) ቀጥሎ የሚከተሉት አዲስ ንዑስ ፊደል ተራ (ሠ) እና (ረ)ተጨምረዋል

  • “(ሠ) ድርጅቱ ለአገር ደህንነት ስጋት መሆኑ በባለሥልጣኑ የሚታመንበት ከሆነ፡፡”
  • “(ረ) በዚህ አንቀፅ ንኡስ አንቀፅ ፊደል ተራ (ሠ) በተመለከተው መሰረት ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመመካከር የአገር ደህንነት ስጋት መሆኑን ይወስናል፤ ለዚህ አፈፃፀም ሲባል አስፈላጊውን መመሪያ ሊያወጣ ይችላል፡፡”

5 of 31

ማሻሻያ

የአዋጁ አንቀፅ 61 (የምዝገባ ውጤት) ንዑስ አንቀፅ (5) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (5) ተተክቷል፡-

5/ ማንኛውም ድርጅት፡-

  • ሀ/ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ወይም ለመንግስት አካላት በስጦታ ለማስተላለፍ ለባለሥልጣኑ በቅድሚያ በ15 ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ማሳወቅ አለበት፡፡
  • ለ/የተመዘገበውን ዓላማ ወይም ፕሮግራም ለመተግበር በህዝብ ስም የሰበሰበው ንብረት በመያዣነት አስይዞ ከማንኛውም አካል ወይም ባንክ ገንዘብ ለመበደር የባለስልጣኑን ፈቃድ ማግኘት አለበት፡፡ “

 

6 of 31

ማሻሻያ

ከአዋጁ አንቀፅ 61 ንዑስ አንቀፅ (5) ቀጥሎ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (6) ተጨምሯል፡-

  • 6/ ባለሥልጣኑ ድርጅቶች ንብረት በሚያስተላልፉበት ወይም በሚያስወግዱበት ጊዜ ለባለስልጣኑ ማሳወቅ የሚጠበቅባቸውን የንብረት ዓይነቶች እና የሚያሳውቁበትን አግባብ በመመሪያ ይወስናል፤ አፈጸጸሙን እና አተገባበሩን ይከታተላል፡፡

የአዋጁ አንቀፅ 62 (የስራ ነጻነት) ንዑስ አንቀፅ (5) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (5) ተተክቷል፡-

  • 5/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) ድንጋጌ ቢኖርም የውጭ ድርጅቶች እና ኢትዮጵያ ውስጥ በሚኖሩ የውጭ አገር ዜጐች የተመሰረቱ አገር በቀል ድርጅቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለአገር በቀል ድርጅቶች የፋይናንስ ወይም የቴክኒካል ድጋፎችን በመስጠት የፖለቲካ አድቮኬሲ፣ በመራጮች ትምህርት ወይም በምርጫ መታዘብ ወይም ማንኛውም ከምርጫ ጋር የተያያዘ ሥራ ላይ መሰማራት አይችሉም።

7 of 31

ማሻሻያ

የአዋጁ አንቀፅ 62 ንዑስ አንቀፅ (6) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (6) ተተክቷል፡-

  • 6/ ማንኛውም አገር በቀል ድርጅት በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (5) የተመለከቱትን ተግባራት ለማከናወን ከውጭ የፋይናንስ ምንጭ ገንዘብ ወይም ሃብት መቀበል አይችልም፡፡

የአዋጁ አንቀፅ 62 ንዑስ አንቀፅ (7) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (7) ተተክቷል፡፡

  • 7/ ማንኛውም የውጭ ድርጅት ፕሮጀክቶችን በሚተገብርበት ወቅት የእውቀት፣ የቁሳቁስ፣ የቴክኖሎጂ ወይም የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ከአገር በቀል ድርጅቶች፣ ከማህበረሰብ ዐቀፍ የልማት ድርጅቶች እና በየደረጃው ካሉ የመንግስት ተቋማት ጋር በአጋርነት በመሥራት የአገር-በቀል ተቋማትና አደረጃጀቶች አቅም እንዲጎለብት ድጋፍ ማድረግ እና ሥራዎች በሎካላይዜሽን መርህ መሰረት እንዲተገበሩ ማበረታታት አለበት፤ ባለስልጣኑ ሎካላይዜሽ የሚተገበርበትን ዝርዝር የአሰራር ስርዓት በመመሪያ ይወስናል፡፡

