እምነ በሐ፣ ቅድስት ቤተክርስቲያን፣ ሥርጉት አረፋቲሃ
ሰላም ላንቺ ይሁን፤ እናታችን ክብርት ቤተክርስቲያን። ግድግዳዎችሽ በጳዝዮን እንቍ
Imine beha qidist bete kiristeeyan sirgut arefateeha
Peace be unto you, our mother, O honorable church. Thy walls are embroidered with Topaz.
በዕንቍ ጳዝዮን፤ እምነ በሐ፣ ቅድስት ቤተክርስቲያን።
ግድግዳዎችሽ በጳዝዮን እንቍ የተጌጡ ናቸው፤ ሰላም ላንቺ ይሁን! እናታችን ክብርት ቤተክርስቲያን።
Be'inqwu pazion imine beha qidist bete kiristeeyan.
Thy walls are embroidered with Topaz. Peace be unto you, our mother, O honorable church
መስቀል አብርሃ! በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ፤ እምኩሉሰ ፀሐይ አርአየ።
መስቀልን አበራ! በኮከቦች ሰማይን አስጌጠ። ከሁሉም ፀሐይን አሳየ።
Mesqel abriha! Bekewakibt aserigewa semaye imkwuluse Tsehay ar'aye.
The cross shined and had the heavens embroidered with stars. Of all the sun is seen.
መስቀል አብርሃ! በከዋክብት አሠርገወ ሰማየ።
መስቀል አበራ። በኮከቦች ሰማይን አስጌጠ።
Mesqel abriha! bekewakibt aserigewa semaye.
The cross shined and had the heavens embroidered with stars.
ይበሉ ሕዝብ፦ ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ፤ ኢይበል ፈላሲ ዘገብአ ኀበ
ጽድቅን የሠራ ሰንበትን ያከበረም ሰው ሁሉ ጻድቅ ነው። ወደ እግዚአብሔር አምልኮት የገባ
People:- Kwulu zegebra letsidq tsadiq wi'itu wezeyakebir senbete eeybel felasee zegebi'a habe
Blessed is he who does blessed deeds and honors the Sabbath. Let him not question whether he will be outcast from
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እምሕዝቡ፤ ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ፣ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር ሰንበተ።
ከምዕመናን ይለየኝ ይሆን ፈጽሞ አይበል። ጽድቅን የሠራ ሰንበትን ያከበረም ሰው ሁሉ ጻድቅ ነው።
People:- Igzee'abihér yifeliteneenu imhizbu kwulu zegebra letsidq tsadiq wi'itu wezeyakebir senbete.
the multitudes if he was to enter into the worship of God. Blessed is he who does blessed deeds and honors the Sabbath.
ይበሉ ሕዝብ፦ ሃሌሉያ! እመቦ ብእሲ እምእመናን ዘቦአ ቤተክርስቲያን፤
ሃሌሉያ! በቅዳሴ ጊዜ ከምዕመናን ወገን ወደ ቤተክርስቲያን የገባ ሰው ቢኖር፣
People:- Halléluya! imebo bi'isee im'imenan zebo'a béte kiristeeyan
Hallelujah! If there be anyone of the faithful that hath entered the church at the time of mass and
ይበሉ ሕዝብ፦ በጊዜ ቅዳሴ ወኢሰምዐ መጻሕፍተ ቅዱሳተ ወኢተዐገሠ እስከይፈጸሙ ጸሎተ ቅዳሴ
ቅዱሳተ መጻሕፍትን ሳይሰማ፣ የቅዳሴው ጸሎት እስኪፈጸም ባይታገሥ፣
People:- Begeezé qidase we'eete'agese iske yifetsimu tselote qidasé
and hath not heard the holy Scriptures, and hath not waited until they finish the prayer of the Mass, and hath not
ወኢተመጠወ እምቍርባን ይሰደድ እምቤተክርስቲያን እስመ አማሰነ ሕገ-እግዚአብሔር፤ ወአስተሐቀረ ቀመተ
ከቁርባኑም ባይቀበል፣ ከቤተክርስቲያን ይለይ፣ የእግዚአብሔርን ሕግ አፍርሷልና። የሥጋና የነፍስ
We'eetemetewe imqwurban yiseded imbéte kiristeeyan isme amasene hige Igzee'abihér we'astehaqere qemete
received the holy communion, let him be driven out of the church: for he hath violated the law of God and disdained to
ቅድመ ንጉሥ ሰማያዊ፤ ንጉሠ ሥጋ ወመንፈስ፤ ከመዝ መሐሩነ ሐዋርያት በአብጥሊሶሙ።
ፈጣሪ በሚሆን በሰማያዊ ንጉሥ ፊት መቆምንም አቃሏልና። ሐዋርያት በሲኖዶሳቸው እንዲህ ብለው አስተምረውናል።
Qidme nigus semayawee nigus siga wemenfes kemez meharune
Stand Before the heavenly King, the King of Body and Spirit. This the Apostles have taught us in their canons.
ከትንሣኤ እስከ በዓለ ሃምሳ
ሃሌሉያ! ዮሴፍ ወኒቆዲሞስ ገነዝዎ ለኢየሱስ በሰንዱናት ለዘተንሥአ እሙታን በመንክር ኪን።
ሃሌሉያ! ዮሴፍ ኒቆዲሞስ ድንቅ በሚሆን ጥበብ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ኢየሱስን በበፍታ ገነዙት።
From Easter to Pentecost
Halléluya, Yoséf weneeqodeemosgeneziwo le'Eeyesus besendunat lezetensi'a imutan lemenkir keen.
Halleluia, Joseph and Nicodemus wrapped with linen cloths Jesus who
rose from the dead in wondrous fashion.
ይበሉ ሕዝብ፦ አንቲ ውእቱ መሶበ ወርቅ ንጹሕ እንተ ውስቴታ መና ኅቡዕ
ለዓለም ሁሉ ሕይወት የሚሰጥ ከሰማይ የወረደ ኅብስት
People:- Antee wi'itu mesobewerq nitsuh inte wistéta mena hibu'i
Thou art the pot of pure gold wherein is hidden the manna,
ይበሉ ሕዝብ፦ ኅብስት ዘወረደ እምሰማያት ወሀቤ ሕይወት ለኵሉ ዓለም።
የተሠወረ መና ያለብሽ፣ ንጹሕ የወርቅ መሶብ አንቺ ነሽ።
People:- Hibu'i hibist zewerede imsemayat wehabé hiywet lekwulu alem.
the bread which came down from heaven giving life unto all the world.
ይበል ካህን፦ ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ዓለም አምላክነ።
ዓለምን የያዘ እግዚአብሔር አብ ቡሩክ ነው።
Priest :- Buruk Igzee'abihér Ab ahazé kwulu alem amlakine.
Blessed be the Lord, Almighty Father, our God.
ይበሉ ሕዝብ፦አሜን።
People :- Amen.
ይበል ካህን፦ ወቡሩክ ወልድ ዋሕድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒነ።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ዋሕድም ቡሩክ ነው።
Priest :- Weburuk weld wahid igzee'ine Eeyesus Kiristos medhaneene.
And blessed be the only Son, our Lord and our Savior Jesus Christ.
ይበሉ ሕዝብ፦አሜን።
People :- Amen.
ይበል ካህን፦ ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጽሔ ኵልነ።
ሁላችንን የሚያነጻ፣ የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው።
Priest :- Weburuk Menfes Qidus peraqleetos mentsi'ee wementsihé kwuline.
And blessed be the Holy Spirit, the Paraclete, the comforter and cleanser of us all.
ይበሉ ሕዝብ፦አሜን።
People :- Amen.
ይበል ካህን፦ ስብሐት ወክብር ይደሉ ለሥሉስ ቅዱስ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፅሩይ ኵሉ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ አበውየ ወአኀውየ ላዕሌየ ወላዕለ ዝንቱ መሥዋዕት።
ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ሁልጊዜም ለተካከሉ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ክብር ምስጋና ይገባል። ዛሬም ዘወትርም ለዘላላሙ አሜንአባቶቼና ወንድሞቼ በእኔ ላይ በመሥዋዕቱም ላይ ጸልዩ።
Priest:- Glory and honor are due to the Holy Trinity, the Father and the Son and the Holy Spirit, always coequal, both now and ever and world without end. Amen. My fathers an my brothers, pray for me and for this sacrifice.
ይበል ንፍቅ ካህን፦ እግዚአብሔር ይስማዕከ ኵሎ ዘሰአልከ ወይትወከፍ መስዋዕተከ ወቍርባነከ ከመ መሥዋዕተ መልከ ጼዴቅ ወአሮን ወዘካርያስ ካህናተ ቤተክርስቲያኑ ለበኵር።
እግዚአብሔር የለመንከውን ሁሉ ይስማህ። የበኵር የቤተክርስቲያኑ ካህናቱ የሚሆኑ የመልከ ጼዴቅንና የአሮንን የዘካርያስንም መሥዋዕት እንደተቀበለ መሥዋዕትህን ቍርባንህንም ይቀበልልህ።
Ass't Priest:- May God hear thee in all that thou hast asked and accept thy sacrifice and offering like the sacrifice of Melchisedec and Aaron and
Zacharias, the priests of the church of the First-born;
ሁሉም ይበሉ፦ አቡነ ዘበሰማያት።
አባታችን ሆይ፡
All shall say:- The Lord's Prayer.
ይበል ካህን፦ አሐዱ አብ ቅዱስ፤ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፤ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።
አንዱ ቅዱስ አብ ነው፤ አንዱ ቅዱስ ወልድ ነው፤ አንዱ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ነው።
Priest :- Ahadu Ab Qidus, Ahadu Weld Qidus, Ahadu wi'itu Menfes Qidus.
One is the Holy Father, one is the Holy Son, one is the Holy Spirit.
ይበሉ ሕዝብ፦ በአማን አብ ቅዱስ፤ በአማን ወልድ ቅዱስ፤ በአማን ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።
አብ በእውነት ቅዱስ ነው፤ ወልድ በእውነት ቅዱስ ነው፡ መንፈስ ቅዱስም በእውነት ቅዱስ ነው።
People :- Be'aman Ab qidus, be'Aman Wold qidus, be'aman wi'itu Menfes Qidus.
Truly the Father is holy, truly the Son is holy, truly the Holy Spirit is holy.
ይበል ካህን፦ ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ኵልክሙ አሕዛብ።
ሕዝቦችም ሁላችሁ እግዚአብሔርን አመስግኑት።
Priest :- Sebihiwo le'Igzee'abihér kwulikimu ahizab.
Praise the Lord, all ye nations.
ይበሉ ሕዝብ፦ ወይሴብሕዎ ኵሎሙ ሕዝብ።
ሕዝቡ ሁሉ ያመሰግኑታል።
People :- Weyisébihwo kwulomu hizbi.
And praise him, all ye people.
ይበል ካህን፦ እስመ ጸንዐት ምሕረቱ ላዕሌነ።
ምሕረቱ በእኛ ላይ ጸንታለችና።
Priest :- Isme tsin'ate mihretu la'iléne.
For his merciful kindness is great toward us.
ይበሉ ሕዝብ፦ ጽድቍሰ ለእግዚአብሔር ይሄሉ ለዓለም።
የእግዚአብሔር ቸርነቱ ለዘለዓለም ይኖራል።
People :- Tsedikuse Le’igziabher yihelu le’alem
And the Truth of the Lord endureth for ever.
ይበል ካህን፦ ስብሐት ለአብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ።
ለአብ፣ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል።
Priest :- Sibhat le'Ab, weWold, weMenfes Qidus.
Glory be to the Father and to the Son and to the Holy Spirit,
ይበሉ ሕዝብ፦ (ካህኑ ያለውን መልሰው ይበሉ።)
People :- (Shall repeat his words)
ይበል ካህን፦ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን ሃሌሉያ።
ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ አሜን ሃሌሉያ።
Priest :- Yi'izénee wezelfenee wele'alem alem amen halléluya.
Both now and ever and world without end. Amen.
ይበሉ ሕዝብ፦ ካህኑ ያለውን መልሰው ይበሉ
People :- (Shall repeat his words)
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ካህኑ የቅዱስ ባስልዮስን የምስጋና ጸሎት በዜማ እንዲህ ብሎ ይጀምር።
ለኛ በጎ ነገርን ያደረገ ይቅር ባይ እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን። ይቅር ባይ የጌታችን የአምላካችንና
The "Prayer of Thanksgiving" of St. Basil.
We give thanks unto the doer of good things unto us, the merciful God, the Father of our Lord and our God and our Savior Jesus Christ: for He hath
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ከርስቶስ አባት ሰውሮናልና ረድቶናልና ጠብቆ አቅርቦናልና ወደ እርሱም ተቀብሎናልና አጽንቶ ጠብቆናልና። እስከዚች ሰዓት አድርሶናልና።
covered us and succored us, He hath kept us and brought us nigh and received us unto Himself, and undertaken our defense, and strengthened us, and brought us unto this hour.
አሁንም ክብርት በምትሆን በዚች ዕለት በሕይወታችን ዘመን ሁሉ በፍጹም ሰላም ሁሉን የሚይዝ አምላካችን እግዚአብሔር ይጠብቀን ዘንድ እንለምነው።
Let us therefore pray unto Him that the Almighty Lord our God keep us in this holy day and all the days of our life in all peace.
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ
Deacon:- Tseliyu
Pray ye.
ይበል ካህን፦ ሁሉን የያዝህ ጌታችን እግዚአብሔር የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት በሥራው ሁሉ ላይ ስለ ሥራው ሁሉ በሥራውም ሁሉ ውስጥ እናመሰግንሃለን፣
Priest:- Master. Lord God Almighty, the Father of our Lord and our God and our Savior Jesus Christ, we render Thee thanks upon everything, for everything and in everything, for Thou hast covered us and succored us, hast kept us and
ሰውረኸናልና፣ ረድተኸናልና፣ ጠብቀኸናልና፣ ወዳንተ አቅርበኸናልና፣ ጥግ ሆነኸናልና፣ አጽንተኸናልና፣ እስከዚችም ሰዓት አድርሰኸናልና።
brought us high, and received us unto Thyself, and undertaken our defense, and strengthened us and brought us unto this hour.
ይበል ዲያቆን፦ ኀሡ ወአስተብቍዑ ከመ ይምሐረነ እግዚአብሔር ወይሣሀል ላዕሌነ፡ ወይትወከፍ
እግዚአብሔር ይምረን ዘንድ ይቅርም ይለን ዘንድ ደጅ ጥኑ ተማለዱ። (በንባብ) ስለእኛ ከቅዱሳን
Deacon:- Hisu we'astebiqwu'u keme yimharene Igzee'abihér weyisahal la'iléne. Weyitwekef
Entreat ye and beseech that the Lord have pity upon us and be merciful to us and receive prayer
ይበል ዲያቆን፦ ጸሎተ ወስእለተ እምነ ቅዱሳኒሁ በእንቲኣነ በዘይሤኒ ኵሎ ጊዜ ይረስየነ ድልዋነ
ጸሎትን ልመናንም ይቀበል ዘንድ ሁልጊዜ ባማረ ነገር ቡሩክ ከሚሆን ምስጢር
Deacon:- Tselote wesi'ilete imine qidusaneehu be'intee'ane bezeyisénee kwulu geezé yiresiyene dilwane
and supplication from his saints on our behalf according to what is expedient at all times, so that he may make us meet to partake of the communion
ይበል ዲያቆን፦ ከመ ንንሣእ እምሱታፌ ምስጢር ቡሩክ ወይሥረይ ለነ ኃጣዉኢነ።
አንድነት እንድንቀበል የበቃን ያደርገን ዘንድ።
Deacon:- Keme ninisa'i imsutafé misteer buruk weyisirey hataweene.
of the blessed sacrament and forgive us our sins.
ይበሉ ሕዝብ፦ ኪራላይሶን።
People:- Kyrie eleison.
ይበል ንፍቅ ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Ass’t Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ንፍቅ ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Ass’t Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ንፍቅ ካህኑ የሐዋርያትን የመባ ጸሎት በንባብ ይበል
ዳግመኛም ሁሉን የሚይዝ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንማልዳለን። ከሁሉ በላይ በምትሆን
Asst. Priest:- “The Prayer of Oblation” of the Apostles.
And again let us beseech the almighty Lord, the Father of the Lord our Savior Jesus Christ, on behalf of those who bring an oblation within the one holy
በከበረች በአንዲት ቤተክርስቲያን መባ ሰለሚያገቡ፣ መሥዋዕቱን፣ ቀዳምያቱንም ካሥር አንዱን፣ የመታሰቢያ ምስጋናን፣ ብዙውንና ጥቂቱን፣ የተሰወረውንና የተገለጸውን፣ ይሰጡ ዘንድ ሲወዱ
universal church, a sacrifice, first fruits, tithes, a thank offering, a memorial, whether much or little, in secret or openly, and of those who wish to give and have not wherewith to give, that He
የሚሰጡት ከሌላቸው ላይ ፈቃዳቸውን ተቀብሎ መንግሥተ ሰማያትን ይሰጥ ዘንድ ለሁሉ በረከትን የሚያድልበት ሥልጣን ገንዘቡ የሚሆን አምላካችን እግዚአብሔር።
accept their ready mind, that He vouchsafe to them the heavenly kingdom; power over all works of blessing belongs to the Lord our God.
ይበል ንፍቅ ዲያቆን፦ ጸልዩ በእንተ እለ ያበውኡ መባአ።
መባ ስለሚያቀርቡ ሰዎች ጸልዩ።
Asst. Deacon:- Tseliyu be'inte ile yabewi'u meba'i.
Pray for them who bring an oblation.
