ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
፩፤ ይ.ዲ. ጸልዩ በእንተ አበዊነ ጳጳሳት ወአበዊነ ኤጲስቆጶሳት ወአበዊነ ቀሳውስት ወአኀዊነ ዲያቆናት ጸልዩ ውሉደ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን በእንተ መሃይምናን ወመሃይምናት።
ስለ አባቶቻችን ጳጳሳትና ስለ አባቶቻችን ኤጲስቆጶሳት ስለ አባቶቻችን ቀሳውስትና ስለ ወንድሞቻችን ዲያቆናት ጸልዩ። የዚች ቤተ ክርስቲያን ልጆች ሆይ ስለ መሃይምናንና ስለ መሃይምናት ጸልዩ
1. Deacon : Pray for our fathers the archbishops and bishops, our fathers the priests, our brothers the deacons. Pray, O ye children of this church, for the faithful men and women.
ወካዕበ ጸልዩ በእንተ ደናግል ወመነኮሳት በእንተ ደቂቅ ወሕፃናት ወበእንተ አእሩግ ወወራዙት ወመዓስባት ቁሙ ሠናየ ቁሙ ከመ ሰላሙ ለእግዚአብሔር የሀሉ ምስሌክሙ ምስለ ኵልክሙ።
ዳግመኛም ስለ ደናግልና ስለ ፈቶች ስለ ሽማግሎችና ስለ ሕፃናቱ ስለ ልጆችና ስለ ጐልማሶች ጸልዩ። የእግዚአብሔር ፍቅሩ ከናንተ ጋራ ይኖር ዘንድ ቁሙ በበጎ ቁሙ።
Again pray for the virgins and the husbandless, for the aged and infants, for children and adults. Stand up well, stand up, that the peace of God may be with you.
፪፤ አኰቴተ ቊርባን ዘጎርጎርዮስ ኤጲስ ቆጶስ ዘኑሲስ እኁሁ ለባስልዮስ ጸሎቱ ወበረከቱ የሀሉ ምስለ ኵልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን።
የኑሲስ ኤጲስ ቆጶስ የባስልዮስ ወንድም የጎርጎርዮስ የቊርባን ምስጋና ይህ ነው። ጸሎቱና በረከቱ ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ፤ አሜን።
2. Anaphora of Gregory, Bishop of Nyssa and brother of Basil : may his prayer and blessing be with us all unto the ages of ages. Amen.
፫፤ ይ.ካ. እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።
3. Priest : The Lord be with all of you.
ይ.ሕ. ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People : And with your spirit.
ይ.ካ. አእኵትዎ ለአምላክነ።
አምላካችንን አመስግኑት።
Priest : Give ye thanks unto our God.
ይ.ሕ. ርቱዕ ይደሉ።
እውነት ነው ይገባል።
People : It is right, it is just.
ይ.ካ. አልዕሉ አልባቢክሙ።
ልቡናችሁን ከፍ ከፍ አድርጉ።
Priest : Lift up your hearts.
ይ.ሕ. ብነ ኀበ እግዚአብሔር አምላክነ።
በአምላካችን በእግዚአብሔር ዘንድ አለን።
People : We have lifted them up unto the
Lord our God.
፬፤ ይ.ካ. ነአኵቶ ለገባሬ ሠናያት ላዕሌነ እግዚአብሔር መሐሪ አቡሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
ለእኛ በጎ ሥራን የሚሠራ ይቅር ባይ የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔርን እናመሰግነዋለን።
4. Priest : We give thanks unto our Benefactor, the merciful God, Father of our Lord, God, and Saviour Jesus Christ.
፭፤ ነአኵተከ አምላክ ቅዱስ አምላክ መሐሪ አምላክ መስተሣህል ርሑቀ መዓት ወብዙኀ ምሕረት ወጻድቅ አንተ ውእቱ አምላክነ ዘእንበለ ጥንት ወመድኃኒነ ዘእንበለ ተፍጻሜት።
ቅዱስ አምላክ፤ መሐሪ አምላክ፤ ይቅር ባይ አምላክ፤ መዓትህ የራቀ ምሕረትህ የበዛ፤ እውነተኛ ጥንት የሌለህ አምላካችን፤ ፍጻሜ የሌለህ መድኃኒታችን አንተ ነህ።
5. We give thanks unto Thee, holy God, compassionate God and merciful God, slow to anger, plenteous in mercy, righteous. Thou art our God, without beginning, and our Saviour without end.