8 of 31

ማሻሻያ…

የአዋጁ አንቀፅ 63 (የሀብት አሰባሰብና አስተዳደር) ንዑስ አንቀፅ (1)(ሐ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (1)(ሐ) ተተክቷል፡-

  • “1(ሐ) ለዓላማው መሳካት ከየትኛውም ሕጋዊ ምንጭ ገንዘብ የመጠየቅ፣ የመቀበልና የመጠቀም መብት አለው፤ ሆኖም ከውጭ አገር ወይም ከአገር ውስጥ ከሚገኝ የውጭ አካል የፋይናንስ ድጋፍ ሲያገኝ ድጋፉን ካገኘበት ቀን ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ የገንዘቡን ምንጭ፣ መጠን፣ ዓላማ እና ሌሎች መረጃዎችን ከደጋፊ ማስረጃ ጋር አያይዞ በፅሁፍ ለባለስልጣኑ ማሳወቅ አለበት፤ ባለስልጣኑ የገንዘብ መጠኑን በመመሪያ ሊወስን ይችላል፡፡

9 of 31

��ማሻሻያ…

የአዋጁ አንቀፅ 70 ርዕስ(ህልውናን ስለማረጋገጥ) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ርዕስ ተተክቷል፡-

  • “7ዐ. ዕድሳት እና ህልውናን ስለማረጋገጥ

የአዋጁ አንቀፅ 70(2) ቀጥሎ የሚከተሉት አዲስ ንዑስ ንዑስ አንቀፅ (3)፣(4)፣(5) እና (6) ተካተዋል፡-

  • 3/ ማንኛውም በባለስልጣኑ ተመዝግቦ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተሰጠው ድርጅት የምዝገባ ምስክር ወረቀቱ በተሰጠው በአራት ዓመት የመጨረሻ አንድ ወር ሲቀረው ጀምሮ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀቱን በባለሥልጣኑ ማሳደስ ይኖርበታል፡፡ የምዝገባ ምስክር ወረቀት እድሳት ዝርዝር አፈፃፀም ቦርዱ በሚያወጣው መመሪያ ይወሰናል፡፡

10 of 31

ማሻሻያ…

  • 4/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) ድንጋጌ ቢኖርም ይህ አዋጅ ተፈፃሚ ከመሆኑ በፊት የተመዘገቡ ድርጅቶች የእድሳት ጊዜ ድርጅቶቹ ከተመዘገቡበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ይሆናል፡፡
  • 5/ ማንኛውም ድርጅት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) ላይ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀቱን ካላሳደሰ ወይም ያላሳደሰበትን ምክንያት ካላቀረበ ባለሥልጣኑ ሰፊ ተደራሽነት ባለው ጋዜጣ ወይም ዲጂታል ማስታወቂያ ለድርጅቱ ጥሪ ማድረግ አለበት፡፡ ጥሪ የተደረገለት ድርጅት ጥሪው በተደረገ በ30 ቀናት ውስጥ የድርጅቱ ኃላፊ ወይም ሕጋዊ ተወካይ የምዝገባ ምስክር ወረቀቱን በወቅቱ ያላሳደሰበትን ምክንያት ለባለስልጣኑ ማስረዳት አለበት።

11 of 31

ማሻሻያ…

  • “6/ ባለስልጣኑ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ላይ በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀቱን ያላሳደሰ ድርጅት በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) መሰረት ቀርቦ ያላሳደሰበትን በቂ ምክንያት ካላቀረበ ባለስልጣኑ ድርጅቱ እንዲሰረዝና እንዲፈርስ ሊወስን ይችላል። በባለስልጣኑ ውሳኔ ቅሬታ ያለው ድርጅት በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ለቦርድ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል

12 of 31

ማሻሻያ…

የአዋጁ አንቀፅ 72 (አመታዊ የሒሳብ መግለጫና ምርመራ) ንዑስ አንቀፅ (2) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (2) ተተክቷል፡-

  • 2/ የዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) ድንጋጌ ቢኖርም በበጀት አመቱ ከአንድ ሚሊዮን ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር የማይበልጥ ይል የነበረው) የማይበልጥ ገንዘብ የሚያንቀሳቅስ ድርጅት ገቢን፣ ወጪን፣ ሐብትና ዕዳን የሚያመለክት የሂሳብ መግለጫ ብቻ ማቅረብ ይችላል። ባለስልጣን መ/ቤቱ እንደአስፈላጊነቱ ለቦርድ በማቅረብ የገንዘብ መጠኑ እንዲሻሻል ሊያደርግ ይችላል፡፡

13 of 31

ማሻሻያ

የአዋጁ አንቀፅ 75 ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀፅ 75 ተተክቷል፡-

“75. የፋይናንስ ድጋፍ እና ባንክ ሒሳብ ስለመክፈት

የባንክ ሒሳብ ስለመክፈት

  • 1/ ማንኛውም ድርጅት የባንክ ሒሳብ ለመክፈት በቅድሚያ ከባለስልጣኑ በጽሑፍ ፈቃድ ለማግኘት ስልጣን ባለው የድርጅቱ አካል በማስወሰን ጥያቄ ማቅረብ አለበት።
  • 2/ ባለስልጣኑ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት ጥያቄ በቀረበለት በ 5 ቀናት ውስጥ ለተጠየቀው ባንክ የፈቃድ ደብዳቤ ይፅፋል።
  • 3/ የማንኛውም ድርጅት የገንዘብ እንቅስቃሴ በድርጅቱ ስም በተከፈተ የባንክ ሒሳብ መከናወን ይኖርበታል።

14 of 31

ማሻሻያ…

  • 4/ ማንኛውም ባንክ ባለስልጣኑ በጠየቀ ጊዜ ወዲያውኑ በማናቸውም የድርጅት ሥም የተከፈቱ የባንክ ሂሳቦችን ዝርዝርና የሒሳብ መግለጫዎችን የመስጠት ግዴታ አለበት።
  • 5/ የድርጅቱ  የባንክ ሒሳብ እንቅስቃሴ በመተዳደሪያ ደንቡ በተመለከተው አኳኋን መሆን አለበት።  

15 of 31

ማሻሻያ…

የአዋጁ አንቀፅ 77 (ምርመራ የማድረግ ስልጣን) ንዑስ አንቀፅ (4) እና (5) ተሰርው በሚከተሉት አዲስ ንዑስ አንቀፅ (4) እና (5) ተተክተል፡-

  • 4/ ባለሥልጠኑ የምርመራ ሥራውን በሚያከናውንበት ወቅት ከባድ የሕግ ጥሰት ስለመፈጸማቸው አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም(ሲያረጋግጥ ይል የነበረው) እና ድርጅቱ ካልታገደ የማይመለስ ጉዳት ይደርሳል ብሎ ካመነ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር እስከ ሶስት ወር የሚደርስ የእግድ ትዕዛዝ አስተላልፎ ምርመራ ሊያደርግ ይችላል፤ ሆኖም ምርመራው በሶስት ወር የእግድ ጊዜ ውስጥ ካልተጠናቀቀ ቦርዱ እግዱን ለተጨማሪ ሶስት ወራት ሊያራዝመው ይችላል፡፡ ባለስልጣኑ የድርጅቱን የባንክ ሂሳብ በከፊል ወይም በሙሉ ሊያግድ ይችላል፡፡

16 of 31

ማሻሻያ…

  • 5/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (4) መሠረት ዋና ዳይሬክተሩ በሰጠው እግድ ላይ ቅር የተሰኘ ድርጅት የእግድ ውሳኔው ከተሰጠ ጊዜ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ለቦርዱ ማቅረብ ይችላል፤ ቦርዱ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡(ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድቤት ይግባኝ ማቅረብ ይችላል ይል የነበረው)”