ይበሉ ሕዝብ፦ ተወከፍ መባኦሙ ለአኃው ወተወከፍ መባኦን ለአኃት ለነኒ ተወከፍ መባአነ ወቍርባነነ።
የወንዶችን መባቸውን ተቀበል። የሴቶችንም መባቸውን ተቀበል። የኛንም መባችንን ቁርባናችንንም ተቀበል።
People:- Tewekef meba'omu le'ahaw wetewekef meba'on le'ahat lenenee tewekef meba'ane weqwurbanene.
Accept the oblation of our brethren, accept the oblation of our sisters, and ours also accept, our oblation and our offering.
ንፍቅ ካህን፦ ሁሉን የምትገዛ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ! እንለምንሃለን እንማልድሃለንም ከሁሉ በላይ በምትሆን ባንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን ውስጥ መባ ስለሚያገቡ ሰዎች። መሥዋዕቱ፣
Asst. Priest :- Lord our God who art almighty, we pray Thee and beseech Thee for them that bring an oblation within the one holy universal church, a sacrifice, first-fruits, tithes, a thank
መጀመሪያውን፣ ካሥር አንዱን፣ የመታሰቢያ ምስጋናውን፣ ብዙውንና ጥቂቱን የተሰወረውንና የተገለጸውን ይሰጡም ዘንድ ሊወዱ የሚሰጡት ከሌላቸው ላይ ፈቃዳቸውን ተቀብለህ ለሁሉም
offering, a memorial, whether much or little, in secret or openly, and for those who wish to give and have not wherewith to give. Thy acceptance of their ready mind grant Thou unto every one:
የበረከት ዋጋን ስጥ፤ ዕድል ፈንታ ትሆን ዘንድ። በአንድ ልጅህ በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ላንተ ይገባል ከርሱ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ በእውነት።
let the recompense of blessing be a portion to all of them: through Thy only begotten Son, through whom to Thee with Him and with the Holy Spirit be glory and dominion, both now and ever and world without end. Amen.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ የኅብስት ጸሎት
መምህሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከቀዳማዊ አብ ጋራ አንድ የምትሆን፤ ንጹሕ የሚሆን የአብ ቃል፤ የማሕየዊ መንፈስ ቅዱስም ቃል፤ ከሰማያት የወረድህ የሕይወት ኅብስት አንተ ነህ። ስለ ዓለሙ መዳን ነውር
Priest:- ("The prayer of Oblation.")
O my Master, Jesus Christ, co-eternal pure Word of the Father, and Word of the Holy Spirit, the life giver, Thou art the bread of life which didst come down from heaven,
የሌለበት መሥዋዕት እንድትሆን መናገርን አስቀደምህ። አሁንም ከበጎነትህ ቸርነት እንለምናለን እንማልዳለንም። ሰው ወዳጅ ሆይ ያንተ በሚሆን በዚህ በመንፈሳዊው ታቦት ላይ ባኖርነው በዚህ ኅብስት ላይና በዚህ ጽዋ ላይ ፊትህን ግለጽ። ይህንን ኅብስት ባርከው
and didst foretell that Thou wouldest be the Lamb without Spot for the life of the world. We now pray and beseech of Thine excellent goodness, O lover of man, make Thy face to shine upon this bread, and upon this cup, which we have set upon this spiritual ark of Thine. Bless this bread,
ይህንንም ጽዋ አክብረው ሁለቱንም አንጻቸው። ይህ ንጹህ ሥጋህ ይሆን ዘንድ ለውጠው። በዚህ ጽዋ ውስጥ የተቀዳው ወይን የከበረ ደምህ ይሁን፤ ለሁላችንም ያረገ ለነፍሳችንና ለሥጋችን ለልቡናችንም ፈውስ ይሆን ዘንድ።
and hallow this cup, and cleanse them both. And change this bread to become Thy pure body, and what is mingled in this cup to become Thy precious blood, let them be offered for us all for healing and for the salvation of our soul and our body and our spirit.
አምላካችን ክርስቶስ የሁላችን ንጉሥ አንተ ነህ። ከፍ ያለ ምስጋናህንና ክብርን ስግደትንም ላንተ እንልካለን። ቸር ከሚሆን ከሰማያዊ አባትህ ጋራ ካንተ ጋራ ከሚተካከል ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ፤ አሜን።
Thou art the King of us all, Christ our God, and to Thee we send up high praise and glory and worship, with Thy good heavenly Father and the Holy Spirit, the life giver, who is coequal with Thee, both now and ever and world without end. Amen.
ይበል ዲያቆን፦ ያባቶቻችን የሐዋርያት ትእዛዝ ነው። ሰው በልቦናው ቂምንና በቀልን ቅንዓትንና ጠብን በባልንጀራው ላይ በማንም ላይ ቢሆን አይያዝ።
Deacon:- This is the order of our fathers the Apostles: Let none Keep in his heart malice or revenge or envy or hatred towards his neighbor, or towards any other body.
ይበል ዲያቆን፦ ስገዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት።
በፍርሃት ለእግዚአብሔር ስገዱ።
Deacon:- Sigidu le'Igzee'abihér befirihat.
Worship the Lord with fear.
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሓከ።
አቤቱ በፊትህ ወድቀን እንሰግዳለን። እናመሰግንሃለን።
People:- Qidméke igzee'o nisegid wenisébihake.
Before thee, Lord, we worship, and thee do we glorify.
ተንበርከኩ
Bow
ፍትሐት ዘወልድና በእንተ ቅድሳት በንባብ ከተስማ በኋላ የጸሎተ ዕጣን ሥርዓት እንዳበቃ ዲያቆኑ እንዲህ ይበል፣
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ ንስግድ። (፫ ጊዜ)
እንስገድ። (ሦስት ጊዜ)
Priest:- Nisigid (3 times)
Let's worship (3 times )
ይበሉ ሕዝብ፦ ለአብ፣ ወወልድ፣ ወመንፈስ ቅዱስ እንዘ ሠለስቱ አሐዱ። (፫ ጊዜ)
ሦስት ሲሆኑ አንድ ለሚሆኑ ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም። (ሦስት ጊዜ)
People:- Le'Ab, weWeld, weMenfes Qidus inze selestu ahadu. (3 times)
The Father and the Son and the Holy Spirit, three in one. (3 times)
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኪ።
ሰላም ላንቺ ይኹን።
Priest:- Selam lekee
Peace be unto Thee:
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅድስት ቤተክርስቲያን ማኅደረ መለኮት።
የመለኮት ማደሪያ የሆንሽ ክብርት ቤተክርስቲያን።
People:- Qidist béte kiristeeyan mahidere melekot.
Holy church, dwellingplace of the godhead.
ይበል ካህን፦ ሰአሊ ለነ።
ለምኚልን።
Priest:- Se'alee lene.
Ask for us:
ይበሉ ሕዝብ፦ ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ።
አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም።
People:- Dingil Mariam weladeete amlak.
Virgin Mary, mother of God,
ይበል ካህን፦ አንቲ ውእቱ።
አንቺ ነሽ።
Priest:- Antee wi'itu.
Thou art:
ይበሉ ሕዝብ፦ ማዕጠንት ዘወርቅ እንተ ፆርኪ ፍሕመ እሳተ ቡሩክ ዘነስኣ እመቅደስ ዘይሠሪ ኃጢአተ
ቡሩክ ከቤተ መቅደስ የተቀበላት የወርቅ ጽና አንቺ ነሽ፣ የእሳት ፍሕም የያዝሽ፣ ኃጢአትን
People:- Ma'itente zewerq inte tsorqee fihime isate buruk zenesi'a imeqdesi
The golden censer which didst bear the coal of fire which the blessed took from
ወይደመስስ ጌጋየ ። ዝውእቱ ዘእግዚአብሔር ቃል ዘተሰብአ እምኔኪ ዘአዕረገ ለአቡሁ ርእሶ ዕጣነ
የሚያስተሰርይ፤ በደልንም የሚያጠፋ። ይኸውም ካንቺ ሰው የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ነው።
Weyidemesis gégaye. Ziwi'itu ze'Igzee'abihér qal zetesebi'a imnekee ze'a'irege le'abuhu. ri'iso itane
the sanctuary, and which forgiveth sin and blotteth out error, who is God's Word that was, made man from
ወመሥዋዕተ ሥሙረ። ንሰግድ ለከ ክርስቶስ ምስለ አቡከ ኄር ሰማያዊ
ራሱን ያማረ ዕጣንና መሥዋዕት አድርጎ ለአባቱ ያቀረበ። ክርስቶስ ሆይ! ሰማያዊ ከሚሆን ከቸር
wemeswa'it simure. Nisegid leke Kiristos misle abuke hér semayawee
thee, who offered himself to his Father for incense and an acceptable sacrifice. We worship Thee, Christ, with Thy good heavenly Father
ወመንፈስከ ቅዱስ ማሕየዊ እስመ መጻእከ ወአድኀንከነ።
ራሱን ያማረ ዕጣንና መሥዋዕት አድርጎ ለአባቱ ያቀረበ። ክርስቶስ ሆይ! ሰማያዊ ከሚሆን ከቸር
wemenfesike qidus mahiyewee isme metsa'ike we'adhankene.
and Thy Holy Spirit, the life-giver, for Thou didst come and save us.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ ስብሐት ወክብር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ
ልዩ ሦስት ለሚሆኑ ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም
Priest:- Sebhat wekibir lesilus kidus yidelu
Glory and honor are meet to he Holy Trinity,
ይበል ዲያቆን፦ ይደልዎሙ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
Deacon :- Yidelwomu le’ab wewold wemenfes kidus
ይበል ካህን፦ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኵሎ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም
ሁል ጊዜ ክብር ምስጋና ይገባቸዋል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Priest:- Ab wewold wemenfes kidus kulo gize yi’izeni wezelfeni wele’aleme alem
the Father and the Son and the Holy Spirit at all times. Both now and ever and world without end. Amen.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን።
People:- Amen.
፩ ኛ ምንባብ፡
የመጀመሪያይቱ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት ወደ ቈላስይስ ሰዎች
ም ፫ ቍ ፩ - ፍ.ም
1st Reading:
2nd Epistle of St. Paul the Apostle to the Colossians
Ch. 3 : 1 - End
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱስ ሐዋርያ ጳውሎስ ሠናየ መልእክት ፈዋሴ ዱያን ዘነሣእከ አክሊለ ሰአል
ሐዋርያ ቅዱስ ጳውልስ መልእክትህ የበጀ፣ የታመሙትን ያዳንክ፣ አክሊልን የተቀበልህ፤
People:- Qidus hawariya Pawulos senaye mel'ikti fewasé duyane zenesa'ike akleele se'al wetselee
Holy Apostle Paul, good messenger, healer of the sick, who hast received the crown, ask and pray for us in order
ወጸሊ በእንቲኣነ ያድኅን ነፍሳተነ በብዛኅ ሣህሉ ወምሕረቱ በእንተ ስሙ ቅዱስ።
ስለእና ለምንልን፣ ጸልይልን። ስለቅዱስ ስሙ ብሎ በቸርነቱ በይቅርታው ብዛት ሰውነታችንን ያድነን ዘንድ።
Wetselee be'intee'ane yadihin nefsatene bebiziha sahilu wemihretu be'inte simu qidus.
that He may save our souls in the multitude of His mercies and in His pity for His holy name's sake.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
፪ ኛ ምንባብ፡
የመጀመሪያይቱ የቅዱስ ጴጥሮስ መልክት
ምዕ ፫ ቍ ፲፭ - ፍ.ም
2nd Reading:
1st Peter
Ch 3 : 15 - End
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱስ ሥሉስ ዘኅቡር ህላዌከ ዕቀብ ማኅበረነ በእንተ ቅዱሳን
ባሕርይህ አንድ የሚሆን፣ በሦስትነት ያለህ ቅዱስ ሆይ! አንድነታችንን ጠብቅልን፤
People:- Qidus silus zehibur hilawéke iqeb mahiberene be'inte qidusan
Holy con substantial Trinity, preserve our congregation for Thy holy elect disciples' sake:
ኅሩያን አርዳኢከ ናዝዘነ በሣህልከ በእንተ ቅዱስ ስምከ።
ስለተመረጡ ክቡራን ደቀመዛሙርትህ፤ ሰለቅዱስ ስምህም ብለህ በይቅርታህ አረጋጋን።
hiruyan arda'eeke nazizene besahilike be'inteqidus simike.
comfort us in Thy mercy, for Thy holy name's sake.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
፫ ኛ ምንባብ፡
የሐዋርያት ሥራ
ምዕ ፲፩ ቍ ፩ - ፲፱
3rd Reading:
Acts of the Apostle
Ch 11 : 1 - 19
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ አንተ አምላክ አብ አኃዜ ኵሉ።
ሁሉን የያዝህ አብ ሆይ! ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ አንተ ነህ።
People:- Qidus qidus qidus ante amlak Ab ahazé kwulu.
Holy Holy Holy art Thou, Father ,
ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ አንተ ወልድ ዋሕድ ዘአንተ ቃለ አብ ሕያው።
የሕያው አብ ቃል ተቀዳሚ ተከታይ የሌለህ ወልድ ሆይ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ አንተ ነህ።
Qidus qidus qidus ante weld wahid ze'ante qal Ab hiyaw.
Holy Holy Holy art Thou, only-begotten Son, who art the Word of the living Father.
ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ አንተ መንፈስ ቅዱስ ዘተአምር ኵሎ።
ሁሉን የምታውቅ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ አንተ ነህ።
Qidus qidus qidus ante Menfes Qidus zete'amir kwulo.
Holy Holy Holy art Thou, Holy Spirit who knowst all things.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ በእንተ …
Deacon:- Pray for …,
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን ኪራላይሶ እግዚኦ ተሣሃለነ።
People:- Amen Kyreeyalyso Igzio tesahalene.
ይበል ካህን፦ ደኅንነትን የምንለምንሽ ክብርን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ።
Priest:- Rejoice, O thou of whom we ask healing, O holy, full of honor,
ይበሉ ሕዝብ፦ ደስ ይበልሽ።
People:- Des yibelish.
Rejoice.
ይበል ካህን፦ ሁልጊዜ ድንግል የምትሆኝ አምላክን የወለድሽ የክርስቶስ እናት ሆይ ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ወደ ላይ ጸሎታችንን አሳርጊ።
Priest:- Ever-virgin, parent of God, mother of Christ, offer up our prayer on high to thy beloved Son that He may forgive us our sin.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን።
People:- Amen.
ይበል ካህን፦ በእውነት የጽድቅ ብርሃን የሚሆን አምላካችንን ክርስቶስን የወለድሽልን (ንጽሕት) ሆይ ደስ ይበልሽ።
Priest:- Rejoice, O thou who didst bear for us the very light of righteousness, even Christ our God:
ይበሉ ሕዝብ፦ ደስ ይበልሽ።
People:- Des yibelish.
Rejoice.
ይበል ካህን፦ ንጽሕት ድንግል ሆይ ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግልን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ጌታችን ለምኝልን።
Priest:- O Virgin pure, plead for us unto our Lord that He may have mercy upon our souls and forgive us our sins.
ይበሉ ሕዝብ፦ ለምኝልን።
People:- Plead for us
ይበል ካህን፦ በእውነት ለሰው ወገን አማላጅ የምትሆኝ አምላክን የወለድሽ ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ።
Priest:- Rejoice, O Virgin Mary, parent of God, holy and pure, very pleader for the race of mankind;
ይበሉ ሕዝብ፦ ደስ ይበልሽ።
People:- Des yibelish.
Rejoice.
ይበል ካህን፦ የኃጢአታችንን ሥርየት ይሰጠን ዘንድ በልጅሽ በክርስቶስ ፊት ለምኝልን።
Priest:- Plead for us before Christ thy Son, that He may vouchsafe us remission of our sins.
ይበሉ ሕዝብ፦ ለምኝልን።
People:- Plead for us
ይበል ካህን፦ በእውነት ንግሥት የምትሆኝ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ።
Priest:- Rejoice, O Virgin pure, very Queen;
ይበሉ ሕዝብ፦ ደስ ይበልሽ።
People:- Des yibelish.
Rejoice.
ይበል ካህን፦ የባሕርያችን መመኪያ ሆይ ደስ ይበልሽ።
Priest:- Rejoice, O pride of our kind;
ይበሉ ሕዝብ፦ ደስ ይበልሽ።
People:- Des yibelish.
Rejoice.
ይበል ካህን፦ አምላካችንን አማኑኤልን የወለድሽልን ሆይ ደስ ይበልሽ።
Priest:- Rejoice, O thou that barest for us Emmanuel our God.
ይበሉ ሕዝብ፦ ደስ ይበልሽ።
People:- Des yibelish.
Rejoice.
ይበል ካህን፦ በጌታችን በኢየሱስ ፊት እውነተኛ አስታራቂ ሆነሽ ታስቢን ዘንድ እንለምንሻለን። ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግልን ዘንድ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ።
Priest:- We ask thee to remember us, O true Mediatrix, before our Lord Jesus Christ that He may have mercy upon our souls and forgive us our sins.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን።
People:- Amen.
ይበል ካህን፦ ክርስቶስ ተንስአ እሙታን ሞተ ወኬዶ ለሞት ለእለ ውስተ መቃብር ወሀበ ሕይወተ ዘለዓለም እረፍተ።(፫ ጊዜ)
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ! ሞተ ሞትን አጠፋው። በመቃብርም ላሉ የዘላለም ዕረፍት የሚሆን ሕይወትን ሰጠ።
Priest:- Kiristos temsi’a imutan mote wekedo lemot le’ile wiste meqabir wehabe hiwete zela’lem irefte(3times).