፮፤ የማነ እዴሁ እሳት ወሥልጣነ ቃሉ ዘኢይትነሠት አልቦ ኍልቊ ለኑኀ ዘመኑ ወአልቦ ወሰን ለራኅበ ምኵናኑ።
ቀኝ እጁ እሳት ነው። የቃሉም ሥልጣን የማይፈርስ ነው። ለዘመኑ ብዛት (ርዝመት) ቊጥር የለውም፤ ለግዘቱም ስፋት ወሰን የለውም።
6. His right hand is fire and the authority of His word is indestructible, the length of His years is uncountable, and there are no bounds to the range of His government.
፯፤ አልቦ አድልዎ በኀቤሁ ወኢነሢአ ገጽ ለአውሥኦተ ቃሉ፤ ኢየኀፍሮ ለባዕል እንበይነ ብዕሉ ወኢይሰድዶ ለነዳይ መንገለ ገጽ ዘአፍኣ።
በርሱ ዘንድ አድልዎ የለም፤ ለቃሉም ምላሽ፤ ፊት መንሣት የለበትም። ባለጸጋውን ስለ ባለጸግነቱ አያፍረውም ድሀውንም ወደ ውጪ አስወጥቶ አይሰደውም።
7. He has no respect of persons, neither does He turn aside His face from giving an answer; He does not reverence the rich because of his riches, He does not send the poor away because of his poverty.
፰፤ እስመ አንተ ውእቱ ረኣዬ ኅቡኣት እምትካት ወነጻሬ ነገር እስከ እስትንፋስ ደኃሪት።
ከጥንት ጀምሮ የተሠወረውን የምታይ እስከ መጨረሻዪቱ እስትንፋስም ነገሩን የምትመለከት አንተ ነህና።
8. Because Thou sees the hidden from the beginning, looks upon everything until the last breath.
፱፤ ይ.ዲ. ንነጽር ሥነ ስብሐቲሁ ለአምላክነ።
የአምላካችንን የጌትነቱን ብዛት እናስተውል።
9. Deacon : Let us look at the beauty of our God’s glory.
፲፤ ይ.ካ. ዝ ውእቱ ዘገብረ ሰማየ ወዝ ውእቱ ዘሣረረ ምድረ፤ አልቦ ዕመቅ ለመለኮቱ አልቦ ላዕል ወአልቦ ታሕት ወአልቦ ኑኅ ወግድም፤ አልቦ የማን ወአልቦ ፀጋም ወአልቦ ማእከል አላ ምሉዕ ውእቱ ውስተ ኵሉ አጽናፈ ዓለም።
ሰማይን የፈጠረ ይህ ነው። ምድርንም የፈጠረ ይህ ነው። ለመለኮቱ ጥንት (መሠረት) የለውም፤ ላይ የለውም፤ ታችም የለውም፤ ርዝመት የለውም ቁመት የለውም። ቀኝ የለውም ግራም የለውም፤ መካከል የለውም በዓለም ዳርቻ ሁሉ የመላ ነው እንጂ።
10. Priest : This is He who made heaven, and this is He who built the earth. His divinity is unfathomable, has neither height nor depth, neither length nor width, neither right nor left, no centre, but it fills all the ends of the world.
፲፩፤ ሥውር ውእቱ እምሕሊና ኵሎሙ መላእክት አልቦ ዘየአምሮ ለህላዌሁ ወአልቦ ዘይኌልቆ ዘለሐኮ በእዴሁ።
ከመላእክት ሁሉ ሕሊና የተሠወረ ነው፤ ባሕርዩን የሚያውቀው የለም፤ በእጁ የፈጠረውንም የሚቈጥረው የለም።
11. He is hidden from the minds of all the angels, none can know his nature and none can count that which he formed with his hand.
፲፪፤ ይ.ዲ. እለ ትነብሩ ተንሥኡ።
የተቀመጣችሁ ተነሡ።
12. Deacon : Ye that are sitting, stand up.
፲፫፤ ይ.ካ. መጽአ እመልዕልተ ሰማይ ጠፈሩ ወተሠገወ ኀቤነ ወተሰብአ ኀበ ዘቀዳሚ ተግባሩ፤ ወረደ እንዘ ኢየዐርቅ በተድላ መለኮት ወአሕየወነ በሞተ ዚአሁ።
ከጠፈሩ ከሰማይ ላይ መጣ፤ ከእኛም ዘንድ ሰው ሆነ ከቀደመ ፍጥረቱ ዘንድ ሰው ሆነ፤ ሳይለይ በመለኮት ተድላ ወረደ፤ በእርሱም ሞት አዳነን።
13. Priest : He came from above the heavens, His firmament, was incarnated, taking our nature, and was made man, taking the body of His first creature, he descended without being emptied of the joy of His divinity, and has quickened us through His death.