17 of 31

ማሻሻያ…

የአዋጁ አንቀፅ 78 ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ አንቀፅ 78 ተተክቷል፡-

78. አስተዳደራዊ እርምጃ

1/ ባለሥልጣኑ ከሚከተሉት ጥፋቶች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ጥፋቶች ለፈፀመ ድርጅት የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል፡-

ሀ) በመተዳደሪያ ደንቡ ወይም በተሰጠው የውክልና ስልጣን ወይም በተፈቀደለት ዝርዝር መሰረት የማይመራና የማይንቀሳቀስ ከሆነ፤

ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 65(1) መሰረት በስራ መሪነት ወይም በድርጅት የቦርድ ወይም የስራ አስፈፃሚ አባልነት መካተት የማይገባውን ሰው በአባልነት አካቶ ከተገኘ፤

18 of 31

ማሻሻያ…

ሐ) የምዝገባ ምስክር ወረቀቱን ግልፅ በሆነ ቦታ ላይ በዋናው መ/ቤት እና በቅርንጫፍ መ/ቤቶች አለመለጠፍ ወይም አለማስቀመጥ፤

መ) በባለስልጣኑ በሚቀርብለት ጥያቄ መሰረት ተገቢውን ምላሽና መረጃ በወቅቱ አለመስጠት ወይም አለማቅረብ፤

ሠ) በአዋጁ መሰረት ማቅረብ የሚገባውን ማንኛውንም የክንውን እና የፋይናንስ ሪፖርት በጊዜ ገደቡ አለማቅረብ፤

ረ) ንብረት እንዲሁም መተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ ሌሎች ድርጅቱን የሚመለከቱ ሰነዶች አደራጅቶ በአግባቡ ካልጠበቀ ወይም ካልያዘ፣

19 of 31

ማሻሻያ

ሰ) በዚህ አንቀፅ ሌላ እርምጃ የሚያስወስዱ መሆኑ የተደነገገ ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ወይም አዋጁን ለማስፈፀም በወጣ ደንብ ወይም መመሪያ የተጣሉበትን ሌሎች ግዴታዎች በግልጽ የጣሰ ከሆነ፡፡

ሸ) በዚህ ንኡስ አንቀፅ ከተጠቀሱት ጥፋቶች ጋር በባህሪ ተመሳሳይ ወይም የሚቀራረቡ የሆኑ እና በባለስልጣኑ መመሪያ ሊወሰኑ የሚችሉ ጥፋቶችን መፈፀም፤

2/ በዚህ አንጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሰረት የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ የተፈፀመውን የሕግ ጥሰት፣ ሊደረግ የሚገባውን ማስተካከያ እና በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መስተካከል እንዳለበት በግልጽ በሚያሳይ ሁኔታ በፅሁፍ መሰጠት አለበት።

20 of 31

ማሻሻያ…

3/ ከሚከተሉት ጥፋቶች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ጥፋቶች የፈፀመ ድርጅት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ወይም የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል፡-

ሀ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (2) መሰረት የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኋላ በአንድ የበጀት ዓመት ውስጥ ተመሳሳይ እርምጃ የሚያስወስድ ጥፋት ከፈፀመ፤

ለ) በዚህ አዋጅ ወይም አዋጁን ለማስፈፀም በወጣ ደንብ ወይም መመሪያ የተጣለበትን በፅሁፍ ለባለስልጣኑ ዕቅድ እና ሪፖርት የማቅረብ ወይም የማሳወቅ ግዴታ አሳማኝ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር በጊዜ ገደቡ ካልተወጣ፤

ሐ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 72 መሰረት ዓመታዊ የሂሳብ ምርመራ የማድረግ እና መግለጫ የመስጠት ግዴታውን ካልተወጣ፣