Christ rose from the dead. He died and trampled death under foot. He gave the life of eternal rest to those who were in the grave.
ይበል ካህን፦ ዝውእቱ ጊዜ ባርኮት ወዝውእቱ ጊዜ ዕጣን ኅሩይ ጊዜ ሰብሖቱ ለመድኃኒነ መፍቀሬ ሰብእ ክርስቶስ።
ይህ የማመስገን ጊዜ ነው፣ የተመረጠ የዕጣን ጊዜም ነው፣ ሰውን የሚወድ መድኃኒታችን ክርስቶስ የሚመሰገንበት ጊዜ ነው።
Priest:- Ziwi'itu geezé barkot wez wi'itu geezé itan hiruy geezé sebihotu lemedhaneene mefeqeré seb'i kiristos.
This is the time of blessing; this is the time of chosen incense, the time of the praise of our Savior, lover of man, Christ.
ይበሉ ሕዝብ፦ ዕጣን ይእቲ ማርያም ዕጣን ውእቱ እስመ ዘውስተ ከርሣ ዘይትሜዐዝ እምኵሉ ዕጣን ዘወለደቶ መጽአ ወአድኀነነ።
ማርያም ዕጣን ናት፣ በማኅፀንዋ ያደረው ዕጣን እርሱ ነው። ከዕጣን ሁሉ የሚሸት ነውና፣ የወለደችው መጥቶ አዳነን።
People:- Itan yi'itee Mariam iTan wi'itu isme zewiste kersa zeyitimé'az imkwulu iTan zeweledeto metsi'a we'adhanene.
Mary is the incense, and the incense is He, because He who was in her womb is more fragrant than all chosen incense. He whom she bare came and saved us.
ይበል ካህን፦ ዕፍረት ምዑዝ ኢየሱስ ክርስቶስ ንዑ ንስግድ ሎቱ ወንዕቀብ ትእዛዛቲሁ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
መዓዛ ያለው ሽቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እንስገድለት ዘንድ ኑ! ትእዛዞቹንም እንጠብቅ ኃጢአታችንን ይቅር ይለን ዘንድ።
Priest:- Ireft mi'uz Eeyesus Kiristos ni'u nisigid lotu weni'iqeb ti'izazateehu keme yisirey lene haTaw'eene.
The fragrant ointment is Jesus Christ. O come let us worship Him and keep His commandments that He may forgive us our sins.
ይበሉ ሕዝብ፦ ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል ወብሥራት ለገብርኤል ወሀብተ ሰማያት ለማርያም ድንግል።
ምሕረት ለሚካኤል ተሰጠው። ማብሠር ለገብርኤል፣ ሰማያዊ ሀብትም ለድንግል ማርያም።
People:- Tewihibo mihiret leMeeka'él webisrat leGebri'él wehabte semayat leMariam Dingil.
To Michael was given mercy, and glad tidings to Gabriel, and a heavenly gift to the Virgin Mary.
ይበል ካህን፦ ተውህቦ ልቡና ለዳዊት ወጥበብ ለሰሎሞን ወቀርነ ቅብዕ ለሳሙኤል እስመ ውእቱ ዘይቀብዕ ነገሥተ።
ልቦና ለዳዊት ተሰጠው። ጥበብ ለሰሎሞን። የሽቱ ቀንድም ለሳሙኤል ንጉሦችን የቀባ ነውና።
Priest:- Tewihibo libuna leDaweet weTibeb leSelomon weqerine qib'I leSamu'el isme wi'itu zeyiqbi'a negeste.
To David was given understanding, and wisdom to Solomon, and an horn of oil to Samuel for he was the anointer of kings.
ይበሉ ሕዝብ፦ ተውህቦ መራኁት ለአቡነ ጴጥሮስ ወድንግልና ለዮሐንስ ወመልእክት ለአቡነ ጳውሎስ እስመ ውእቱ ብርሃና ለቤተክርስቲያን።
ሥልጣን ለአባታችን ጴጥሮስ ተሰጠው፣ ድንግልና ለዮሐንስ፣ መልእክት መጻፍ ለጳውሎስ፣ የቤተክርስቲያን ብርሃኗ ነውና።
People:- Tewihibo merahut le'abune PeTros wedingilina leYohanis wemeli'ikt le'abune Pawlos isme wi'itu birhana lebéte kiristeeyan.
To our father Peter were given the keys, and virginity to John, and apostleship to our father Paul, for he was the light of the church.
ይበል ካህን፦ ዕፍረት ምዕዝት ይእቲ ማርያም እስመ ዘውስተ ከርሣ ዘይትሌዐል እምኵሉ ዕጣን መጽአ ወተሠገወ እምኔሃ።
መዓዛ ያላት ሽቱ ማርያም ናት። የማኅፀንዋ ፍሬ ከዕጣን ሁሉ የሚበልጥ ነውና መጥቶ ከርሷ ሰው ሆነ።
Priest:- Ireft mi'izit yi'itee Mariam isme zewiste kersa zeyitlé'al imkwulu iTan meÍi'a wetesegewe imnéha.
The fragrant ointment is Mary, for He that was in her womb, who is more fragrant than all incense, came and was incarnate of her.
ይበሉ ሕዝብ፦ ለማርያም ድንግል ንጽሕት ሠምራ አብ ወአሠርገዋ ደብተራ ለማኅደረ ፍቁር ወልዱ።
ንጽሕት ድንግል ማርያምን አብ ወደዳት፤ ለተወደደ ልጁ ማደሪያ እንድትሆን አስጌጣት።
People:- LeMariam Dingil nitshit semra ab we'aserigewa debtera lemahidere fiqur weldu.
In Mary virgin pure the Father was well-pleased, and He decked her to be a tabernacle for the habitation of His beloved Son.
ይበል ካህን፦ ተውህቦ ሕግ ለሙሴ ወክህነት ለአሮን ተውህቦ ዕጣን ኅሩይ ለዘካርያስ ካህን።
ሕግ ለሙሴ ተሰጠው፤ ክህነት ለአሮን፣ የተመረጠም ዕጣን ለካህኑ ለዘካርያስ።
Priest:- Tewihibo hig leMusé wekihinet le'Aron tewihibo iÊan hiruy leZekariyas kahin.
To Moses was given the law, and priesthood to Aaron. To Zacharias the priest was given chosen incense.
ይበሉ ሕዝብ፦ ደብተራ ስምዕ ገብርዋ በከመ ነገረ እግዚእ ወአሮን ካህን በማእከላ የዐርግ ዕጣነ ኅሩየ።
ጌታ እንደተናገረ የምስክር ድንኳን አደረጓት፣ ካህኑ አሮን በመካከሏ የተመረጠ ዕጣን ያሳርጋል።
People:- Debtera sim'i gebriwa bekeme negere igzee'I we'Aron kahin bema'ikela ye'arig iTan hiruye.
They made a tabernacle of testimony according to the word of God; and Aaron the priest, in the midst thereof, made the chosen incense to go up.
በሕብረት፦ ሱራፌል ይሰግዱ ሎቱ ወኪሩቤል ይሴብሕዎ ይጸርሑ እንዘ ይብሉ።
ሱራፌል ይሰግዱለታል። ኪሩቤልም ያመሰግኑታል። እንዲህ እያሉ፣ ይዘምራሉ
Together:- Surafel yisegidulotu wekeerubél yisébihwo yiÍerhu inze yiblu.
The seraphim worship Him, and cherubim praise Him and cry saying:
በሕብረት፦ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር በኀበ አእላፍ ወክቡር በውስተ ረበዋት።
እግዚአብሔር በአእላፍ መላእክት ዘንድ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው። በአለቆችም ዘንድ ክቡር ነው።
Together:- Qidus qidus qidus Igzee'abihér behabe a'ilaf wekibur bewiste rebewat.
Holy Holy Holy is the Lord among the thousands and honored among the tens of thousands.
በሕብረት፦ አንተ ውእቱ ዕጣን ኦ መድኃኒነ እስመ መጻእከ ወአድኃንከነ ተሣህለነ።
መድኃኒታችን ሆይ! ዕጣን አንተ ነህ፤ መጥተህ አድነኸናልና። ይቅር በለን።
Together:- Ante wi'itu iTan o medhaneene isme meÍa'ike we'adhankene tesahalene.
Thou art the incense, O our savior, for Thou didst come and save us. Have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ቅዱስ።
Priest:- Qidus
Holy
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣህለነ እግዚኦ።
እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት፤ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደ፣ አቤቱ ይቅር በለን።
People:- Igzee'abihér, qidus hayal qidus hiyaw ze'eeyimewit zetewelde iMariam imqidist dingil tesahalene igzee'o.
God, holy Mighty, holy Living, Immortal, who was born from the holy Virgin Mary, have mercy upon us, Lord.
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል። ተሣህለነ እግዚኦ።
ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት፤ በዮርዳኖስ የተጠመቀ፣ በመስቀል ላይ የተሰቀለ አቤቱ ይቅር በለን።
People:- Qidus Igzee'abiher qidus hayal qidus hiyaw ze'iymewit zeteTemqe beYordanos weteseqle deebe itSe mesqel tesahalene igzio.
Holy God, Holy Mighty, Holy Living, Immortal, who was baptized in Jordan and crucified on the tree of the cross, have mercy upon us, Lord.
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት
ቅዱስ እግዚአብሔር፣ ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው የማይሞት፤ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይቶ የተነሣ፣
People:- Qidus Igzee'abihér qidus hayal qidus hiyaw ze'eeyimewit zetensi'a imutan ame salist ilet
Holy God, Holy Mighty, Holy Living, Immortal, who didst rise from the dead on the third day,
ይበሉ ሕዝብ፦ ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ
በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ የወጣ፣ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ፣
People:- Arge besibihat wiste semayat wenebere beyemane abuhu
Ascend into heaven in glory, sit at the right hand of thy Father and
ይበሉ ሕዝብ፦ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ።
በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ ዳግመኛ በጌትነት ይመጣል አቤቱ ይቅር በለን።
People:- Dagime yimeÍ'i besibhat yikwonin hiyawane wemutane tesahalene igzee'o.
again wilt come in glory to judge the quick and the dead, have mercy upon us, Lord.
ይበሉ ሕዝብ፦ ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ
ለአብ ምስጋና ለወልድ ምስጋና፣ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና
People:- Sibhat le'Ab sibhat leWeld sibhat leMenfes Qidus
Glory be to the Father, glory be to the Son, glory be to the Holy Spirit,
ይበሉ ሕዝብ፦ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ለዓለመ ዓለም አሜን ወአሜን ለይኩን፣ ለይኩን።
ዛሬም፣ ዘወትርም ለዘለዓለም እውነት በእውነት ይሁን፣ ይሁን።
People:- Yi'izénee wezelfenee wele'alem alem amen we'amen leyikun leyikun.
both now and ever and world without end. Amen and Amen, so be it, so be it.
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱስ ሥሉስ እግዚአብሔር ሕያው ተሣሃለነ።
በሦስትነት ያለህ ቅዱስ ሕያው እግዚአብሔር ሆይ! ይቅር በለን።
People:- Qidus silus Igzee'abihér hiyaw tesahalene.
O Holy Trinity, living God have mercy on us.
ይበል ካህን፦ ጸጋ ዘእግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ።
የእግዚአብሔር ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን።
Priest:- Tsega ze'Igzee'abihér yehalu.
The grace of God be with you.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ ንሰብሖ ለአምላክነ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።
Priest:- Nisebiho le'amlakine.
Let us glorify our God
ይበሉ ሕዝብ፦ ርቱዕ ይደሉ።
እውነት ነው ይገባል።
People:- Ritu'i yidelu.
It is right, it is just.
ይበል ካህን፦ አጽንዑ ሕሊና ልብክሙ።
የልባችሁን አሳብ አጽኑ።
Priest:- Atsni'u hileena libikimu.
Strengthen the thought of your heart,
ይበሉ ሕዝብ፦ ብነ ኀበ እግዚአብሔር አቡነ ዘበሰማያት፣ አቡነ ዘበሰማያት፣
በእግዚአብሔር ዘንድ አለን። አባታችን ሆይ! አባታችን ሆይ!
People:- Bine habe Igzee'abihér abune zebesemayat, abune zebesemayat,
We lift them unto the Lord our God. Our Father who art in heaven, Our Father who art in heaven,
ይበሉ ሕዝብ፦ አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
አባታችን ሆይ! አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
People:- Abune zebesemayat, eetabi'ane igzee'o wiste mensut.
Our Father who art in heaven, lead us not into temptation.
ካህኑ የኪዳን ጸሎት “እግዚአብሔር አብ …” የሚለውን በንባብ ሲያሰማ፤
ይበሉ ሕዝብ፦ ኪያከ ንሴብሕ እግዚኦ።
አቤቱ አንተን እናመሰግንሃለን።
As the priest starts to read the “O God theFather...” Prayer of the Covenant
People:- keeyake nisébih igzee'o
Oh we thank Thee.
ካህኑ የኪዳን ጸሎት “እግዚኦ ኢየሱስ ክርስቶስ …” በንባብ ሲያሰማ፤
ይበሉ ሕዝብ፦ ኪያከ ንዌድስ እግዚኦ።
አቤቱ አንተን እናወድስሃለን።
As the priest starts to read the ”O Lord, Jesus Christ ” Prayer of the Covenant
People:- keeyake niwédis igzee'o
Oh Lord, we praise Thee.
ካህኑ የኪዳን ጸሎት “ንሤልስ ለከ ዘንተ ቅዱስ …” አሰምቶ እንዳበቃ
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን።
በእውነት።
After the priest finishes reading the “Thrice over...” Prayer of the Covenant”
People:- Amen
ካህኑ የኪዳን ጸሎት “ንሤልስ ለከ ዘንተ ቅዱስ …” አሰምቶ እንዳበቃ
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን።
በእውነት።
After the priest finishes reading the “Thrice over...”
Prayer of the Covenant”
People:- Amen
ይበሉ ሕዝብ፦ ኦ ሥሉስ ቅዱስ መሐረነ፤ ኦ ሥሉስ ቅዱስ መሐከነ፤ ኦ ሥሉስ ቅዱስ ተሣሃለነ።
ልዩ ሦስት ሆይ ማረን፤ ልዩ ሦስት ሆይ ራራልን፤ ልዩ ሦስት ሆይ ይቅር በለን።
People:- O silus qidus meharene, O
silus qidus mehakene, o silus qidus
tesahalene.
O Holy Trinity, pity us, O Holy Trinity, spare us, O Holy Trinity, have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ተፈሥሒ፣ ተፈሥሒ፣ ተፈሥሒ ኦ ማርያም ድንግል ምልዕተ ጸጋ።
ጸጋን የተመላሽ ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፣ ደስ ይበልሽ፣ ደስ ይበልሽ።
Priest:- Tefesihee tefesihee tefesihee o Mariam dingil mil'ite tsega.
Rejoice, rejoice, rejoice, O Virgin Mary, full of grace.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚአብሔር ምስሌኪ
እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነው።
People:- Igzee'abihér mislékee.
The Lord is with thee.
ይበል ካህን፦ ተንብሊ ወሰአሊ ኀበ ፍቁር ወልድ።
ወደ ተወደደ ልጅሽ ለምኝልን አማልጅንም።
Priest:- tenbilee wese'alee habe fiqur weld.
Intercede and pray to thy beloved Son;
ይበሉ ሕዝብ፦ ከመ ይሥረይ ለነ ኃጣውኢነ።
ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዝንድ።
People:- Keme yisrey lene hataweene.
That he may forgive us our sins.
ይበል ካህን፦ ስብሐት ወክቡር ለሥሉስ ቅዱስ ይደሉ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
ልዩ ሦስት ለሚሆን ለአብና ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስም
Priest:- Sibhat wekibir lesilus qidus yidelu Ab weWeld weMenfes Qidus
Glory and honor are meet to the Holy Trinity, the Father and the Son and the Holy Spirit
ይበል ካህን፦ ኵሎ ጊዜ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም አሜን።
ሁልጊዜ ክብር ምስጋና ይገባቸዋል ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Priest:- kwulo geezé yi'izénee wezelfenee wele'alem alem amen.
at all times, both now and ever and world without end. Amen.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ አቤቱ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ! ክቡራን ንጹሐን ለሚሆኑ ደቀመዝሙሮችህ ለሐዋርያት እንዲህ ያልካቸው። (በንባብ) እናንተ የምታዩትን ያዩ ዘንድ ብዙ ነቢያት ጻድቃን ወደዱ፤ አላዩም። እናንት ዛሬ
Priest:- O Lord Jesus Christ, our God, who didst say to Thy holy disciples
and Thy pure apostles: Many prophets and righteous men have desired to
see the things which ye see and have
ይበል ካህን፦ የምትሰሙትንም ይሰሙ ዘንድ ወደዱ፤ አልሰሙም። የናንተ ያዩ ዓይኖቻችሁና የሰሙ ጆሮቻችሁ ግን የተመሰገኑ ናቸው።
Priest:- not seen them, and have desired to hear the things which ye hear and have not heard them, but you, blessed are your eyes that have seen and your ears that have heard,
ይበል ካህን፦ እኛንም እንደ እነሱ የበቃን አድርገን፤ በቅዱሳን ጸሎት የከበረ የወንጌልን ቃል ሰምተን እንሠራ ዘንድ።
Priest:- Do Thou make us also like them meet to hear and to do the word of Thy holy gospel through the prayer of the saints.
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ በእንተ ወንጌል ቅዱስ።
ክቡር ስለሚሆን ወንጌል ጸልዩ።
Deacon :- Tseliyu be'inte wengél qidus.
Pray for the holy gospel.