፲፬፤ ይ.ዲ. ውስተ ጽባሕ ነጽሩ።
ወደ ምሥራቅ ተመልከቱ።
14. Deacon : Look to the east.
፲፭፤ ይ.ካ. ናንቀዐዱ ኀቤከ አዕይንተ አልባቢነ ወናደንን ለከ ቀፈተ ልብነ ግናይ ለከ ስብሐት ለመንግሥትከ ወናቄርብ ለከ ዕጣነ ንጹሐ ምስለ ሊቃነ መላእክቲከ።
ዓይነ ልቡናችንን ወደ አንተ እናንጋጥጣለን፤ ክሣደ ልቡናችንን እናዘነብልልሃለን። ላንተ መገዛት ይገባል፤ ለመንግሥትህም ምስጋና ይገባል፤ ከሊቃነ መላእክትህም ጋራ ንጹሕ ዕጣንን እናቀርብልሃለን።
15. Priest : We lift up the eyes of our heart to Thee, and bow our stubborn hearts to Thee. Submission be to Thee, glory to Thy kingdom ; and we offer unto Thee pure incense together with Thine archangels.
፲፮፤ ይ.ሕ. ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። ተዘከረነ እግዚኦ ኦ ሊቅነ በውስተ መንግሥትከ። ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ። በከመ ተዘከርኮ ለፈያታዊ ዘየማን እንዘ ሀሎከ ዲበ ዕፀ መስቀል ቅዱስ።
አቤቱ በመንግሥትህ አስበን፤ ሊቅ ሆይ አቤቱ በመንግሥትህ አስበን፤ ቅዱስ በሚሆን በዕፀ መስቀል ላይ ሳለህ ፈያታዊ ዘየማንን እንዳሰብከው አቤቱ በመንግሥትህ አስበን።
16. People : Remember us, Lord, in Thy kingdom .... (Anaphora of the Apostles #34: p.45)
፲፯፤ ይ.ካ. ንሰፍሕ ለከ አእዳወ መዝራዕት ወንጼልል ዲበ ዝንቱ መሥዋዕት።
ክንድ ያላቸው እጆቻችንን ዘርግተን በዚህ መሥዋዕት ላይ እናሳርፋለን።
17. Priest : We stretch out our hands to Thee and overshadow this sacrifice.
፲፰፤ ይ.ካ. ሐመ በፈቃዱ ወተሰቅለ በሥምረቱ ወሞተ በምክረ አቡሁ ወተንሥአ በሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት፤ ከደነ ሰማያተ ሥኑ ወመልዐ ምድረ ስብሐቲሁ።
በፈቃዱ ታመመ፤ በፈቃዱ ተሰቀለ፤ በአባቱ ምክርም ሞተ በሦስተኛውም ቀን ተነሣ በክብር ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ደም ግባቱ ሰማያትን አለበሰ፤ ምስጋናውም በምድር መላ።
18. Priest : He suffered by His will, was pleased to be crucified, died through the counsel of His Father, rose on the third day, ascended in glory into heaven, His beauty covered heaven, and His glory filled the earth.
፲፱፤ ይ.ዲ. አውሥኡ።
ተሰጥዎውን መልሱ።
19. Deacon : Answer ye.
፳፤ ይ.ሕ. ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉዕ ሰማያተ ወምድረ ቅድሳተ ስብሐቲከ።
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ፍጹም አሸናፊ እግዚአብሔር የጌትነትህ ምስጋና በሰማይና በምድር የመላ ነው።