21 of 31

ማሻሻያ…

መ) የድርጅቱ አድራሻ ወይም ቢሮ ለውጥን ጨምሮ ማናቸውንም የድርጅቱን ለውጦች ለባለስልጣኑ አለማሳወቅ፣

ሠ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 71 መሰረት የድርጅቱን የሂሳብ መዝገብ በአግባቡ የመያዝ ግዴታውን ካልተወጣ፣

ረ) የድርጅቱ ሰራተኞችና የስራ መሪዎች በድርጅቱ ውስጥ በተመደቡበት የስራ ምድብ ተገቢ ስራ እንዲሰሩ አለማድረግና ተገቢው አመራር አለመሰጠት፤

ሰ) ያለባለስልጣኑ እውቅና የድጋፍ ደብዳቤ የባንክ ሂሳብ መክፈት እና ባልተፈቀደላቸው ወይም ስልጣን በሌላቸው ግለሰቦች የባንክ ሂሳብን ማንቀሳቀስ፣

ሸ) በሀሰት የሌላ ሰውን ፊርማ አስመስሎ መፈረም፣ አለአግባብ ማህተም መጠቀም እና የጥቅም ግጭት የሚያስከትል ተግባር መፈጸም፤

22 of 31

ማሻሻያ…

ቀ) ያለባለስልጣኑ ፍቃድና እውቅና የሂሳብ ሰነዶች፣ ደረሰኞችን ማሳተም፣ ማህተም ማስቀረፅ፤

በ) ከባንክ ስርዓት ወይም በህግ ከተፈቀደው የገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገድ ውጭ ሂሳብ ማንቀሳቀስ ወይም ምንጩ ያልታወቀ ገንዘብ ከውጭ አገር ወይም ከአገር ውስጥ መቀበል ወይም ማንቀሳቀስ፤

ተ) ከባለስልጣኑ እውቅና ወይም ፈቃድ ውጭ የድርጅቱን ንብረት መሸጠ፣ ማስተላለፈ፣ ማስወገድ፣ መደበቀ ወይም ማሸሸ፤

ቸ) ሃብት የተገኘለትን ፕሮጀክት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከተፈራረሙ በኋላ አለመፈፀም ወይም ከ6 ወር በላይ ሳይፈፅሙ መዘግየት፤

ኘ) በአዋጁ በተደነገገው መሰረት የአስተዳደራዊ ወጪው ከ20 ፐርሰንት በላይ ከሆነ፤

አ) በዚህ ንኡስ አንቀፅ ከተጠቀሱት ጥፋቶች ጋር በባህሪ ተመሳሳይ ወይም የሚቀራረቡ የሆኑ እና በባለስልጣኑ መመሪያ ሊወሰኑ የሚችሉ ጥፋቶችን መፈፀም፤

23 of 31

ማሻሻያ…

4/ በዚህ አንጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሰረት የሚሰጥ ማስጠንቀቂያ የተፈፀመውን የሕግ ጥሰት፣ ሊደረግ የሚገባውን ማስተካከያ፣ ማስተካከያው በምን ያህል ጊዜ ውስጥ መፈፀም እንዳለበት እና ጥብቅ ወይም የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መሆኑን በግልጽ በሚያሳይ ሁኔታ በፅሁፍ መሰጠት አለበት።

5/ ከሚከተሉት ጥፋቶች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ጥፋቶች የፈፀመ ድርጅት እንደጥፋቱ መጠን በባለሥልጣኑ ውሳኔ ከሃምሳ ሺህ እስከ ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል፡-

ሀ) የድርጅቱን ጥቅም ወይም የተጠቃሚዎችን ጥቅም ወይም የአባላትን ጥቅምና ፍላጎት የሚጎዳ ተግባር በግልፅ መፈፀም፤

ለ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 76(3) መሰረት ስራው በኢትዮጵያውያን ሊሸፈን የማይችል ስለመሆኑ በባለስልጣኑ ሳይረጋገጥ የውጭ አገር ዜጋን እያሰራ ከተገኘ፤