ይበሉ ሕዝብ፦ ይረስየነ ድልዋነ ለሰሚዐ ወንጌል ቅዱስ።
የከበረ ወንጌልን ለመስማት የበቃን ያድርገን።
People:- Yiresiyene dilwane leseme'ea wengél qidus.
May He make us meet to hear the holy gospel.
ይበል ካህን፦ ዳግመኛ አቤቱ ካንተ ዘንድ የምንሻውን በምንለምንበትና በምንጸልይበት ጊዜ እናስባቸው ዘንድ አስቡን ያሉንን ዳግመኛ አስብ።
Priest:- Remember again, Lord them that have bidden us to remember
them at the time of our prayers and supplications wherewith we make
request of Thee.
ይበል ካህን፦ አቤቱ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ከእኛ አስቀድመው የሞቱትን አሳርፋቸው የታመሙትንም ፈጥነህ አድናቸው።
Priest:- O Lord our God, give rest to them that have fallen asleep before us,
heal speedily them that are sick, for Thou art the life of us all, the hope of us
ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጎበኘኸኝ።
ፈተንከኝ ምክንያትም አላገኘህብኝም።
የሰውን ሥራ አንደበቴ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው
መዝ ፲፮ ፥ ፫
ምስባክ
ሐወጽከኒ ሌሊት ወፈትንኮ ለልብየ።
አመከርከኒ ወኢትረክበ ዐመፃ በላዕሌየ።
ከመ ኢይንበብ አፉየ ግብረ ዕጓለ እመሕያው
ይበል ዲያቆን፦ ሃሌሉያ! ቁሙ ወአጽምኡ ወንጌለ ቅዱስ፣ ዜናሁ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
ሃሌሉያ! ጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተናገረውን ክቡር የሚሆን ወንጌል ቆማችሁ አድምጡ።
Deacon :- Halléluya qumu we'atsmi'u wengéle qidus zenahu le'igzee'ine wemedhaneene Eeyesus Kiristos.
Halleluia, stand up and hearken to the holy gospel, the message of our Lord and Savior Jesus Christ.
ይበል ካህን፦ እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
Priest:- Igzee'abihér misle kwulikimu.
The Lord be with you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ ወንጌል ቅዱስ ዘዜነወ ማቴዎስ ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።
ክቡር የሚሆን ይህ ወንጌል ማቴዎስ የተናገረው የእግዚአብሔር ልጅ ቃል ነው።
Priest:- Wengél qidus zezénewe Matéwos qale weld igzee'abihér.
The holy gospel which Matthew proclaimed the Word of the Son of God.
ይበል ካህን፦ ወንጌል ቅዱስ ዘዜነወ ማርቆስ ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።
ክቡር የሚሆን ይህ ወንጌል ማርቆስ የተናገረው የእግዚአብሔር ልጅ ቃል ነው።
Priest:- Wengél qidus zezénewe Marqos qale weld igzee'abihér.
The holy gospel which Mark proclaimed the Word of the Son of God.
ይበል ካህን፦ ወንጌል ቅዱስ ዘዜነወ ሉቃስ ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።
ክቡር የሚሆን ይህ ወንጌል ሉቃስ የተናገረው የእግዚአብሔር ልጅ ቃል ነው።
Priest:- Wengél qidus zezénewe Luqas qale weld igzee'abihér.
The holy gospel which Luke proclaimed the Word of the Son of God.
ይበል ካህን፦ ወንጌል ቅዱስ ዘሰበከ ዮሐንስ ቃለ ወልደ እግዚአብሔር።
ክቡር የሚሆን ይህ ወንጌል ዮሐንስ የሰበከው የእግዚአብሔር ልጅ ቃል ነው።
Priest:- Wengél qidus zesebeke Yohanis qale weld igzee'abihér.
The holy gospel which John preached the Word of the Son of God.
ይበሉ ሕዝብ፦ ስብሐት ለከ ክርስቶስ እግዚእየ ወአምላኪየ ኵሉ ጊዜ
ጌታዬ ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ ሁልጊዜ ምስጋና ይገባሃል።
People:- Sibhat leke Kiristos igzee'iye we'amlakeeye kwulu geezé
Glory be to Thee, Christ my Lord and my God, at all times.
ይበሉ ሕዝብ፦ ተፈሥሑ በእግዚአብሔር ዘረደአነ ወየብቡ ለአምላክ ያዕቆብ ንሥኡ መዝሙር
ረዳት በሆነን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ የያዕቆብንም አምላክ አመስግኑ መዝሙር በሉ
People:- Tefesihu be'Igzee'abihér zeredi'ane weyebibu le-amlake Ya'iqob nisi'u mezmure
Sing aloud unto God our strength: make a joyful noise unto the God of Jacob. Take a psalm, and bring hither
ይበሉ ሕዝብ፦ ወሀቡ ከበሮ። መዝሙር ሐዋዝ ዘምስለ መሰንቆ።
ከበሮም ያዙ መዝሙር ከበገና ጋራ የተስማማ ነው።
People:- Wehabu kebero. mezmur hawaz zemisle mesenqo.
the timbrel, The pleasant harp with the psaltery.
በጾም ወራት
ይበሉ ሕዝብ፦ በወንጌል መራህከነ ወበነቢያት ናዘዝከነ ዘለ ሊከ አቅረብከነ ስብሐት ለከ።
በወንጌል መራኸን በነቢያትም አጽናናኸን ላንተ ላቀረብከን ምስጋና ይገባዋል።
People:- Bewengél merahikene webenebeeyat nazezikene zele leeke aqrebikene sibihat leke.
Thou hast guided us with the Gospel, comforted us with the prophets, and drawn us high unto Thee. Glory be to Thee.
የሉቃስ ወንጌል
ም ፳፬ ቍ ፴፫ - ፵፭
Gospel According to
Luke
C. 24 ፡ 33 - 45
የማቴዎስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ ነአምን አብ ዘበአማን፤ ወነአምን ወልደ ዘበአማን፤ ወነአምን መንፈሰ ቅዱስ ዘበአማን፤
አብን በእውነት እናምናለን፤ ወልድንም በእውነት እናምናለን፤ መንፈስ ቅዱስንም በእውነት
When reading is from Matthew
People:- Ne'amin Abe zebe'aman wene'amin Welde zebe'aman wene'amin Menfese Qiduse zebe'aman
We believe in the very Father, We believe in the very Son, and we believe
የማቴዎስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ ህልወ ሥላሴሆሙ ነአምን።
እናምናለን። የማይለወጠውን ሦስትነታቸውን እናምናለን።
When reading is from Matthew
People:- hiliwe silaséhomu neamin.
Holy Spirit, we believe in their unchangeable Trinity.
የማርቆስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ እሉ ኪሩቤል ወሱራፌል ያዐርጉ ሎቱ ስብሐተ እንዘ ይብሉ
እሊህ ኪሩቤል ሱራፌልም ል እርሱ ምስጋና ያቀርቡለታል። እንዲህ እያሉ
When reading is from Mark
People:- ilu keerubél wesurafél ya'arigu lotu sibhat inze yiblu
Those cherubim and seraphim offer to Him glory saying;
የማርቆስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እግዚአብሔር አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አንተ እግዚአብሔር ነህ
When reading is from Mark
People:- Qidus qidus qidus ante Igzee'abihér Ab weWeld WeMenfes Qidus.
Holy Holy Holy art Thou God, Father, Son and the Holy Spirit.
የሉቃስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ መኑ ይመስለከ እምነ አማልክት እግዚኦ አንተ ውእቱ ዘትገብር መንክረ አርአይኮሙ ለሕዝብከ ኃይለከ
አቤቱ ከአማልክት ወገን የሚመስልህ ማነው ተአምራትን የምታደርግ አንተ ነህ ኃይልህን ለወገኖችህ አሳየሃቸው። ወደ ሲዖል ወርደህ ምርኮን ከዚያ አወጣህ ነፃነትንም
When reading is from Luke
People:- Mmenu yimesileke inine amalikt igzee'o ante wi'itu zetigebir menkire ar'ayikomu lehizbike hayleke we'adhankomu lehizibike
Who is like unto Thee, O Lord, among the gods? Thou art the God that doest wonders: Thou hast declared Thy strength among the
የሉቃስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ ወአድኅንኮሙ ለሕዝብከ በመዝራዕትከ። ሖርከ ውስተ ሲኦል ወአዕረገ ፄዋ እምህየ ወጸጎከነ ምዕረ ዳግመ ግዕዛነ እስመ መጻእከ ወአድኅንከነ። በእንተ ዝንቱ
አቤቱ ከአማልክት ወገን የሚመስልህ ማነው ተአምራትን የምታደርግ አንተ ነህ ኃይልህን ለወገኖችህ አሳየሃቸው። ወደ ሲዖል ወርደህ ምርኮን ከዚያ አወጣህ ነፃነትንም
People:- hayleke we'adhankomu lehizibike bemezra'itike. horke wiste see'ol we'a'irege tséwa imhiye weÍegokene mi'ire dagime gi'izane
people. Thou hast with Thine arm redeemed Thy people. Thou didst go into Kades and the Captives rose up from there, and thou didst
የሉቃስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ ንሴብሓከ ውንጸርሕ ኅቤከ እንዘ ንብል ቡሩክ አንተ እግዚኦ ኢየሱስ ክርስቶስ እስመ መጻእከ ወአድኅንከነ።
ዳግመኛ ለዘለዓለም ሰጠኸን። መጥተህ አድነኸናልና። ስለዚህ እናመሰግንሃለን ወዳንትም እንዲህ እያልን እንጠራለን አቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ቡሩክ አንተ ነህ ሰው ሆነህ አድነኸናልና።
People:- be'inte zintu nisébihake weniÍerih habéke inze nibl buruk ante igzee'o Eeyesus Kiristos isme meÍa'ike we'adhankene.
come and save us. For this cause we glorify Thee and cry unto Thee saying, Blessed art Thou, Lord Jesus Christ, for Thou didst come and save us.
የዮሐንስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ ቃል ቃለ እግዚአብሔር ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ ወኅደረ ላዕሌነ ወርኢነ ስብሓቲሁ ከመ
ቃል አስቀድሞ የነበረ ያ ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው። ያ ቃል ሥጋ ሆነ በኛም አደረ። በአባቱ እንደ አንድ ልጅ
When the reading is from John
People:- Qedameehu qal wi'itu qal qale igzee'abihér wi'itu qal siga kone wehadere la'iléne wer'eene sibhateehu keme sibihat
In the beginning was the Word, the Word was the Word of God: The Word was made flesh, and dwelt among us, and we beheld his
የዮሐንስ ወንጌል ሲሆን
ይበሉ ሕዝብ፦ ስብሐተ አሐዱ ዋሕድ ለአቡሁ። ቃለ አብ ሕያው ወቃል ማሕየዊ ቃለ እግዚአብሔር ተንሥአ ወሥጋሁኒ ኢማስነ።
የሚሆን ክብሩን አየን የሕያው አብ ቃል ነው። ቃልም ሕይወትን የሚሰጥ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ተነሣ፤ ሥጋውም አልጠፋም።
People:- sibihat ahadu wahid leabuhu. qale Ab hiyaw we qal mahiyewee qale Igzee'abihér tensi'a wesigahunee eemasene.
glory, the glory as of the onlybegotten of the Father, the Word of the living Father, and the lifegiving Word, the Word of God, rose again and His flesh was not corrupted.
ይበል ዲያቆን፦ ፃኡ ንኡሰ ክርስቲያን።
የክርስቲያን ታናናሾች በሰላም ሂዱ።
Deacon :- Tsasu ni'use kiristeeyan.
Go forth, ye catechumens.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን አሐቲ ቅድስት ጉባኤ እንተ ሐዋርያት ርትዕት በኅበ እግዚአብሔር
ሐዋርያት ለሰበሰቡዋት በእግዚአብሔር ዘንድ ስለቀናች ክብርት ስለምትሆን አንዲት ቤተ ክርስቲያን ስላም ጸልዩ።
Deacon :- Tseliyu be'inte selame béte
kiristeeyan ahatee qidist guba'é inte hawariyat riti'it behabe Igzee'abihér.
Pray for the peace of the one holy apostolic church orthodox in the Lord.
ይበሉ ሕዝብ፦ ኪራላይሶን።
People:- Kyrie eleison.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ንፍቅ ዲያቆን፦ ጸልዩ በእንተ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ______ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት
ብፁዕ ስለሚሆን ስለ ሊቀ ጳጳሳቱ ስለ አባ ______ የደገኛዩቱ አገር ኢትዮጵያ ፓትርያርክ የሊቃነ
Asst. Deacon:- Tseliyu be'inte ri'ise leeqane papasat abba ______ partriarik ri'ise leeqane papasat zehager abay
Pray for the Patriarch Abba ______, lord chief of the bishops of the
ይበል ንፍቅ ዲያቆን፦ ዘሀገር ዐባይ ኢትዮጵያ ወዲበ ርእሰ ሀገር አበዊነ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ አባ _________ም
ጳጳሳቱ አለቃ ጌታ ስለሚሆን ባባቶቻችን አገርም ብፁዕ ስለሚሆን ስለ አባ ________ሃይማኖታቸው
Asst. Deacon:- Ethiopia wedeebe ri'ise hagere abeweene bisu'i leeqe papasat abba _______ wekwulomu épees
Ethiopia, and for the blessed Primate of the country of our fathers Abba ______ and all
ይበል ንፍቅ ዲያቆን፦ ወኵሎሙ ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ርቱዓነ ሃይማኖት።
ሃይማኖታቸው ስለ ቀና ስለ ኤጲስ ቆጶሳቱ ስለ ቀሳውስቱና ስለ ዲያቆናቱም ሁሉ ጸልዩ።
Asst. Deacon:- épees qoposat qesawist wedeeyaqonat ritu'ane haymanot.
the orthodox bishops, priests and deacons.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ በእንተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ቅድስት ወማኅበርነ በውስቴታ።
ክብር ስለምትሆን ስለዚች ቤተ ክርስቲያን በውስጥዋም ስላለ አንድነታችንም ጸልዪ
Deacon :- Tseliyu be'inte zatee béte
kiristeeyan qidist wemahiberene
bewisteta.
Pray for this holy church and our congregation therein.
ይበሉ ሕዝብ፦ ማኅበርነ ባርከ ዕቀብ በሰላም።
አንድነታችንን ባርክ በስላም ጠብቅ።
People:- Mahiberene barike iqeb beselam.
Bless our congregation and keep them in peace.
ይበል ዲያቆን፦ ንበል ኵልነ በጥበበ እግዚአብሔር ጸሎተ ሃይማኖት።
በእግዚአብሔር ጥበብ ሆነን ሁላችን የሃይማኖትን ጸሎት እንበል።
Deacon :- Nibel kwuline betibebe
Igzee'abihér tselote haymanot.
Let us all say, in the wisdom of God, the prayer of faith
ይበሉ ሕዝብ፦ ነአምን በአሐዱ አምላክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ገባሬ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተርኢ
ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
People:- ne'amin be'ahadu amlak Igzee'abihér Ab ahazé kwulu gebaré semayat wemidri
ze'eeyasteree weze'eeyasteree.
We believe in on God the Father almighty, maker of heaven, earth and all things visible and invisible.
ጸሎተ ሐይማኖት
ሁሉን በያዘ ሰማይንና ምድርን የሚታይና የማይታየውን በፈጠረ በአንድ አምላክ በእግዚአብሔር አብ እናምናለን።
ዓለም ሳይፈጠር ከርሱ ጋር በነበረ የአብ አንድ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስም እናምናለን።
The Prayer of Faith
We believe in on God the Father almighty, maker of heaven, earth and all things visible and invisible. And we believe in one Lord Jesus Christ, the only-begotten Son of the Father who was with Him before the creation of the world:
ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኝ አምላክ የተፈጠረ ያይደለ የተወለደ በመለኮቱ ከአብ ጋር የሚተካከል። ሁሉ በርሱ የሆነ ያለ እርሱ ግን ምንም ምን የሆነ የለም። በሰማይም ያለ በምድርም ያለ። ስለእኛ ስለሰው ስለ መዳኛችን ከሰማይ ወረደ።
Light from light, true God from true God, begotten not made, of one essence with the Father:By whom all things were make, and without Him was not any things in heaven or earth made: Who for us men and for our salvation came down from heaven,
ከመንፈስ ቅዱስ የተነሣ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፈጽሞ ሰው ሆነ። ሰው ሁኖ በጰንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን ስለእኛ ተሰቀለ። ታመመ ሞተ ተቀበረም በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደ ተጻፈ። በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ።
was made man and was incarnate from the Holy Spirit and from the holy Virgin Mary. Became man, was crucified for our sakes in the days of Pontius Pilate, suffered, died, was buried and rose from the dead on the third day as written in the holy scriptures: Ascended in glory into heaven, sat at the right hand of His Father,
ዳግመኛ ሕያዋንን ሙታንንም ይገዛ ዘንድ በጌትነት ይመጣል። ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም። ጌታ ማሕየዊ በሚሆን ከአብ በሠረፀ በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን። እንሰግድለት እናመሰግነውም ዘንድ ከአብና ከወልድ ጋር በነቢያት የተናገረ።
and will come again in glory to judge the living and the dead; there is no end of His reign. And we believe in the Holy Spirit, the life-giving God, who proceedeth from the Father; we worship and glorify Him with the Father and the Son; who spoke by the prophets;
ከሁሉ በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሰበሰብዋት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እናምናለን።
ኃጢአትን ለማስተሥረይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን። የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።
And we believe in on holy, universal, apostolic church, And we believe in one baptism for the remission of sins, and wait for the resurrection from the dead and the life to come, world without end. Amen.