20. People : Holy, holy, holy, perfect Lord of hosts, heaven and earth are full of the holiness of Thy glory.
፳፩፤ ይ.ካ. (በለኆሳስ) ኦ እግዚእየ ሊቅ ሱታፌ ቀዳማዊ ወደኃራዊ አንተ ውእቱ ኅብስተ ሕይወት ዘወረድከ እምሰማያት ፈኑ መንፈሰ ቅዱሰ ወኃይለ ዲበ ዝንቱ ኅብስት ወላዕለ ዝ ጽዋዕ ዘይቄድስ ነፍሰነ ወሥጋነ
(በቀስታ) አቤቱ ጌታዬ ሊቅ ከቀዳማዊና ከደኃራዊ ጋራ አንድ የምትሆን፤ ከሰማይ የወረድህ የሕይወት ኅብስት አንተ ነህ። በዚህ ኅብስት ላይና በዚህ ጽዋ ላይ መንፈስ ቅዱስን ኃይልንም ላክ። ነፍሳችንንና ሥጋችንን መንፈሳችንንም የሚያነጻ፤
21. Priest : (in a low voice) O my Lord, Master, Who has fellowship with the first and the last, Thou art the living bread which came down from heaven. Send the Holy Spirit and power on this bread and on this cup which
፳፩፤ … ወመንፈሰነ ከመ ንኩን ንጹሓነ ቦቱ እምኵሉ ኃጣውኢነ። ወንቅረብ ለነሢአ ምሥጢርከ ቅዱስ እስመ ለከ ይእቲ መንግሥት ወኃይል ወስብሐት ወስግደት ለዓለመ ዓለም።
… በእርሱ ከኃጢአታችን ሁሉ የነጻን እንሆን ዘንድ፤ ቅዱስ ምሥጢርህንም ለመቀበል እንቀርብ ዘንድ። መንግሥት ያንተ ናትና፤ ኃይልና ምስጋና ስግደትም ለዘላለሙ።
21. … sanctify our souls, bodies and spirits, that we may be purified, through Him, from all our sins, and that we may draw near to take Thy holy mystery, for Thine is the kingdom, and the power, and the glory, and worship, unto endless ages.
፳፪፤ (በልዑል ዜማ) ይ.ካ. ኦ አምላክ ዘለዓለም ቀዳማዊ ወደኃራዊ፤ ቀዳማዊ ዘእንበለ ጌሠም ወደኃራዊ ዘእንበለ ትማልም ብሉየ መዋዕል ዘእንበለ ዮም ወጌሠም።
(ከፍ ባለ ቃል) ቀዳማዊና ደኃራዊ የምትሆን የዘላለም አምላክ ሆይ ነገ ሳይኖርበት ቀዳማዊ የሚሆን ትላንት ሳይኖርበት ደኃራዊ የሚሆን ዛሬ ሳይኖርበት በዘመን ያረጀ።
22. Priest : (in a loud chant) O eternal God, Thou art the beginning and the ending, the beginning without a morrow, and the ending without a previous day, full of years without a today.
፳፫፤ የዐቊር ማየ በከርሠ ደመና፤ ወያወርድ ዝናመ እምከርሠ ማኅፀና፤ ያዐርግ ዐቀበ መንገለ ሰማያት ወያወርድ ዝናመ ለሲሳየ ኵሉ ፍጥረት። ይገብር በከመ ሐለየ፤ ወይፌጽም በከመ ወጠነ፤ ወያጠዓጥዕ በከመ ፈቀደ።
ውኃን በደመና ውስጥ ይቋጥራል፤ ዝናምንም ከማኅፀንዋ ውስጥ ያወርዳል፤ ወደ ሰማይ ሽቅብ ያወጣል፤ ለፍጥረት ሁሉ ምግብ ሊሆን ዝናምን ያወርዳል፤ እንደ አሰበ ያደርጋል፤ እንደ ወደደም ይፈጽማል።
23. He binds up the waters in clouds and lets rain go down from their womb; He takes it up into heaven and lets rain descend for the nutrition of all creatures, He does according to His design and fulfills according to His will.
፳፬፤ ፫ቱ ዕደው ሀለዉ ኀቤነ አኃዝያነ ኵሉ ዓለም በአሐቲ ምክር ወበአሐቲ ሥልጣን ወበአሐቲ ፅምረት።
ዓለምን ሁሉ የያዙ ሠለስቱ ዕደው ከእኛ ዘንድ አሉ። በአንዲት ምክር በአንዲት ሥልጣን በአንዲት ተዋሕዶ።
24. There are among Us three persons who hold all the world with one counsel, with one authority and with one unity.
፳፭፤ ኅቡረ ምስለ አቡሁ ሰማያተ ገብረ አልቦ ከማከ መሐሪ ወአልቦ ዘከማከ በሥልጣነ ቃሉ ተዓጋሢ።
ከአባቱ ጋራ በአንድነት ሰማያትን ፈጠረ፤ እንደ አንተ ይቅር ባይ የለም በቃሉ ሥልጣን እንደ አንተ የሚታገሥ የለም።
25. Together with Thy Father Thou made heaven. There is none compassionate like Thee and there is none whose word is with such authority who is patient like Thee.