24 of 31

ማሻሻያ…

ሐ) በዚህ አዋጅ መሰረት ለባለስልጣኑ የተሰጠ የክትትል እና ቁጥጥር ተግባርን ካስተጓጎለ ወይም ካደናቀፈ፤

መ) በዚህ አዋጅ አንቀጽ 70 መሰረት የምዝገባ ምስክር ወረቀቱን በተገቢው ጊዜ ውስጥ ካላሳደሰ/ህልውናውን በጊዜ ገደቡ ውስጥ ካላረጋገጠ፤

ሠ) ከባለስልጣኑ ተገቢ ፈቃድ ወይም እውቅና ሳያገኝ በአደባባይ ህዝባዊ መዋጮ ያካሄደ ወይም ገቢ የሰበሰበ፤

ረ) በዚህ አዋጅ በተደነገገው መሰረት የፋይናንስ ገቢን ወይም ወደ ውጭ አገር ሲልክ በጊዜ ገደቡ ለባለስልጣኑ ካላሳወቀ፤

6) በዚህ አንቀፅ በተደነገገው መሰረት ሌሎች ጥፋቶችን የፈፀመ ድርጅት በአንቀፁ የተመለከተው እርምጃ የሚወሰድበት መሆኑ እንደተጠበቀ ሁኖ በባለስልጣኑ ውሳኔ በተጨማሪነት የገንዘብ መቀጮ ሊቀጣ ይችላል፡፡

25 of 31

ማሻሻያ…

7/ ከሚከተሉት ጥፋቶች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ጥፋቶች የፈፀመ ድርጅት ከአንድ ወር እስከ ስድስት ወር የሚደርስ የእግድ እርምጃ ይወሰድበታል፡-

ሀ) ከተመዘገበበት ወይም ከተፈቀደለት ዓላማ ውጭ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ፤

ለ) ከተከለከለ የገቢ ምንጭ ሃብት ከተቀበለ ወይም ለተከለከለ የስራ መስክ ሃብት ከሰጠ፤

ሐ) የህዝብና የሀገርን ጥቅም የሚጎዳ ሕገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙ ወይም በዚህ አይነት ተግባር ውስጥ መሳተፉ ከተረጋገጠ፤

መ) ሐሰተኛ ሪፖርት ወይም የተሳሳተ መረጃ ያቀረበ

ሠ) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለአገር በቀል ድርጅቶች ፋይናንስ ወይም የቴክኒካል ድጋፎችን በመስጠት የፖለቲካ አድቮኬሲ፣ በመራጮች ትምህርት ወይም በምርጫ መታዘብ ወይም ማንኛውም ከምርጫ ጋር የተያያዘ ሥራ መስራቱ ወይም በዚህ ስራ ላይ መሰማራቱ ከተረጋገጠ፤

26 of 31

ማሻሻያ…

ረ) ከፖለቲካ ገለልተኛ ሳይሆን ኃላፊነት በጎደለው መልኩ መንቀሳቀሱ በግልፅ ከተረጋገጠ፤

ሰ) የበጀት ዓመቱ የአስተዳደራዊ ወጪው ከ40 ፐርሰንት በላይ ከሆነ፤

ሸ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (3) መሰረት ጥብቅ ወይም የመጨረሻ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው በኋላ ወይም በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (5) መሰረት የገንዘብ መቀጮ ከተቀጣ በኋላ ተመሳሳይ እርምጃ የሚያስወስድ ጥፋት በበጀት ዓመቱ ለሁለተኛ ጊዜ ከፈፀመ፤

8/ በዚህ አንጽ ንዑስ አንቀጽ (7) መሰረት የሚወሰድ የእግድ እርምጃ የተፈፀመውን የሕግ ጥሰት፣ እግዱ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እና ሊደረግ የሚገባውን ማስተካከያ በግልጽ በሚያሳይ ሁኔታ በፅሁፍ መሰጠት አለበት።