ይበሉ ሕዝብ፦ ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወተ ዘይመጽእ ለዓለም ዓለም አሜን።
የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘላለሙ አሜን።
People:- weniséfo tinsa'é mutan wehiywete zeyimeÍi'i le'aleme alem amen.
and wait for the resurrection from the
dead and the life to come, world without
end. Amen.
ይበል ንፍቅ ካህን፦ንጹሕ የሆነ ከቍርባኑ ይቀበል፤ …
Asst. Priest:- He that is pure let him receive of the oblation and he that is not pure let him not receive it, that he may not be consumed by the fire of the godhead which is prepared for the devil and his angels. Who so hath revenge in his heart and who so hath in him strange thoughts and fornication let him not draw nigh. As I have cleansed my hands from outward pollution, so also I am pure from the blood of you all. If you presumptuously draw nigh to the body and blood of Christ I will not be responsible for your reception thereof. I am pure of your wickedness but your sin will return upon your head if you do not draw nigh in purity.
ይበል ዲያቆን፦ ይህን የቄሱን ቃል ያቀለለ ወይም የሳቀና የተነጋገረ ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በክፋት የቆመ ቢኖር ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዳሳዘንው በርሱም እንደ ተነሣሣ ይወቅ ይረዳ ስለ በረከት ፈንታ መርገምን ስለ ኃጢአት ሥርየት ፈንታም ገሃነመ እሳትን ከእግዚአብሔር ዘንድ ይቀበላል
Deacon :- If there be any who disdains this word of the priest or laughs or speaks or stands in the church in an evil manner, let him know and understand that he is provoking to wrath our Lord Jesus Christ, and bringing upon himself a curse instead of a blessing, and will get from God the fire of hell instead of the remission of sin.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ባስልዮስ የተናገረው የአምኃ ጸሎት
ይበል ካህን፦ ለዘላለሙ ገናና የምትሆን እግዚአብሔር ሆይ ያለጥፋት ሰውን የፈጠርኸው። አስቀድሞ በሰይጣን ቅንዓት የገባውን ሞት …
“Prayer of Salutation” of St. Basil:
Priest:- God, great eternal, who didst form a man uncorrupt,
ይበሉ ሕዝብ፦ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለስብእ
በሰማይ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይገባል ሰላም በምድር ፍቅሩ ለሰው ሆነ።
People:- Sibhat le'Igzee'abihér besemayat weselam bemidir simretu leseb'i.
Glory to God in heaven and on earth peace, His goodwill toward men.
ይበል ካህን፦ አቤቱ ፈቃድህን በሁላችን ልቡና ሙላ፤
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ በእንተ ሰላም ፍጽምት ወፍቅር ተአምኁ በበይናቲክሙ በአምኃ ቅድሳት።
ፍጽምት ስልምትሆን ሰላምና ፍቅር ጸልዪ እርስ በርሳችሁ በተለየች ሰላምታ እጅ ተነሳሱ።
Deacon:- Tseliyu be'inte selam fitsimt wefiqir te'amihu bebeyinateekimu be'amiha qidisat.
Pray for the perfect peace and love. Salute one another with a holy salutation
ይበሉ ሕዝብ፦ ክርስቶስ አምላክነ ረሰየነ ድልዋነ ከመ ንትአማኅ በበይናቲነ በአምኃ ቅድሳት
ፈጣሪያችን ክርስቶስ ሆይ እርስ በርሳችን በከበረች ሰላምታ እጅ እንነሳሳ ዘንድ የበቃን አድርገን።
People:- Kiristos amlakine resiyene diliwane keme niti'amah bebeyinateene be'amiha qidisat.
Christ our God, make us meet to salute one another with a holy salutation.
ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ
The Anaphora Diyoscoros
ይበል ካህን፦ አኮቴተ ቁርባን ዘቅዱስ ዲዮስቆሮስ በረከቱ ጸሎቶሙ የሀሉ ምስለ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቲነ አባ ______ ወምስለ ሊቀ ጳጳስነ አባ ______ ወምስለ ኵልነ ሕዝበ ክርስቲያን ወይ ዕቀባ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ ለዓለም ዓለም አሜን።
የቅዱስ ዲዮስቆሮስ የቍርባን ምስጋና። የፀሎታቸው በረከት በጳጳሳቱ አለቃ በአባ ______ በጳጳሳችን በአባ ______ በሁላችንም ላይ ይደር አገራችንን ኢትዮጵያን ይጠብቃት ለዘላለሙ አሜን።
Priest:- The Anaphora of St. Dioscorus; may his prayer and blessing be with our Patriarch Abba ______ and Our Bishop Abba _____, and may he watch over Ethiopia, world without end. Amen.
ይበል ካህን፦ እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
Priest:- Igzee'abihér misle kwulikimu.
The Lord be with you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ አእኵትዎ ለአምላክነ
ፊጣሪያችንን አመስግኑት
Priest:- A'ikwutiwo le'amlakine
Give ye thanks unto our God.
ይበሉ ሕዝብ፦ ርቱዕ ይደሉ
እውነት ነው ይገባዋል።
People:- Ritu'i yidelu.
It is right, it is just.
ይበል ካህን፦ አልዕሉ አልባቢክሙ
ልቦናችሁ ሰማያዊ ነገር ያስብ።
Priest:- Al'ilu albabeekimu.
Lift up your hearts.
ይበሉ ሕዝብ፦ ብነ ኅበ እግዚአብሔር አምላክነ።
በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ዘንድ ተስፋ አለን።
People:- Bine habe Igzee'abihér amlakine.
We have lifted them up unto the Lord our God.
ይበል ካህን፦ እግዚአብሔር ከዓለም በፊት እስከ ዘላለምም ድረስ፤ እግዚአብሔር በሦስትነቱ አለ እግዚአብሔር በመለኮቱ፤ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ። ከጎሕና ከጽባሕ በፊት፤ ከመዓልትና ከሌሊት በፊት፤ መላእክት ሳይፈጠሩ እግዚአብሔር በመንግሥቱ አለ።
Priest:- From before the world and ever after, God is in His trinity, God is in His divinity, and God is in His kingdom. Before the dawn and the morning, before day and
night, and before the creation of the angels, God was in His kingdom.
ይበል ካህን፦ ሰማያት ሳይዘረጉ የየብስም ፊት ሳይታይ፣ ሐመልማላት ሳይበቅሉ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
ከፀሓይና ከጨረቃም ከከዋክብትም በፊት፤ ከብርሃናትም መመላለስ ፊት እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
Priest:- Before the heavens were stretched out, before the face of the earth appeared, and before the green plants were produced, God was in His kingdom. Before the sun, the moon, the stars and before the motion of lights, God was in His kingdom.
ይበል ካህን፦ ከሚንቀሳቀስ እንስሳ በፊት፤ ከሚበሩም አዕዋፍ በፊት፤ ከባሕር አራዊት በፊት፤ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ። አዳምን በርሱ አምሳልና አርኣያ ሳይፈጥረው፤ ትእዛዙንም ሳያፈርስ እግዚአብሔር በመንግሥቱ ነበረ።
Priest:- Before the moving beasts, the flying birds, and before the beasts of the sea, God was in His kingdom. Before He created Adam after His image and likeness and before Adam transgressed His commandment, God was in His kingdom.
ይበል ካህን፦ ስብሐት ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል፤ ዛሬ ዘወትርም ለዘላለምም።
Priest:- sibhat le'Ab weWeld weMenfes Qidus yi'izénee wezelfenee wele'aleme alem.
Glory be to the Father, the Son and the Holy Spirit, both now and ever and world without end.
ይበል ዲያቆን፦ በአንተ ብፁዕ ወቅዱስ አባ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት። ወብፁዕ ሊቀ ጳጳስነ አባ አብርሃም።
ብፁዕ ቅዱስ ስለሚሆን ስለ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ አባ ጳውሎስ ብፁዕም ስለሚሆን ስለ አባ አብርሃም በጸሎታቸውና
Deacon:- Beinte bitsu'i weqidus ri'ise leeqane papasat aba Pawulos webitsu'i leeqe papas aba Abraham
For the sake of the blessed and holy Patriarch Abba Pawulos and the blessed Archbishop Abba Abraham while they
ይበል ዲያቆን፦ እንዘ የአኵቱከ በጸሎቶሙ ወበስእለቶሙ እስጢፋኖስ ቀዳሜ ሰማዕት ዘካርያስ ካህን ወዮሐንስ መጥምቅ። …
በልመናቸው ሲያመስግኑህ የሰማዕታት መጀመሪያ እስጢፋኖስ። ካህን ዘካርያስና መጥምቁ ዩሐንስ።
Deacon:- inze ye'akwutuke betselotomu webes'iletomu Isteefanos qedame sema'it. Zekarias kahin weyohanis metmiq.
yet give thee thanks in their prayer and in their supplication: Stephen the first martyr, Zacharias the priest and John the Baptist..
ንፍቅ ካህኑ ቅዱስ ባስልዮስ የተናገረውን የቡራኬ ጸሎት ይበል።
ይበል ንፍቅ ካህን፦ ልዩ ሦስት የምትሆን …
The assistant priest shall say the "Prayer of Benediction" of St. Basil.
Asst. Priest:- O Holy Trinity, Father and Son and Holy Spirit, bless Thy people, Christians beloved, …
ይበል ዲያቆን፦ መሐሮሙ እግዚኦ ወተሣሃሎሙ ለሊቃነ ጳጳሳት፣ ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ወኵሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን።
አቤቱ የጳጳሳት አለቃ ጳጳሳቱን ኤጲስ ቆጶሳቱን ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱን የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ ማራቸው ይቅርም በላቸው።
Deacon:- Meharomu igzee'o wetesahalomu leleeqane papasat papast épeesqoposat qesawist wedeeyaqonat wekwulomu hizbe kiristeeyan.
Lord pity and have mercy upon the patriarchs, archbishops, bishops, priest, deacons and all the Christian people.
ይበል ካህን፦ ይስማዕ ሰማይ ወታጽምእ ምድር ወይደንግፁ መሠረታት ሕምዝ።
ሰማይ ይስማ ምድርም ታድምጥ የምድር መሠረቶችም ይድንግጡ።
Priest:- Let heaven hear, the earth
listen, and the foundations of the
earth be afraid.
ይበል ዲያቆን፦ እለ ትነብሩ ተንሥኡ።
የተቀመጣችሁ ተነሱ።
Deacon:- ile tinebiru tensi'u.
Ye that are sitting, stand up.
ይበል ካህን፦ በፈቃደ አቡሁ ወረደ ኀበ ማርያም ተአንገደ በድንግልናሃ ንጹሕ እግዚአብሔር ተወልደ።
በአባቱ ፈቃድ ወረደ፤ በማርያም ዘንድ እንግዳ ሆነ፤ እግዚአብሔር በንጹሕ ድንግልናዋ ተወለደ።
Priest:- The Lord came down through the will of His Father, sojourned in Mary and was born while she was a pure virgin.
ይበል ዲያቆን፦ ውስተ ጽባሕ ነጽሩ።
ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ።
Deacon:- Wiste tsibah netsiru..
Look to the east.
ይበል ካህን፦ በእንስሳት በረት ተጨመረ፤ የንግሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ፤ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ። በግልጥ ተመላለሰ፤ እንደ ሰውም ታየ፤ በየጥቂቱ አደገ፤ በሠላሳ ዘመን በዮርዳኖስ
ተጠመቀ።
Priest:- He was laid in the manger of the cattle, received the presents of His kingdom, and wept as infants do, asking for food from the breasts of His mother. He walked openly and appeared like a man, grew little by little and was baptized in Jordan at the age of thirty.
ይበል ዲያቆን፦ ንነጽር
እናስተውል።
Deacon:- Ninetsir.
Let us give heed.
ይበል ካህን፦ ከመ እንተ ብእሲ ለጸዊም በውስተ ገዳም ኀደረ እምኀበ ዲያብሎስ ተመከረ በኃይለ መለኮቱ መኳንንተ ጽልመት ሠዐረ።
እንደ ሰው ሆኖ ለመጾም በገዳም አደረ፤ ከዲያብሎስ ዘንድ ተፈተነ፤ የጨለማን መኳንንት በአምላክነቱ ኃይል ሻረ።
Priest:- He stayed in the wilderness as a fasting man, was tempted by the Devil and He degraded the rulers of darkness through the power of His divinity.
ይበል ዲያቆን፦ አውሥኡ
ተሰጥዎውን መልሱ።
Deacon:- Awsi’u.
Answer ye.
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ ሰማያት ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።
ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ፍጽም አሸናፊ እግዚአብሔር የጌትነትህ ምስጋና ሰማይና በምድር የመላ ነው።
People:- Qidus qidus qidus Igzee'abihér tseba'ot fitsum milu'I semayate wemidre qidisate sibhateeke.
Holy Holy Holy, perfect Lord of hosts, heaven and earth are full of the holiness of Thy glory.
ይበል ካህን፦ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር በሥላሴሁ እንዘ ነጋሢ ለሊሁ አርአየ ትሕትናሁ ከመ ገብር።
እግዚአብሔር በሦስትነቱ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ይባላል፤ እርሱ ንጉሥ ሲሆን እንደ ባሪያ ትሕትናውን አሳየ።
Priest:- Holy, Holy, Holy God in His trinity; being a king He showed His humility like a servant.
ይበሉ ሕዝብ፦ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅ በውስተ መንግሥትከ።
አቤቱ በመንግሥትህ አስበን አቤቱ መምህራችን ሆይ በመንግሥትህ አስበን። አቤቱ በመንግሥትህ
People:- Tezekerene igzee'o bewiste mengistike tezekerene igzee'o O leeq bewiste mengistike
Remember us, Lord, in Thy kingdom; remember us, Lord, Master, in Thy kingdom; remember us, Lord, in Thy kingdom, as Thou didst remember
ይበሉ ሕዝብ፦ ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። በከመ ተዘከርኮ ለፊያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ።
አቤቱ በመንግሥትህ አስበን ቅዱስ በሚሆን በዕፀ መስቀል ላይ ሳለህ ፈያታዊ ዘየማንን እንዳሰብከው አቤቱ በመንግሥትህ አስበን።
People:- Tezekerene igzee'o bewiste mengistike. Bekeme tezekerko lefiyatawi zeyeman enze haloke dibe itse meskel kidus.
Remember us, Lord, in Thy kingdom;
ይበል ካህን፦ ሰፍሐ እደዊሁ ለሕማም ዘለሐኰ ሰብአ ከመ ያግዕዞ ለአዳም እምአርዑተ ኃጢአት፤
ሰውን የፈጠረ እርሱ እጁን ለሕማም ዘረጋ አዳምን ከኃጢአት ቀንበር ነፃ ያደርገው ዘንድ
Priest:- He who created man stretched forth His hands for suffering to set free Adam from the
yoke of sin.
ይበል ዲያቆን፦ አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስት።
ቀሳውስት እጆቻችሁን አንሡ
Deacon:- Ansi'u ideweekimu qesawist.
Priests, raise up your hands.
ይበል ካህን፦ እርሱን በሚያስይዙባት በዚያች ሌሊት ነውር በሌለባቸው ቅዱሳት ብፁዓት በሆኑ እጆቹ ኅብስቱን ያዘ።
Priest:- In the same night in which they betrayed Him, He took bread in His holy, blessed and spotless hands.
ይበሉ ሕዝብ፦ ነአምን ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
ይህ በእውነት እንደሆነ እናምናለን።
People:- Ne'amin kemzintu wi'itu be'aman ne'amin.
We believe that this is He, truly we believe.
ይበል ካህን፦ ወዳንተ ወዳባቱ ወደ ሰማይ አቅንቶ አየ አመሰገነ ባረከ ቈረሰም። ንጹሐን ቅዱሳን ወገኖቹ ለሆኑ ደቀ መዛሙርቱ ለሐዋርያት ሰጣቸው፤ ይህ ኅብስት ለኃጢአት ማስተሠረያ ስለናንተ የሚፈተት ሥጋዬ ነው ንሡ ብሉ አላቸው።
Priest:- He looked up to heaven towards you, His Father, gave thanks, blessed and broke and He gave to His holy disciples and His pure apostles and said unto them:
Take, eat, this bread is my body which will be broken for you for the remission of sin.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን፣ አሜን፣ አሜን ነአምን ወንትአመን ንሴብሓከ ኦእግዚእነ ወአምላክነ ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
እውነት፣ እውነት፣ እውነት እናምናለን እንታመናለን ጌታችን ፍጣሪያችን ሆይ እናመሰግንሃለን ይህ በእውነት ሥጋህ እንደሆነ እናምናለን።
People:- Amen amen amen: ne'amin wenit‘ amen nisebihake O igzee'ine we'amlakine keme zintu wi'itu be'aman ne'amin.
Amen amen amen: We believe and confess, we glorify Thee, O our Lord and our God; that this is He we truly believe.
ይበል ካህን፦ ዳግመኛ ውኃውን ከወይን ጋራ ቀላቅሎ አመሰገነ ባረከ አከበረ። ንጹሓን ቅዱሳን ወገኖቹ ለሆኑ ደቀ መዛሙርቱ ለሐዋርያት ሰጣቸው ይህ ጽዋ “እማሬ” ለብዙ ሰዎች ቤዛ ስለናንተ የሚፈስ ደሜ ነው ንሡ ጠጡ አላቸው።
Priest:- Again He mixed water with wine, gave thanks, blessed, hallowed and gave it to His holy disciples and His pure apostles and said unto them: take, drink, this cup is my blood which will be shed for you as a propitiation for many.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን፣ አሜን፣ አሜን ነአምን ወንትአመን ንሴብሓከ ኦእግዚእነ ወአምላክነ ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
እውነት፣ እውነት፣ እውነት እናምናለን እንታመናለን ጌታችን ፍጣሪያችን ሆይ እናመሰግንሃለን ይህ በእውነት ሥጋህ እንደሆነ እናምናለን።
People:- Amen amen amen: ne'amin wenit‘ amen nisebihake O igzee'ine we'amlakine keme zintu wi'itu be'aman ne'amin.