፳፮፤ ይ.ሕ. በከመ ምሕረትከ አምላክነ፤ ወአኮ በከመ አበሳነ። (፫ተ ጊዜ)
አምላካችን ሆይ እንደ ቸርነትህ ነው፤ እንደ ኃጢአታችን አይደለም። (፫ ጊዜ)
26. People : According to Thy mercy, our God, and not according to our sins. (to be chanted thrice)
፳፯፤ ይ.ካ. ግሩም ውእቱ እምግሩማን፤ ወልዑል ውእቱ እምልዑላን ወጽኑዕ ውእቱ እምአርእስተ አድባር ጽኑዓን።
ከግሩማን ይልቅ ግሩም ነው፤ ከልዑላንም ይልቅ ልዑል ነው፤ ከተራሮች ራሶችም ይልቅ ጽኑ ነው።
27. Priest : He is more terrible than the terrible, higher than the high, and stronger than the peaks of the mountains.
፳፰፤ ክቡር ውእቱ ዘይነብር መልዕልተ አርያም፤ ዕሙቅ ውእቱ ዘይነብር መትሕተ ማዕምቅት፤ ሠረገላሁ በረድ ወራኅበ ዘውሩ በእሳት ሕፁር።
ከአርያም በላይ የሚኖር ክቡር ነው፤ ከጥልቅ በታች የሚኖር ጥልቅ ነው፤ ሠረገላው በረድ ነው፤ የዙሪያው ስፋት በእሳት የታጠረ ነው።
28. Glorious is He Who sits in the highest heaven, profound is He Who sits beneath the depths, His chariot is snow and the bounds of its circle are fenced with fire.
፳፱፤ ወማእከሉ ዘምሉዕ ጢስ፤ አልቦ ዘይበውእ ወአልቦ ዘይወፅእ እንበለ ውእቶሙ ግሩማነ ራእይ እንስሳ እለ ፮ቱ ክነፊሆሙ ወእንተ ኵለንታሆሙ ምሉዓነ አዕይንት።
ማኽሉም ጢስን የተመላ ነው፤ በመልክ ግሩማን፣ ክንፎቻቸው ስድስት ከሚሆኑ በሁለንተናቸው ዓይኖችን ከተመሉ ከሊህ ከአርባዕቱ እንስሳ በቀር የሚገባ የለም፤ የሚወጣም የለም።
29. Its centre is full of smoke. None enters and none goes out except those creatures of terrible appearance and with six wings, whose bodies are full of eyes.
፴፤ ይ.ዲ. አንሥኡ እደዊክሙ ቀሳውስት።
ቀሳውስት እጆቻችሁን አንሡ።
30. Deacon : Priests, raise up your hands.
፴፩፤ ይ.ካ. ነሥአ ኅብስተ በእደዊሁ ዘተቀነወ ወበዘለሐኮ ለአዳም አቡነ ንጹሕ ውእቱ ዘእንበለ ኃጢአት ወጽሩይ ውእቱ ዘእንበለ ተምያን።
አባታችንን አዳምን በፈጠረባቸውና በተቸነከሩ እጆቹ ኅብስቱን ያዘ። ኃጢአት ሳይኖርበት ንጹሕ ነው፤ ዝገት ሳይኖርበት ጽሩይ ነው።
31. Priest : He took bread on His nailed hands which formed our father Adam. He is pure without sin, and absolutely pure without deceit.
፴፪፤ ይ.ሕ. ነአምን ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
እናምናለን ይህ እርሱ እንደ ሆነ በእውነት እናምናለን።
32. People : We believe that this is He, truly we believe.
፴፫፤ ይ.ካ. አእኰተ ባረከ። ወፈተተ። ወወሀቦሙ ለአርዳኢሁ ወይቤሎሙ ንሥኡ ብልዑ ዝኅብስት ሥጋየ ውእቱ መብልዐ ጽድቅ ዘበአማን ዘይትወሀብ ለመድኃኒተ ኵሉ ዓለም። ዘበሊዖሂ የሐዩ እስከ ለዓለመ ዓለም።
አመሰገነ ባረከ ቈረሰ። ይህ ኅብስት ለዓለም ሁሉ ደኅንነትን የሚሰጥ እውነተኛ የጽድቅ መብል ሥጋዬ ነው ንሡ ብሉ ብሎ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው። የበላውም እስከ ዘላለሙ ይድናል።
33. Priest : He gave thanks, blessed and broke. And gave it to His disciples and said to them, Take, eat, this bread is My body, which is indeed the food of righteousness, and which is given for the salvation of all the world. He who will eat it shall live forever.