27 of 31

ማሻሻያ…

9/ ከሚከተሉት ጥፋቶች አንዱን ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ ጥፋቶች የፈፀመ ድርጅት እንዲሰረዝ ይደረጋል፡-

ሀ) ሃሰተኛ ሰነድ በማቅረብ ወይም አሳሳች መረጃ በመስጠት ወይም በማጭበርበር የተመዘገበ ከሆነ፤

ለ) በከፍተኛ ደረጃ የህዝብና የሀገርን ሰላም፣ ጥቅም ወይም ደህንነት አደጋ ላይ በሚጥል ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙ ወይም መሳተፉ ከተረጋገጠ፤

ሐ) በወንጀል ድርጊት የተሰማራን ማንኛውም ሰው ወይም ቡድን በገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣ በሃሳብ ወይም በቴክኒክ የሚደግፍ መሆኑ ከተረጋገጠ፣

መ) ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳቱ ከተረጋገጠ፤

28 of 31

ማሻሻያ…

ሠ) በወንጀል የተገኘ ሃብትን ህጋዊ አስመስሎ ካቀረበ ወይም ከተጠቀመ፤

ረ) ሰራተኞች ወይም የሥራ መሪዎች የድርጅቱን ገንዘብ ከመዘበሩ ወይም ከድርጅቱ ዓላማ ውጭ ለግል ጥቅሙ ካዋሉ እና ድርጅቱ የእርምት እርምጃ ካልወሰደ፤

ሠ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (7) መሰረት የስድስት ወር የእግድ እርምጃ ተወስዶበት ተመሳሳይ እርምጃ የሚያስወስድ ጥፋት በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በድጋሚ ከፈፀመ፤

10/ በዚህ አንጽ ንዑስ አንቀጽ (9) መሰረት የሚወሰድ የመሰረዝ እርምጃ የተፈፀመውን የሕግ ጥሰት በግልጽ በሚያሳይ ሁኔታ በፅሁፍ መሰጠት አለበት።

29 of 31

ማሻሻያ…

11/ በዚህ አንቀፅ መሰረት ድርጅቱን ለቅጣት የሚዳርጉ ጥፋቶች የፈፀሙ ወይም እንዲፈፀም ያደረጉ የድርጅቱ የስራ መሪዎች ወይም ሰራተኞች ወይም የሚመለከታቸው አካላት ላይ የድረጅቱ የበላይ አካል አስፈላጊውን እርምጃ በመውሰድ ለባለሥልጣኑ ማሳወቅ ይኖርበታል፡፡

12/ በዚህ አንቀጽ መሰረት የሚወሰድ አስተዳደራዊ እርምጃ አግባብነት ባለው ሕግ መሰረት በድርጅት ወይም በድርጅት ኃላፊ ላይ ሊወሰድ የሚችል የወንጀል ተጠያቂነትን አያስቀርም፡፡

የአዋጁ አንቀፅ 85 ንዑስ አንቀፅ (6) ተሰርዞ በሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (6) ተተክቷል፡-

“6/ ምክር ቤቱ በባለሥልጣኑ ቦርድ ውስጥ ድርጅቶችን የሚወክሉ 2 ተወካዮችን ይመርጣል።”

30 of 31

ማሻሻያ…

7/ ምክርቤቱ ህጉን ተከትሎ በየዓመቱ የሚሰራቸው ስራዎችና የፋይናንስ አፈፃፀሙን በተመለከተ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ለባለስልጣኑ ያሳውቃል፤

8/ የምክርቤቱ ተጠሪነት ለምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባኤ ይሆናል፡፡

ከአዋጁ አንቀፅ 86 (የሲቪል ማኅበረሰብ ፈንድ) ንዑስ አንቀፅ (3) (ሐ) ቀጥሎ የሚከተለው አዲስ ንዑስ አንቀፅ (3) (መ) ተጨምራል፡-

(መ) ከለጋሽ ድርጅቶች እና በድርጅቶች በራስ ተነሳሽነት ወይም በፍቃደኝነት ከሚደረግ ድጋፍ”

31 of 31

አመሰግናለሁ