Amen amen amen: We believe and confess, we glorify Thee, O our Lord and our God; that this is He we truly believe.
ይበል ካህን፦ አይሁድ ያዙት የመላእክት ሠራዊት በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የሚቆሙለትን እርሱን በዐደባባይ አቆሙት።
Priest:- The Jews took hold of Him and made Him stand in the court, Him before whom the hosts of angels stand in fear and trembling.
ይበል ካህን፦ በዕንጨት ላይ ሰቅለው በቀኖት ቸነከሩት፤ ራሱንም በዘንግ መቱት ጐኑን በጦር ወጉት፤ ለጉበኞች እስራኤል ካንድ ድንጋይ ያጠጣቸውን ለጥሙ ከከርቤ ጋራ የተቀላቀለ ሐሞትን አጠጡት።
Priest:- They crucified Him on the tree, nailed Him with nails, beat Him on the head with sticks, pierced His side with a spear, to Him who gave drink to the Israelites from a rock they gave to drink gall mixed with myrrh in His thirst.
ይበል ካህን፦ የማይሞት እርሱ ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ፤ በቃል ኪዳን ተስፋው እንደ ነገራቸው።
Priest:- The immortal died, died to destroy death, died to quicken the dead as He promised them with the word of covenant.
ይበሉ ሕዝብ፦ ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ ወትንሣኤከ ቅድስተ ነአምን ዕርገተከ ወዳግመ ምጽአተከ ንሴብሓከ
አቤቱ ሞትህን ክብርት የምትሆን ትንሣኤህንም እንናገራለን ዕርገትህን ዳግመኛ መምጣትህንም
People:- Nizénu moteke igzee'o wetinsa'éke qidist ne'amin irgeteke wedagime mitsi'ateke nisebihake
We proclaim Thy death, Lord, and Thy holy resurrection; we believe in Thy ascension and Thy second advent.
ይበሉ ሕዝብ፦ ንሴብሓከ ወንትአመነከ ንስእለከ ወናስተበቍዐከ ኦ እግዚእነ ወአምላክነ።
እናምናለን ጌታችን ፈጣሪያችን ሆይ! እናመሰግንሃለን፤ እናምንሃለን፤ እንለምንሃለን፤ እንማልድሃለን።
People:- Weniti'ameneke nis'ileke wenastabiqwu'ake O igzee'ine we amlakine.
We glorify Thee, and confess Thee, we offer our prayer unto Thee and supplicate Thee, O our Lord and our God.
ይበል ካህን፦ ከዕንጨት አወረዱት በበፍታም ገንዘው በአዲስ መቃብር ቀበሩት። በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ የተሰበሰቡ ደቀ መዛሙርቱ ወዳሉበትም ገባ፤ በጽርሐ ጽዮንም ታያቸው፤
Priest:- They took Him down from the tree, wrapped Him in linen cloths, and buried Him in a new grave. He rose from the dead on the third day, and entered where His disciples were gathered and appeared to them in the upper room of Zion,
ይበል ካህን፦ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ባረገ ጊዜ የአብን ተስፋ ደጅ ጥኑ ብሎ አዘዛቸው። በአምሳውም ቀን በእሳት አምሳል መንፈስ ቅዱስን ሰደደላቸው በአገሩም ቋንቋ ተናገሩ፤
Priest:- and when He ascended unto heaven on the fortieth day He ordered them saying, Wait for the promise of the Father. On the fiftieth day He sent to them the Holy Sprit in the likeness of fire, and they spoke in the languages of all countries;
ይበል ካህን፦ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ሥጋና ደም ያደርገው ዘንድ ለዘላለሙ።
አንተ ሥጋዬን የበላ ደሜንም የጠጣ ከእኔ ጋራ ይኖራል እኔም ከእርሱ ጋራ እኖራለሁ እንዳልህ።
Priest:- so also, as Thou didst with them, send the Holy Spirit over this bread and this cup to make them the body and blood of our Lord and Savior Jesus Christ, world without end: as Thou didst say, He that eats my flesh, and drinks my blood, dwells in me, and I in Him.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን እግዚኦ መሐረነ እግዚኦ መሐከነ እግዚኦ ተሣሃለነ
እውነት አቤቱ ማረን አቤቱ ራራልን አቤቱ ይቅር በለን።
People:- Amén; igzee'o meharene, igzee'o mehakene, igzee'o tesahalene.
Amen; Lord have pity upon us, Lord spare us, Lord have mercy upon us.
ይበል ዲያቆን፦ በኵሉ ልብ ናስተበቍዖ ለእግዚአብሔር አምላክነ ኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ሠናየ ከመ ይጸግወነ።
በፍጹም ልብ ፈጣሪያችን እግዚአብሔርን እንማልደው ያማረ የመንፈስ ቅድስን አንድነት ይሰጠን ዘንድ።
Deacon:- Bekwulu lib nastebiqwu'o le'Igzee'abihér amlakine hibrete Menfes Qidus senaye keme yitsegiwene.
With all the heart let us beseech the Lord our God that He grant unto us the good communion of the Holy Spirit.
ይበሉ ሕዝብ፦ በከመ ሀሎ ህልወ ወይሄሉ ለትውልደ ትውልድ ለዓለመ ዓለም።
በፊት እንደነበረ ለዘላለሙ ለልጅ ልጅ ይኖራል።
People:- Bekeme halo hiliwe weyihélu letiwlide tiwlid le'aleme alem.
As it was, is and shall be unto generations of generations, world without end.
ይበል ካህን፦ ደሚረከ ተሀብ ለኵሉ ሕዝብከ ይኩኖሙ ለሕይወት ወለአንጽሖ እምርስሐት ለዓለመ ዓለም።
ለሕይወትና ለዘላለም ከኃጢአት ለማንጻት ይሆናቸው ዘንድ ለወገኖችህ ሁሉ አንድ አድርገህ ስጥ።
Priest:- demeereke tehab lekwulu hizbike yikunomu lehiywet wele'anÍiho imrisihat le'aleme alem.
Grant it together unto all Thy people that it may be unto them for life and for purification from sin, world without end.
ይበል ካህን፦ ሀበነ ንኅበር በዘዚኣከ መንፈስ ቅዱስ ወፈውሰነ በዝንቱ ጵርስፎራ
ያንተ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ ስጠን። በዚህም ጵርስፎራ (በሥጋውና ደሙ) አድነን።
Priest:- Habene nihiber bezezee'ake Menfes Qidus. Wefewisene bezintu pirsifora
Grant us to be untied through Thy Holy Spirit, and heal us by this
ይበሉ ሕዝብ፦ ሕዝብ ካህኑን ይቀበል።
People:- Repeat his words!
ይበል ካህን፦ ከመ ብከ ንሕየው ዘለኵሉ ዓለም ወለዓለመ ዓለም።
ለዓለሙ ሁሉ በምትሆን ባንተ ለዘለዓለም ሕያዋን ሆነን እንሆን ዘንድ።
Priest:- Keme bike nihiyew zelekwulu alem wele'aleme alem.
oblation that we may live in Thee for ever.
ይበሉ ሕዝብ፦ ሕዝብ ካህኑን ይቀበል።
People:- Repeat his words!
ይበል ካህን፦ ቡሩክ ስሙ ለእግዚአብሔር። ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር።
የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው። በእግዚአብሔር ስም የሚመጣውም ምስጉን ነው።
Priest:- Buruk simu le'Igzee'abihér.
weburuk zeyimets'i besime Igzee'abihér.
Blessed be the name of the Lord, and blessed be He that cometh in the name of the Lord, and
ይበሉ ሕዝብ፦ ሕዝብ ካህኑን ይቀበል።
People:- Repeat his words!
ይበል ካህን፦ ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ ለይኩን፣ ለይኩን ቡሩከ ለይኩን።
የጌትነቱም ስም የተመሰገነ ይሁን፣ ይሁን፣ ይሁን ምስጉን ይሁን።
Priest:- Weyitbarek sime sibhateehu leyikun leyikun buruke leyikun.
Let the name of His glory be blessed. So be it, so be it, so be it blessed.
ይበሉ ሕዝብ፦ ሕዝብ ካህኑን ይቀበል።
People:- Repeat his words!
ይበል ካህን፦ ፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ።
የመንፈስ ቅዱስ ፀጋን ላከልን።
Priest:- Fenu tsega Menfes Qidus
la'iléne .
Send the grace of the Holy Spirit upon us.
ይበሉ ሕዝብ፦ ሕዝብ ካህኑን ይቀበል።
People:- Repeat his words!
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
የመፈተት ጸሎት
ይበል ካህን፦ የጥበብ አገርዋ ወዴት ነው ማደርያዋስ ወዴት ነው ቦታዋ ወዴት ነው የጐዳናዋስ ፍለጋ በወዴት ተገኘ። ባሕሩን ተሻግሮ በቀይ ወርቅ የገዛት ማነው፤ ከደመናትስ በላይ ወጥቶ ያወረዳት ማነው፤
“Prayer of Fraction”
Priest:- Where is the country of Wisdom, where is its abode, where is its province, and where can the trace of its way be found? Who crossed the sea and bought it for red gold; who ascended above the cloud and brought it down?
ይበል ካህን፦ መዋቲ ጐዳናዋን አያውቃትም፤ በሰውም ዘንድ የለችም። ከሰው ሁሉ ተዘነጋች፤ ከሰማይም አእዋፍ ሁሉ ተሠወረች፤ እርስዋን የገዙ ከእግዚአብሔር ጋራ ተወዳጁ፤ እርስዋን የሚጠሏት ሞትን ይወዳሉ፤ ከፀሐይ ይልቅ ታምራለች፤ በከዋክብትም አኗኗር።
Priest:- Mortal man does not know its way; it is not for mortal man. It is forgotten by all men, and it is hidden from all the birds of heaven. Those who possess it gain friendship with God, and those who hate it love death. It is more beautiful than the sun and all the concourse of stars.
ይበል ካህን፦ እርስዋ ቀዳሚት እንደ መሆንዋ ከብርሃን ጋራ ስትነጻጸር ትገኛለች። በእርጅና ሳለች ሁሉን ታድሳለች በየትውልዱም በጻድቃን ሰውነት ትፋለሳለች። ከከበረ ዕንቍ እርስዋ ትበልጣለች ክብርም ሁሉ መጠንዋ አይደለም፤
Priest:- It is compared with the Light because it was in the beginning. Though it is in the old, it renews all; and in every generation it enters into the souls of the righteous. It is better than rubies; and all honor is not to be compared to it.
ይበል ካህን፦ ምክር ዕውቀት አላት ጽንዕ አእምሮም አላት ነገሥታቱም በእርስዋ ይነግሣሉ፤ ኃያላንም በእርስዋ እውነትን ይጽፋሉ። ደጋጎቹ በእርስዋ ይከብራሉ መኳንንትም በእርስዋ ምድርን ይይዛሉ የሚወዷትን ትወዳለች ሕጓን የሚጠብቁትንም ትጠብቃለች፤ እርስዋንም የሚሹ ባለሟልነትን ያገኛሉ።
Priest:- It has counsel and power, strength and knowledge, by it kings reign, and the powerful decree justice. By it the great are honored, and by it the rulers take hold of the earth. It loves them that love it, it keeps them that keep it, and those that seek it find favor.
ይበል ካህን፦ በእውነት መንገዶች ትመላለሳለች፤ በእውነት ፍለጋም ትመላለሳለች፤ ለሚያውቋት ሰዎች ብዕልን ትሰጣቸው ዘንድ መዝገባቸውንም ተድላን ትመላ ዘንድ። ሁሉን የሚያውቅ እርሱ ያውቃታል። ሁሉን የሚረዳ እርሱ ጐዳናዋን አሳመረ።
Priest:- It walks in the way of righteousness and moves about in the path of righteousness to grant them that know its riches and to fill their treasuries with rejoicing. He who knoweth all knoweth it, and he who understandeth all beautifieth its way,
ይበል ካህን፦ እርሱ ለባለሟሉ ለያዕቆብ ለቅዱሱም ለእስራኤል ሰጠው። እርሱ ለባለሟሉ ለያዕቆብ ለቅዱሱም ለእስራኤል ሰጠው። ከዚህ በኋላ በምድር ላይ ታየች እንደ ሰውም ተመላለሰች። እነሆ ቤትን ሠራች ሰባት አዕማድን አቆመች፤
Priest:- He gave it to His servant Jacob and to His holy Israel. Afterwards it appeared on the earth and walked like man.
Behold she hat builded a house for herself and established seven pillars,
ይበል ካህን፦ የርስዋን እርድ አረደች በማድጋዋም የርስዋን ወይን ጨመረች የርስዋንም ማዕድ አዘጋጀች። ባሮችዋን ላከች፤ በረጅም ስብከት ሰነፍ የሆነ ሰው ወደ እኔ ይምጣ እያለች እውቀት ያነሳቸውንም ትጠራለች
Priest:- she hath killer her beasts and poured her wine in the bowl and furnished her table. She hat sent forth her servants ceaselessly proclaiming and saying: Whoso is simple let him turn in towards me: as for him that wanteth understanding, she saith to him,
ይበል ካህን፦ ኑ የኔን ኅብስት ብሉ የኔንም ወይን ጠጡ ስንፍናንም ትታችሁ ኑሩ እያለች።
ጥበብ ግን መድኃኒታችን ነው በሥጋው መሥዋዕትነት ያዳነን፤ በደሙ ፈሳችነት የተወዳጀን ለመንግሥቱም የመረጠን ለዘላለሙ።
Priest:- Come, eat of my bread, and drink of my wine, forsake the foolish and live.
But wisdom is our Savoir who redeemed us with the sacrifice of His body, and bought us with the sprinkling of His blood, and chose us for His kingdom for ever.
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ
Deacon:- Tseliyu
Pray ye.
ይበሉ ሕዝብ፦ አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ
አባታችን ሆይ! በሰማይ የምትኖር፣ ስምህ ይቀደስ፣ መንገሥትህ ትምጣ፣ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነ
People:- Abune zebesemayat yitqedes simike timtsa'i mengistike weyikun feqadike bekeme besemay kemahu
Our father who art in heaven, hallowed be thy name, Thy kingdom come, Thy will be done on earth as it
ይበሉ ሕዝብ፦ ከማሁ በምድር። ሲሳየነ ዘለለ ዕለትነ ሀበነ ዮም። ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ። ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ
እንዲሁም በምድር ይሁን! የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ፣ በደላችንን ይቅር በለን፣ እኛም
People:- kemahu medir. Seesayene zelele'iletine habene yom. Hidig lene abesane wegégayene keme nihinenee nihidig leze'abese lene. eetabi'ane
is in heave; give us this day our daily bread, and forgive us our trespasses
ይበሉ ሕዝብ፦ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኵሉ እኩይ እስመ ዚኣከ ይእቲ
የበደሉንን ይቅር እንደምንል፣ አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን፣ ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ፣
People:- mensut ala adihinene webalihane imkwulu ikuy isme zee'ake yi'itee
as we forgive them that trespass against us, and lead us not into temptation but deliver us and rescue us from all evil;
ይበሉ ሕዝብ፦ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።
መንግሥት ያንተ ናትና። ኃይል፣ ምስጋና ለዘለዓለም በእውነት።
People:- mengist hayl wesibihat le'alem alem.
for Thine is the kingdom, the power and the glory for ever and ever.
ይበሉ ሕዝብ፦ በከመ ምሕረትከ አምላክነ ወአኮ በከመ አበሳነ። (3 ጊዜ)
ፈጣሪያችን ሆይ እንደቸርነትህ ነው እንደ በደላችን አይደለም። (3 ጊዜ)
People:- Bekeme mihiretike amlakine we'ako bekeme abesane. (3 times )
According to Thy mercy, our God, and not according to our sins. (3 times )
ካህናትና ሕዝቡ እየተቀባበሉ እንዲህ ይበሉ፦
ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔ ዓለም ይቀውሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔ ዓለም።
የመድኃኔ ዓለም አገልጋዮች የሚሆኑ የመላእክት ሠራዊት በመድኃኔ ዓለም ፊት ይቆማሉ።
In succession, they shall all say:
Seraweete mela'ikteehu lemedihané alem yiqewimu qidméhu lemedihane alem;
The hosts of the angels of the Savior of the World, stand before the Savior of the world and encircle the Savior
ካህናትና ሕዝቡ እየተቀባበሉ እንዲህ ይበሉ፦
ወይኬልልዎ ለመድኃኔ ዓለም ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔ ዓለም።
መድኃኔ ዓለምን ያመሰግኑታል የመድኃኔ ዓለም ሥጋውና ደሙ።
In succession, they shall all say:
Weyikéliliwo lemedihané alem sigahu wedemu lemedihané alem.
of the world even the body and blood of the Savior of the world
ካህናትና ሕዝቡ እየተቀባበሉ እንዲህ ይበሉ፦
ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔ ዓለም በአሚነ ዚኣሁ ሐዋርያት ተለዉ ዐሠሮ::
ወደ መድኃኔ ዓለም ፊት እንቅረብ እርሱን በማመን ሐዋርያት ፍለጋውን ተከተሉ
In succession, they shall all say:
Wenibtsah qidme getsu lemedihané alem beameene zee-ahu hawariyat telewu asero.