፴፬፤ ይ.ሕ. አሜን አሜን አሜን ነአምን ወንትአመን ንሴብሐከ ኦ እግዚእነ ወአምላክነ ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
አሜን አሜን አሜን እናምናለን እንታመናለንም። ጌታችንና አምላካችን ሆይ እናመሰግንሃለን። ይህ እርሱ እንደ ሆነ በእውነት እናምናለን።
34. People : Amen. Amen. Amen. We believe and confess, we glorify Thee, O our Lord and our God; that this is He, we truly believe.
፴፭፤ ይ.ካ. ወካዕበ ነጸረ ዲበ ዝንቱ ጽዋዕ ማየ ሕይወት ምስለ ወይን አእኰተ ባረከ። ወቀደሰ ወመጠዎሙ ለእሊአሁ ሐዋርያቲሁ ወይቤሎሙ ንሥኡ ስትዩ ዝጽዋዕ ደምየ ውእቱ ስቴ ሕይወት ዘበአማን።
ዳግመኛም በዚህ ጽዋ ላይ ከወይን ጋራ የሕይወት ውኃን ተመለከተ፤ አመሰገነ ባረከ። አከበረ። ይህ ጽዋ እውነተኛ የሕይወት መጠጥ የሚሆን ደሜ ነውና ንሡ ጠጡ ብሎ ለወገኖቹ ለሐዋርያት ሰጣቸው።
35. Priest : He also looked upon this cup, the water of life with wine, gave thanks, blessed, sanctified, gave it to His apostles and said unto them, Take, drink; this cup is My blood which is the drink of life indeed.
፴፭፤ … ዘሰትየ እምኔሁ ቦ ሕይወት ዘለዓለም ንሥኡ ስትዩ እምኔሁ ኵልክሙ ይኩንክሙ ለሕይወት ወለመድኃኒት።
… ከርሱ የጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው። ለሕይወትና ለመድኃኒት ይሆናችሁ ዘንድ ሁላችሁ ንሡ ጠጡ።
35. ... He who drinks of it will have eternal life. Take, drink of it, all of you, that it may be to you for life and salvation.
፴፬፤ ይ.ሕ. አሜን አሜን አሜን ነአምን ወንትአመን ንሴብሐከ ኦ እግዚእነ ወአምላክነ ከመ ዝንቱ ውእቱ በአማን ነአምን።
አሜን አሜን አሜን እናምናለን እንታመናለንም። ጌታችንና አምላካችን ሆይ እናመሰግንሃለን። ይህ እርሱ እንደ ሆነ በእውነት እናምናለን።
34. People : Amen. Amen. Amen. We believe and confess, we glorify Thee, O our Lord and our God; that this is He, we truly believe.
፴፮፤ ይ.ካ. እለ ተጋባእክሙ ውስተ ዛቲ ቤተ ጸሎት ምጽላየ ኵሎሙ መሃይምናን ወመሃይምናት።
የወንዶችና የሴቶች ሁሉ መጸለያ በምትሆን በዚህች በጸሎት ቤት የተሰበሰባችሁ።
36. Priest : (Take, drink) ye who have gathered in this house of prayer where all the faithful men and women pray.
፴፯፤ ይ.ሕ. ንዜኑ ሞተከ እግዚኦ ወትንሣኤከ ቅድስተ ነአምን ዕርገተከ ወዳግመ ምጽአተከ ንሴብሐከ ወንትአመነከ ንስእለከ ወናስተበቊዐከ ኦ እግዚእነ ወአምላክነ።
አቤቱ ሞትህን ቅድስት ትንሣኤህንም እንናገራለን። ዕርገትህን ዳግመኛም መምጣትህን እናምናለን። እናመሰግንሃለን እናምንሃለንም። ጌታችንና አምላካችን ሆይ እንለምንሃለን እንማልድሃለንም።
37. People : We proclaim Thy death, Lord, and Thy holy resurrection; we believe Thy ascension and Thy second advent. We glorify Thee, and confess Thee, we offer our prayer unto Thee and supplicate Thee, O our Lord and our God.