Let us draw nigh the face of the Savior of the world. In the faith which is of Him the Apostles followed his steps.
ይበል ንፍቅ ዲያቆን፦ አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት።
መኳንንት ደጆችን ክፈቱ።
Asst. Deacon:- Arhiwu hohate mekwanint
Open ye the gates, princes.
ይበል ዲያቆን፦ እለ ትቀውሙ አትሕቱ ርእሰክሙ።
የቆማችሁ ሰዎች ራሳችሁን ዝቅ፣ ዝቅ አድርጉ።
Deacon:- ile tiqewimu atihitu ri'isekimu.
Ye Who are standing, bow your heads.
ይበል ካህን፦ በግዕ ይምጣ በዓይናችን እንድናየው በእጃችንም እንድናርደው በእርሱ ደስ ይለን ዘንድ። ሥጋው ከዚህ ኅብስት ጋራ አንድ ይሁን ደሙም በዚህ ጽዋ ይቀዳ። ከኛ ወገን ላንዱ ይህን ኅብስት በሚበላበት ጊዜ ያለ ደምና ያለ መንፈስ ሥጋን ብቻ የሚበላ
Priest:- Let the Lamb come so that we may see Him with our eyes, slay Him with our hands and rejoice in Him. May His body be joined with this bread, and may His blood be poured into this cup. Let none of us think when He eats of this bread that He eats mere flesh without blood and Spirit.
ይበል ካህን፦ ይህንም ጽዋ በሚጠጣበት ጊዜ ከኛ ወገን ላንዱ ያለ ሥጋና ያለ መንፈስ ደምን ብቻ የሚጠጣ አይምሰለው። ሥጋናም ደም መንፈስም አንድ ናቸው እንጂ መለኮቱ ከትስብእቱ ጋራ አንድ እንደሆነ ለዘላለሙ።
Priest:- Let none of us think when He drinks of this cup that He drinks mere blood without body and Spirit, but one is the body, blood and Spirit as His divinity became one with His humanity, world without end.
ይበል ዲያቆን፦ ስገዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት።
በፍርሃት ሁናችሁ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
Deacon:- Sigedu le'Igzee'abihér befirhat
Worship the Lord with fear.
ይበል ሕዝብ፦ ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሓከ።
አቤቱ በፊትህ ወድቀን እንሰግዳለን እናመሰግንሃለን።
People:- Qidméke igzee'o nisegid
wenisébihake.
Before Thee, Lord, we worship, and Thee do we glorify.
የንስሓ ጸሎት
አቤቱ ዓለሙን ሁሉ የያዝህ ጌታችን እግዚአብሔር አብ የነፍሳችንንና የሥጋችንን፤ የደመ ነፍሳችንን፣ ቍስል የምታድን አንተ ነህ። …
“Prayer of Pentence”
O Lord God, the Father almighty, it is Thou that healest the wounds of our
soul and our body and our spirit, …
ይበል ዲያቆን፦ ነጽር።
ተመልከት።
Deacon:- Netsir.
Give heed
ይበል ካህን፦ ቅድሳት ለቅዱሳን።
ቅድሳት ለቅዱሳን ነው።
Priest:- Qidisat leqidusan.
Holy things for the holy.
ይበል ሕዝብ፦ አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።
ቅዱስ አብ አንድ ነው፤ ቅዱስ ወልድ አንድ ነው፤ መንፈስ ቅዱስም አንድ ነው።
People:- Ahadu Ab qidus, ahadu Weld qidus, ahadu wi'itu Menfes Qidus.
One is the Holy Father, one is the Holy Son, one is the Holy Spirit.
ይበል ካህን፦ እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
Priest:- Igzee'abihér misle kwulikimu.
The Lord be with you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ። (3 ጊዜ)
አቤቱ ክርስቶስ ማረን። (3 ጊዜ)
Priest:- Igzee'o meharene Kiristos. (3 times)
Lord have compassion upon us, O Christ: Lord. (3 times)
ይበሉ ሕዝብ፦ እንደርሱ ሦስቴ ይበሉ።
People:- Repeat his words three times.
ይበል ካህን፦ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ። (5 ጊዜ )
አቤቱ ክርስቶስ ማረን። (5 ጊዜ )
Priest:- Igzee'o meharene Kiristos. (5 times)
Lord have compassion upon us, O Christ: Lord. (5 times)
ይበሉ ሕዝብ፦ እንደርሱ ሦስቴ ይበሉ።
People:- Repeat his words three times.
ይበል ካህን፦ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ። (3 ጊዜ)
አቤቱ ክርስቶስ ማረን። (3 ጊዜ)
Priest:- Igzee'o meharene Kiristos. (3 times)
Lord have compassion upon us, O Christ: Lord. (3 times)
ይበሉ ሕዝብ፦ እንደርሱ ሁለቴ ይበሉ።
People:- Repeat his words two times.
ይበል ዲያቆን፦ እለ ውስተ ንስሓ ሀለውክሙ አትሕቱ ርእሰክሙ።
በንሥሐ ውስጥ ያላችሁ፣ ራሳችሁን ዝቅ፣ ዝቅ አድርጉ።
Deacon:- ile wiste nisiha halewikimu atihitu ri'isekimu.
Ye that are penitent, bow your heads.
ይበል ካህን፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በንስሓ ውስጥ ወዳሉት ወገኖችህ ተመልከት። እንደ ይቅርታህም ብዛት ይቅር በላቸው። እንደ ቸርነትህም ብዛት በደላቸውን አጥፋላቸው፤ ከክፉ ነገርም ሁሉ ጠብቃቸው ሰውራቸውም።
Priest:- Lord our God, look upon Thy people that are penitent, and according
to Thy great mercy have mercy upon them, and according to the multitude of Thy compassion blot out their iniquity, cover them and keep them from all evil.
የቀደመ ሥራቸውን ይቅር ብለህ በሰላም ነፍሳቸውን አድን፤ ከቅድስት ቤተክርስቲያንህ አንድ አድርጋቸው፤ ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው በአንድ ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ
And redeem their souls in peace, forgive their former works. Join them with they holy church; through the grace and compassion of Thy only begotten Son our Lord and our God and our Savior Jesus Christ,
በይቅርታውና በምሕረቱ ከቅድስት ቤተክርስቲያንህ ጨምራቸው። በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ለአንተ ይገባል፤ ከርሱ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ፤ አሜን።
through whom to Thee with him and with the Holy Spirit be glory and dominion, both now and ever and world without end. Amen.
ይበል ዲያቆን፦ ተንሥኡ ለጸሎት
ለጸሎት ተነሡ።
Deacon :- Tensi'u letselot
Stand up for prayer.
ይበሉ ሕዝብ፦ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
People :- Igzee'o tesahalene.
Lord have mercy upon us.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁም።
Priest:- Selam lekwulikimu.
Peace be unto you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበል ካህን፦ ሥጋ ቅዱስ ዘበአማን ዝ ውእቱ …
በእውነት ክቡር የሚሆን የጌታችንና …
Priest:- Siga qidus zebe'aman zi wi'itu
This is the true holy body of our Lord …
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን።
People:- Amen
ይበል ካህን፦ ደም ክቡር ዘበአማን ዝ ውእቱ …
በእውነት አምነው ከርሱ ለሚቀበሉ …
Priest:- Dem kibur zebe'aman zi wi'itu
This is the true precious blood of our Lord …
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን።
People:- Amen
ይበል ካህን፦ እስመ ዝንቱ ውእቱ …
በእውነት የአምላካችን የአማኑኤል …
Priest:- isme zintu wi'itu sigahu wedemu le'Amanu'él amlakine zebe'aman.
For this is the body and blood of Emmanuel our very God.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን።
People:- Amen
ይበል ካህን፦ አአምን አአምን አአምን ወእታመን እስከ ድኃሪት እስትንፋስ ከመ ዝንቱ ውእቱ ሥጋሁ ወደሙ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘነሥአ እምእግዝተ ኵልነ ቅድስት ድንግል በ፪ ምርያም ወረስዮ ፩ደ ምስለ መለኮቱ
አምናለሁ አምናለሁ አምናለሁ እስከ መጨረሻይቱም እስትንፋስ እታመናለሁ በሁለት ወገን ድንግል ክምትሆን ከሁላችን እመቤት ከቅድስት ማርያም የነሳው የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችንም የኢየሱስ ክርስቶስ ስጋው ደሙ
Priest:- I believe,I believe, I believe and I confess, unto my latest breath, that this is the body and blood of our lord and our God and our Savior Jesus Christ which he took from the lady of us all, the holy mary of two fold verginity.
ይበል ካህን፦ ዘእንበለ ቱስሕት ወኢትድምርት ዘእንበለ ፍልጠት ወኢውላጤ ወኮነ ሰማዕተ በስምዕ ሠናይ በመዋዕለ ጲላጦስ ጰንጤናዊ ወመጠዎ በእንቲአነ ወበእንተ ሕይወተ ኵልነ።
ይህ እንደሆነ ያለመቀላቀልና ያለትድምርት ያለመለወጥና ያለመለየት ከመለኮቱ ጋራ አንድ ያደረገው በጴንጤናዊ ጲላጦስም ዘመን ባማረ ምስክርነት ምስክር የሆነ ሰለእኛና ስለሁላችንም ሕይወት አሳልፎ የሰጠው።
Priest:- And made it one with his godhead without mixture or confusion without diviion or alteration ;and he verily confessed with a good testimony in the days of Pontis Pilate, this body he gave up for our sakes and for the life of us all.
ሕዝብ ፦አሜን
People:- amen
ይበል ካህን፦ አአምን አአምን አአምን ወእታመን ከመ ኢተፈልጠ መለኮቱ እምትስብትእቱ ኢአሐተ ሰዓተ ወኢከመ ቅጽበተ ዓይን አላ መጠወ በእንቲአነ ለሕይወት ወለመድኃኒት ወለሥርየተ ኃጢአት ለእለ ይትሜጥው እምኔሁ በአሚን።
አምናለሁ አምናለሁ አምናለሁ መለኮቱ ከሰውነቱ አንዲት ሰዓት እንኳን እንደ ዓይን ቅጽበትስ ስንኳ እንዳልተለየም እታመናለሁ። ስለኛ ሰጠው እንጅ ለሕይወትና ለመድኃኒት ለኃጥያትም ማስረሥረያ ሊሆን አምነው ለሚቅበሉት ሰዎች ስለኛ አሳልፎ ሰጠው እንጅ።
Priest:- I believe,I believe, I believe and I confess that his godhead was not separated his manhood, not for an hour nor for the twinkling of an eye, but he gaveit up for our sakes for life and for salvation of sin unto them that partake of it in faith.
ሕዝብ ፦አሜን
People:- amen
ይበል ካህን፦ አአምን አአምን አአምን ወእታመን ከመ ዝንቱ ዉዕቱ ሥጋሁ ወደሙ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
አምናለሁ አምናለሁ አምናለሁ የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋው ደሙ ይህ እንደሆነ እታመናለሁ።
Priest:- I believe,I believe, I believe and I confess that this is the body and blood of our Lord and our God and our savior Jesus Christ.
ይበል ካህን፦ ዝውእቱ ዘሎቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወስግደት ምስለ አቡሁ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስ ቅዱስ ማህየዊ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን።
ክብርና ምስጋና ስግደትም ቸር ከሚሆን ከሰማያዊ አባቱ ጋራ ማሕየዊ ከሚሆን ከመንፈ ቅዱስ ጋራ የሚገባው ይህ ነው። ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።
Priest:- and that to him are rightly due honour and glory and adoration with his kind heavenly Father and the Holy Sprit, the life giver both now and ever and world without end. Amen.
ሕዝብ ፦አሜን
People:- amen
ይበል ካህን፦ ሰላም ለኪ፥ እንዘንሰግድ ንብለኪ፥ ማርያም እምነ ናስተበቍዓኪ፥
ሰላም ላንቺ ይሁን፥ እያልን እንሰግዳለን፤ እናታችን ማርያም እንማልድሻለን።
Priest:- Selam lekee inzenisegid nibleki Mariam imine nastabeqwu'akee.
Peace be unto you, while bowing unto you, Our mother Mary, we ask for your prayers.
ይበሉ ሕዝብ፦ እምአርዌ ነዓዊ ተማኅፀነ ብኪ፥ በእንተ ሐና እምኪ፥ ወኢያቄም አቡኪ፥ ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ።
ከአዳኝ አውሬ አደራ ጠብቂን። ስለእናትሽ ሐና ስለአባትሽም ኢያቄም አንድነታችንን፥ ድንግል ዛሬ ባርኪልን።
People:- im'arwé ne'awee temhatsene bikee be'inte Hanna imikee we'eeyaqém abukee mahiberene yom dingil barikee.
Protect us from hunting animals. For the sake of thy mother, Hanna, and thy father, Iyakem, O Virgin bless this day
ይበል ንፍቅ ካህን፦ ናዛዚትነ እምኃዘን ወኃይለ ውርዙትነ እምርስአን በማኅጸንኪ ተጸውረ ብሉየ መዋዕል ሕፃን፥
መንፈስ ቅዱስ ይውረድ ባለ ጊዜ ካህኑ፤ በዚህች በከበረች በቤተ መቅደሱ።
Asst. Priest:- Nazazitne emhazen wehaile wurzutne emeresan bemahtsenki tetsewre bluye mawaeel hetsan.
ይበሉ ሕዝብ፦ ኦ ማርያም ተስፋ ለቅቡጻን በጊዜ ጸሎት ወእጣን ወበጊዜ ቅዱስ ቁርባን ለናዝዞትነንዒ ውስተ ዝመካን።
People:- O maryam tesefa leqbutsan begizee tselot weetan webegizee qdus qurban lenazzotnenei wste zmekan.
ይበል ንፍቅ ካህን፦ ወላዲተ አምላክ ማርያም እንበለ ሰብሳብ ወሩካቤ በይነ ዘአቅረቡኩ ለኪ ንስቲተ ቃለ ይባቤ፥
Asst. Priest:- Woladite amlak maryam enbele sebsab werukabee beyine zeaqrebuku leki nstite qale yibabe.
ይበሉ ሕዝብ፦ ፈትቲ እሙ በረከተ አፉኪ መዓዛ ከርቤ ለናዳይ ብእሲ ወለዘረከቦ ምንዳቤ ኅብስተከ ፈትት ኢሳይያስ ይቤ።
People:- fetteti emu berekete afuki meaaza kerebee leneday beesi weleerekebo mndabee hebsteke fettet eisayyas yibee.
ይበል ንፍቅ ካህን፦ ይወርድ መንፈስ ቅዱስ በላዕለ ኅብስቱ ወወይኑ፥ ሶበ ይብል ካህን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ፈኑ፥
መንፈስ ቅዱስ ይውረድ ባለ ጊዜ ካህኑ፤ በዚህች በከበረች በቤተ መቅደሱ።
Asst. Priest:- Yiwerid Menfes Qidus bela'ile hibistu weweynu sobe yibl kahin tsega Menfes Qidus fenu.
As the priest says let the Holy Spirit descend, on this revered Holy of Holies
ይበሉ ሕዝብ፦ ማዕከለ ዛቲ ቅድስት ቤተክርስቲያኑ፥ ይዌልጦሙ በቅጽበት አባላተ ክርስቶስ ይኩኑ፤ በኃይለ ጥበቡ መንክር ወዕፁብ ኪኑ።
በኅብስቱና ወይኑ ይወርዳል መንፈሱ፥ ወደ ሥጋውና ደሙ በቅጽበት የተለየ ነፍሱ፤ ይለውጣቸዋል በጥበቡ እርሱ።
People:- Ma'ikele zatee qidist béte kiristiyanu yiwélitomu beqiÍbet abalate kiristos yikunu behayle tibebu menkir we'itsub keenu.
The Holy Spirit will descend upon the bread and wine and towards the Flesh and Blood, His special Spirit will transform them in an instant with His wisdom.
ይበል ካህን፦ ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት፥ እለ አዕረፍክሙ በሃይማኖት።
ሰላም ለእናንተ ይሁን፥ ጻድቃን፥ ሰማዕታት፥ በሞት ያረፋችሁ ስለ ሃይማኖት
Priest:- Selam lekimu tadqan wesema'it ile a'irefikimu behaymanot.
Peace be unto you, blessed and martyrs, who have died for the faith.
ይበሉ ሕዝብ፦ መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት፤ ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኵሉ ሰዓት፤ እንበለ ንሥሐ ኪያነ ኢይንሥአ ሞት።
ዓለምን ድል የነሣችሁ በብዙ ትዕግሥት፥ በፈጣሪ ፊት ቆማችሁ ለምኑልን ቀንና ሌሊት፥ ንሥሐ ሳንገባ እንዳይወስደን ሞት።
People:- Mewa'iyane alem antimu bebizuh ti'igist se'alu qidme fetaree bekwulu se'at inbele nisiha keeyane eeyins'a mot.
Ye who have conquered the world by patience, pray for us day and night standing in front of our Creator, so that death will not take us before we have repented.
ይበል ንፍቅ ካህን፦ ሰላም ለክሙ ጻድቃን ዛቲ ዕለት ኵልክሙ፤ ዕድ ወአንስት በበአስማቲክሙ።
ሰላም ለእናንተ ይሁን ጻድቃን በዚህች ቀን ሁላችሁ፤ ወንዶችና ሴቶች በየስማችሁ።
Asst. Priest:- Selam lekimu Íadqan zatee ilet kwulikimu id we'an'ist bebe'asmateekimu.
Peace be unto you, all those blessed on this day, men and women according to your name.