፴፰፤ ይ.ካ. ቀዳሚሁ ቃል። ውእቱ ቃል ቃለ እግዚአብሔር። ውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ ወኀደረ ላዕሌነ ወሠወሮ እምኔነ።
ቃል ቀዳማዊ ነው። ያ ቃል የእግዚአብሔር ቃል ነው። ያ ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእኛም አደረ ከእኛም ሠወረው።
38. Priest : In the beginning was the Word, and that Word was the Word of God, and that Word was made flesh and dwelt among us, and His flesh hid Him from us.
፴፱፤ ለብሰ ሥጋ ዘይማስን ወረሰዮ ዘኢይማስን ወበይእቲ ሥጋ ተቀሥፈ ዘኢይትቀሠፍ አምላክ።
የሚጠፋ ሥጋን ለበሰ፤ የማይጠፋም አደረገው። በዚህችም ሥጋ የማይገረፍ አምላክ ተገረፈ።
39. He put on mortal flesh and made it immortal, and through this flesh, God who can never be scourged, was scourged.
፵፤ ንዑ ትርአዩ ዘንተ ቅሥፈተ እለ ትሳተፉ ሕማመ ቢጽክሙ ወእለ ትትዌከፉ ሕማመ ፍቁራኒክሙ። ዕፁብ ውእቱ ለዘይሬእዮ በዓይን ወመድምም ውእቱ ለዘይሰምዖ በእዝን። ንዑ ትርአዩ ጽፍዓተ መላትሕ እምገብር ወተኰርዖተ ርእስ በበትር በዐውደ ሊቃነ ካህናት።
በወንደማችሁ መከራ አንድ የምትሆኑ የወዳጆቻችሁንም መከራ የምትቀበሉ፤ ይህን ግርፋት ታዩ ዘንድ ኑ። በዓይን ለሚያየው ዕፁብ ነው በጆሮው ለሚሰማው ድንቅ ነው። ከባርያ የፊቱን መጸፋትና በሊቃነ ካህናቱም ሸንጎ ራስን በዘንግ መመታቱን ታዩ ዘንድ ኑ።
40. Ye who are willing to partake of the suffering of your neighbours and to take upon yourselves the sufferings of your beloved ones, come to see this scourge. It is astonishing to him who looks at it with his eyes, and amazing to him who listens to it with his ears. Come ye to see the smiting on the cheeks by a servant and the beating on the head with sticks in the court of the chief priests.
፵፩፤ ንዑ ትርአዩ አክሊለ ዘሦክ ዘአስተቀጸልዎ ለማሕየዌ ኵሉ ዓለማት
ሁሉን የሚያድን ጌታን ያቀዳጁትን የእሾህ ዘውድ ታዩ ዘንድ ኑ።
41. Come ye to see the crown of thorns with which they crowned the giver of life to all.
፵፪፤ ንዑ ናስተብርክ ለባሕቲቱ ኵልክሙ ሠራዊተ መላእክት እለ ትሠርሩ መልዕልተ አየራት ወእለ ትትፌነዉ ኀበ ፀሓይ ወወርኅ ወከዋክብት ወእለሂ ተዐርጉ ኀበ አብሕርት ወቀላያት።
ለርሱ ብቻ እንሰግድ ዘንድ ኑ። በአየር ላይ የምትወጡ ሁላችሁ የመላእክት ሠራዊት ወደ ፀሓይና ወደ ጨረቃ ወደ ከዋክብትም የምትላኩ፤ ወደ ባሕርና ወደ ቀላያትም የምትወጡ።
42. Come to kneel to Him only all ye the hosts of angels who fly above the air and who are sent towards the sun, the moon and the stars and who ascend towards the seas and lakes.
፵፫፤ ባሕር ርዕደት ወማየ ተከዚ ጐየት ሶበ ርእየት ጽፍዓተ መላትሒሁ ለአምላክ፤ ፀሓይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ወከዋክብት እምዕበየ ብርሃኖሙ ተዐርቁ።
የአምላክን የፊቱን መጸፋት ባየች ጊዜ ባሕር ተንቀጠቀጠች ማየ ተከዚም ሸሸች። ፀሓይ ጨለመ፤ ጨረቃም ደም ሆነ፤ ከዋክብትም ከብዙ ብርሃናቸው ተራቆቱ።
43. The sea trembled and the waters of the stream fled when they saw God beaten on His cheeks; the sun was darkened, the moon became blood and the stars became void of their great light.