ይበሉ ሕዝብ፦ ቅዱሳነ ሰማይ ወምድር ማኅበረ ሥላሴ አንትሙ፤ ዝክሩነ በጸሎትክሙ፤ በእንተ ማርያም እሙ፤ ተማኅፀነ ለክርስቶስ በሥጋሁ በደሙ።
በሰማይና በምድር የከበራችሁ፤ የሥላሴ ወገኖች ናችሁ፤ ስለ ማርያም ብላችሁ፥ አስቡን በጸሎታችሁ በክርስቶስ በሥጋና ደሙ ተማጠንባችሁ።
People:- Qidusane semay wemidr mahibere silasé antimu zikirune betselotikimu be'inte Mariam imu temahitsene leKiristos besigahu wedemu.
Ye that are glorified in heaven and on earth, friends of the Holy Trinity; remember us in your prayers for the sake of Mary and for the sake of Christ's flesh and blood, we beseech you.
ይበል ንፍቅ ካህን፦ እግዚኦ ኵነኔከ ሀባ ለሀገር ጽድቀከኒ ለቤተ ክርስቲያን።
Asst. Priest:- egzioo kuneneke haba lehager tsedqekeni lebeete krstiyan.
ይበሉ ሕዝብ፦ አግርር ፀራ ታሕተ እገሪሃ ዕቀብ ሕዝባ ወሰራዊታ ለሀገሪትነ ኢትዮጵያ።
People:- Agrere tsera tahte egeriha eeqeb hezba weserawita lehageritne ityopeyaa..
ይበል ካህን፦ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ። (3 ጊዜ)
አቤቱ ክርስቶስ ማረን። (3 ጊዜ)
Priest:- Igzee'o meharene Kiristos. (3 times)
Lord have compassion upon us, O Christ: Lord. (3 times)
ይበሉ ሕዝብ፦ እንደርሱ ሦስቴ ይበሉ።
People:- Repeat his words three times.
ይበል ካህን፦ በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ።
ስለማርያም ክርስቶስ ማረን። (3 ጊዜ)
Priest:- Be'inteMariam mahirene Kiristos
For the sake of Mary, have compassion upon us, O Christ Lord.. (3 times )
ይበሉ ሕዝብ፦ እንደርሱ ሦስቴ ይበሉ።
People:- Repeat his words three times.
ይበል ካህን፦ ሰአሊ ለነ ማርያም፥ ምሕረተ ወልድኪ ሣህሎ ይከፍለነ።
ማርያም ሆይ! የልጅሽን ምሕረት ለምኝልን፤ ይቅርታውን ያደርግልን ዘንድ።
Priest:- Se'alee lene Mariam mihirete weldikee sahilu yikefilene.
O Mary, pray for our mercy, so that He may forgive us.
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ በእንቲአነ ወበእንተ ኵሎሙ ክርስቲያን እለ ይቤሉነ ግበሩ ተዝካሮሙ በሰላም፤ ወበፍቅረ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብሑ ወዘምሩ።
ስለእኛና አስቡን ስላሉን ስለ ክርስቲያኖች ሁሉ ጸልዩ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር አመስግኑ ዘምሩ።
Deacon :- Pray ye for us and for all Christians who bade us to make mention of them. Praise ye and sing in the peace and love of Jesus Christ.
ሁሉም በአንድነት
ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ሥሉስ ዘኢይትነገር፥ ሀበኒ ከመ እንሣእ ለሕይወት ዘንተ ሥጋ ወደመ ዘእንበለ ኵነኔ።
የማይነገር ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ሦስት የምትሆን ይህን ሥጋና ደም ሕይወት፤ ሊሆኝ ሳይፈረድብኝ፥
Qidus qidus qidus silus ze'eeyitneger habenee keme insa'I lehiywet zente siga wedeme ze'inbele kwunené.
Holy Holy Holy Trinity ineffable, grant me to receive this body and this blood for life and not for condemnation.
ሀበነ እግበር ፍሬ ዘያሠምረከ ከመ አስተርኢ በስብሓቲከ ወእሕየው ለከ እንዘ እገብር ዘዚኣከ ፈቃደ።
እቀበል ዘንድ ስጠኝ። በጌትነትህ እንድገለጽ ደስ የሚያሰኝህን ፍሬ እሠራ ዘንድ ስጠኝ፤የአንተንም ፈቃድ እየሠራሁ እኖርልህ ዘንድ ስጠኝ።
Habenee igber firé zeyasemireke keme asteri'ee besebahteeke we'ihiyew leke inze igebir zezee'ake feqade.
Grant me to bring forth fruit that shall be well pleasing unto Thee, to the end that I may appear in Thy glory and live unto Thee doing Thy will.
በተአምኖ እጼውዐከ አብ ወእጼውዕ መንግሥተከ ይትቀደስ እግዚኦ ስምከ በላዕሌነ።
በማመን አባት ብዬ እጠራሃለሁ፤ መንግሥትህንም እጠራለሁ፤ አቤቱ ስምህ በኛ ላይ ይመስገን፤
Bete'amino itsewi'ake Ab we'itsew'i mengistike yitqedes igzee'o simike bela'iléne
In faith I call upon Thee, Father, and call upon Thy Kingdom; hallowed, Lord, be thy name upon us,
እስመ ኃያል አንተ እኵት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም።
ምስጉን ክቡር የምትሆን ኃያል አንተ ነህና፤ ለአንተ ክብር ይገባሃል ለዘላለሙ። (በመደጋገም)
isme hayal ante ikut wesibuh weleke sibhat le'alem alem. (Repeatedly)
for mighty art Thou, praised and glorious, and to Thee be glory, world without end.
ይበል ዲያቆን፦ ነአኵቶ ለእግዚአብሔር ቅድሳቶ ነሢኣነ፤ ከመ ለሕይወተ ነፍስ ይኩነነ ፈውስ
ሥጋውን ደሙን ተቀብለን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን። ለነፍሳችን አኗኗር መድኃኒት
Deacon:- Ne'akwuto le'igzee'abihér qidsato nesee'ane keme lehiywete nefs yikunene fews
We thank God for that we have partaken of His Holy things; we pray and trust that which we have
ይበል ዲያቆን፦ ዘተመጦነ ንስእል ወንትመሐፀን እንዘ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር አምላክነ።
ይሆን ዘንድ የተቀበልነው እኛ፤ ፈጣሪያችን እግዚአብሔርን እያመሰገን እንለምናለን፤ አደራም እንላለን።
Deacon:- zetemetone nisi'il wenitmehatsen inze nisebiho le'Igzee'abihér amlakine.
received may be healing for the life of the soul while we glorify the Lord our God.
ይበል ካህን፦ አሌዕለከ ንጉሥየ ወአምላኪየ ወእባርክ ለስምከ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።
ንጉሤና ፈጣሪዬ ሆይ! ከፍ፣ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ቅዱስ ስምህንም ለዘለዓለም አመሰግናለሁ።
Priest: A'ilé'ileke nigusiye we'amlakeeye we'ibarik lesimike le'alem wele'alem alem.
I will extol Thee, my King and my God, and I will bless Thy name for ever and ever.
ይበሉ ሕዝብ፦ አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
አባታችን ሆይ! በሰማይ የምትኖር አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
People:- Abune zebesemayat eetabi'ane igzee'o wiste mensut.
Our Father who art in heaven, lead us not, Lord, into temptation
ይበል ዲያቆን፦ ተመጦነ እምሥጋሁ ቅዱስ ወእምደሙ ክቡር ለክርስቶስ።
ከክርስቶስ ከቅዱስ ሥጋው ከክቡር ደሙም ተቀበልን።
Deacon:- Temetone imsigahu qidus
we'imdemu kibur leKiristos.
We have received of the holy body and the precious blood of Christ.
ይበል ካህን፦ ኵሎ አሚረ እባርከከ ወእሴብሕ ለስምከ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።
ዘወትር አከብርሃለሁ፤ ቅዱስ ስምህንም ለዘለዓለሙ አመሰግናለሁ።
Priest:- Kwulo ameere ibarikeke we'isebih lesimike le'alem wele'alem.
Every day will I bless Thee, and I will praise Thy name for ever and ever
ይበሉ ሕዝብ፦ አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
አባታችን ሆይ! በሰማይ የምትኖር አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
People:- Abune zebesemayat eetabi'ane igzee'o wiste mensut.
Our Father who art in heaven, lead us not, Lord, into temptation
ይበል ዲያቆን፦ ወናእኵቶ ይደልወነ ከመ ንሳተፍ ምስጢረ ክብርተ ወቅድስተ።
ክብርት ቅድስት የምትሆን ምስጢርን እንሳተፍ ዘንድ ስለበቃን ልናመሰግነው ይገባናል።
Deacon:- Wena'ikwuto yideliwene keme nisatef misteere kibirte weqidiste
And let us give thanks unto Him that maketh us meet to communicate in the precious and holy mystery.
ይበል ካህን፦ ስብሐተ እግዚአብሔር ይነግር አፉየ ወኵሉ ዘሥጋ ይባርክ ለስሙ ቅዱስ፥ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።
አንደበቴ የእግዚአብሔርን ምስጋና ይናገራል የሥጋም ፍጥረት ሁሉ ቅዱስ ስሙን ለዘለዓለም ያመሰግናል።
Priest:- Sibhat le'Igzee'abihér yinegir afuye wekwulu zesiga yibarik lesimu qidus le'alem wealem alem.
My mouth shall speak the praise of the Lord, and let all flesh bless His Holy name for ever and ever.
ይበሉ ሕዝብ፦ አቡነ ዘበሰማያት ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት።
አባታችን ሆይ! በሰማይ የምትኖር አቤቱ ወደ ፈተና አታግባን።
People:- Abune zebesemayat eetabi'ane igzee'o wiste mensut.
Our Father who art in heaven, lead us not, Lord, into temptation
ኅዳፌ ነፍስ
ይበል ካህን፦ ዳግመኛም ሁሉን የሚይዝ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔርን እንማልዳለን፤ ልመናችንን አልናቀምና አልተቈጣምና፤ ይቅርታውንም ከኛ አላራቀምና፤ አምላካችን እግዚአብሔር ይቅር ባይ ስለ ሆነ።
Pilot of the Soul
Priest:- Again we supplicate the almighty God, Father of our Lord and our Savior Jesus Christ, because He did neither disdain nor refuse our supplication, nor did He remove His mercy from us, because the Lord our God is merciful.
ይበል ዲያቆን፦ ጸልዩ
Deacon:- Tseliyu
Pray ye.
ይበል ካህን፦ አዎን አቤቱ የሁሉ አምላክ ነህ።
አዎን አቤቱ የሁሉ ንጉሥ ነህ።
አዎን አቤቱ ሁሉን የያዝህ ነህ።
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትገዛ ነህ።
Priest:- Yea Lord, Thou art the God of all.
Yea Lord, Thou art the King of all.
Yea Lord, Thou art the Almighty.
Yea Lord, Thou art the Governor of all.
ይበል ካህን፦ አዎን አቤቱ ሁሉን የምታድን ነህ።
አዎን አቤቱ በእውነት የሁሉ ገዢ ነህ።
አዎን አቤቱ የሁሉ መድኃኒት ነህ።
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትጠብቅ ነህ።
አዎን አቤቱ ሁሉን የምትመግብ ነህ።
Priest:-Yea Lord, Thou art the Saviour of all.
Yea Lord, Thou art the Judge of all.
Yea Lord, Thou art the Life giver of all.
Yea Lord, Thou art the Keeper of all.
Yea Lord Thou art the Nourisher of all.
ይበል ካህን፦ የልጅህን ሥጋ ከእኛ ሥጋ ጋራ አንድ እንዳደረግህ ያንተን መሢሕ ደምም ከእኛ ጋራ አንድ እንዳደረግህ እንዲሁ አንተን መፍራትን በልቡናችን፤ በጎ አምልኮትህንም በሕሊናችን ጨምር። የሥጋውያን የምንሆን እኛ ግን የሥጋን ሕግ እናስባለን፤ የሥጋንም ሥራ እንሠራለን፤ በሥጋ መንገድም እንሄዳለን።
Priest:- As Thou didst join the body of Thy Son with our body, and Thou didst mix the blood of Thy Messiah with our blood, so put Thy fear in our heart and the beauty of Thy worship in our mind. We who are carnal, mind the things of the flesh and do the works of the flesh and walk in the way of the flesh.
ይበል ካህን፦ አንተ ግን የመንፈስን ሥራ አስተምረን፤ የመንፈስንም ሕግ አስረዳን፤ የምንፈስንም መንገድ ምራን። እኛን ኃጥአንን ብትምረን ያን ጊዜ መሐሪ ትባላለህና። ጻድቃንን ግን ከሥራቸው የተነሣ ትምራቸውለህ፤ እንደ ጽድቃቸውም ትሰጣቸዋለህ።
Priest:- But do Thou teach us the work of the Spirit and make us understand the law of the Spirit and lead us to the way of the Spirit. Because if Thou pity us, we sinners, then Thou wilt be called compassionate. Thou pitiest the righteous because of their works and dost recompense them according to their righteousness.
ይበል ካህን፦ የቀደመ በደላችንን አታስብብን፤ አቤቱ ይቅርታህ ፈጥኖ ይደረግልን። ወደ አንተ እንጮሃለን፤ ወደ አንተ እናለቅሳለን፤ ወደ አንተ እንማለላለን ለዘላለሙ።
Priest:- Remember not against us former iniquities: let Thy tender mercies, O God, speedily prevent us. Towards Thee we cry, towards Thee we weep, Thee we entreat, world without end.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን
People:- Amen
ይበል ዲያቆን፦ አጽንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ በእደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርክሙ።
በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ፣ ዝቅ አድርጉ አገልጋዩ በሚሆን በካህኑ እጅ ይባርካችሁ ዘንድ።
Deacon:- Atsninu ar'isteekimu qidme igzee'abihér amlakine be'ide gebru kahin keme yibarikimu.
Bow your heads in front of the Lord our God, that He may bless you at the hand of His servant the priest.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን ይባርከነ ወይሰሃለነ
አሜን ይባርከን፤ ይቅርም ይበለን።
People:- Amen Igziabher yibarikene weyisehalene
Amen, may He bless us at the hand of His servant the priest.
ይበል ካህን፦ ኦ እግዚኦ አድኅን ሕዝበከ ወባርክ ርስተከ …
አቤቱ ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ። አቤቱ …
Priest:- O igzio adihin hizibike webarik risteke …
O Lord, save Thy people and bless Thy inheritance …
ይበል ካህን፦ እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋር ይሁን።
Priest:- Igzee'abihér misle kwulikimu.
The Lord be with you all.
ይበሉ ሕዝብ፦ ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People:- Misle menfesike.
And with Thy spirit.
ይበሉ ሕዝብ፦ አሜን እግዚአብሔር ይባርከነ ለአግብርቲሁ በሰላም ሥርየተ ይኩነነ ዘተመጦነ ሥጋከ ወደመከ አብሓነ በመንፈስ ንኪድ ኵሎ
በእውነት እግዚአብሔር እኛን አገልጋዮቹን በሰላም ይባርከን። የተቀበልነው ሥጋህና ደምህ ለሥርየት ይሁነን። የጠላትን ኃይል ሁሉ በመንፈስ
People:- Amén Igzee'abihér yibarikene
le'agibiriteehu beselam siriyete yikunene zetemetone sigake wedemike abhane
Amen. May God bless us, His servants, in peace. Remission be unto us who have received Thy body and
ኃይሎ ለጸላዒ። በረከተ እዴከ ቅድስት እንተ ምልዕተ ምሕረት ኪያሃ ንሰፎ ኵልነ እምኵሉ ምግባረ እኩይ አግኅሠነ ወውስተ ኵሉ ምግባረ ሠናየ ደምረነ።
እንረግጥ ዘንድ አሠልጥነን። ምሕረትን የተመላች ክብርት የምትሆን የእጅህን በረከት ሁላችን ተስፋ እናደርጋለን፤ ከክፉ ሥራ ሁሉ አርቀን፤ በበጎውም
bemenfes nikeed kwulo haylo letsela'ee. Berekete idéke qidist inte mil'ite mihiret keeyaha niséfo kwuline imkwulu migbare
Thy blood. Enable us by the Spirit to tread upon all the power of the enemy. We all hope for the blessing of Thy holy
ብሩክ ዘወሀበነ ሥጋሁ ቅዱስ ወደሞ ክቡረ፤ ጸጋ ነሣእነ ወሕይወተ ረከብነ በኃይለ መስቀሉ
ሥራ ሁሉ አንድ አድርገን። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙንም የሰጠን ቡሩክ ነው። ጸጋን ተቀበልን
senay demirene. Buruk zewehabene sigahu qidus wedemo kibre tsega nesa'ine wehiywete rekebne behayle
hand which is full of mercy. From all evil works keep us apart, and in all good works unite us. Blessed be He that hath given us His holy body and His precious blood. We have received grace and we
ለኢየሱስ ክርስቶስ። ኪያከ እግዚኦ ነአኵት ነሢአነ ጸጋ ዘእመንፈስ ቅዱስ።
ደኅንነትንም በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ኃይል አገኘን። አቤቱ ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ ጸጋን ተቀበለን፤ አንተን እናመሰግንሃለን።
mesqelu le'Eeyesus Kiristos. Keeyake igzee'o ne'akwut nesee'ane tsega ze'iMenfes Qidus.
have found life by the power of the cross of Jesus Christ. Unto Thee, Lord, do we give thanks, for that we have received grace from the Holy Spirit.
ይበል ዲያቆን፦ እትዉ በሰላም።
በሰላም ወደ በታችሁ ግቡ።
Deacon:- itiwoo beselam.
Go ye in peace.