፵፬፤ ሞት ፈርሀ ወዲያብሎስ ወድቀ ወሲኦል ሖረት ምስለ እሊኣሃ ኅቡረ ለቀበላ አምላክ ግሩም።
ሞት ፈራ፤ ዲያብሎስም ወደቀ። ሲኦልም ግሩም የሆነ አምላክን ለመቀበል ከወገኖችዋ ጋራ ባንድነት ሄደች።
44. Death was afraid, the Devil fell, and Hades went together with its own to receive the terrible God.
፵፭፤ ንዑ ትርአዩ ዕፁበ ነገረ ዘተገብረ ውስተ ቤተ ጸሎት ጊዜ ይበውእ ሊቀ ካህናት ውስተ ውሳጢተ መንጦላዕት ወይብልዋ ኵሎሙ ኀባኢተ መለኮት ይእቲ ወሠዋሪተ ኵሉ ሕሊናት። ቦአ ኀቤሃ እግዚአ አጋዕዝት ወመናፍስት እንዘ ይጼዐን ዕዋለ አድግ ትሑት።
የካህናት አለቃ ወደ መጋረጃ ውስጥ በገባ ጊዜ በጸሎት ቤት የተደረገውን ድንቅ ነገር ታዩ ዘንድ ኑ። ሁሉም መለኮትን የምትሸሽግ ሕሊናትንም ሁሉ የምትሠውር ናት ይሏታል፤ የአጋዕዝትና የመናፍስት ጌታ በተዋረደ አህያ ግልገል ተቀምጦ ወደርስዋ ገባ።
45. Come ye to see the wonderful thing which was done in the house of prayer when the high priest entered within the veil of which all said that it was the dwelling place of the Deity and the concealing of all thoughts. The Lord of lords and spirits entered therein riding upon the lowly colt of an ass.
፵፮፤ መለኮት አርአየ ለኵሎሙ ሕፃናት እለ ይብሉ ቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ወቡሩክ አንተ እግዚአብሔር አምላከ አማልክት ወንጉሠ እስራኤል።
በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ ቡሩክ ነው፤ አንተም የአማልክት አምላክ የእስራኤልም ንጉሥ እግዚአብሔር ቡሩክ ነህ እያሉ ለሚያመሰግኑ ሕፃናት ሁሉ ጌትነቱን አሳየ።
46. He revealed His divinity to all the infants who said, Blessed is He who cometh in the name of the Lord, and blessed art Thou, Lord, God of gods, and King of Israel.
፵፯፤ ዑደተ ሆሣዕና አርአየ ለእሊአሁ አርዳኢሁ ወይቤሎሙ ቡሩክ በሉ እንዘ ትጸርሑ በዐቢይ ቃል ሆሣዕና በአርያም።
የሆሣዕናን ዑደት ለነርሱ ለደቀ መዛሙርቱ አሳየ፤ ቡሩክ እርሱ በታላቅ ቃል እየጮሃችሁ ሆሣዕና በአርያም በሉ አላቸው።
47. He showed His disciples the manner of going around with the Hosanna; and the Blessed said unto them, Say, crying with a loud voice, Hosanna in the highest.
፵፯፤ … ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም።
… ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም።
ይ.ሕ. ከማሁ እንዘ የዐውዱ።
እየዞሩ እንደዚሁ።
47. … Hosanna in the highest, hosanna in the highest, hosanna in the highest.
The people shall repeat his words while going round.
፵፰፤ ይ.ካ. እምሆሣዕናሁ አርአየ ተኣምረ ወመንክረ ዘኢተገብረ እምቅድመዝ ወዘኢይከውንሂ እምድኅረዝ።
ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ከዚህ አስቀድሞ ያልተደረገ ከዚህም በኋላ የማይደረግ ተኣምራትንና መንክራትን አሳየ።
48. Priest : From His hosanna He showed miracles and wonders which have never been done before and will never happen again.
፵፰፤ … ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም።
… ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም።
ይ.ሕ. ከማሁ።
እንደርሱ።
48. … Hosanna in the highest, hosanna in the highest, hosanna in the highest.
The people shall repeat his words.
፵፱፤ ይ.ካ. እምሆሣዕናሁ አርአየ ጸጋ ወኃይለ ወረደ እምልዑል መንበሩ እንዘ ኢያንቀለቅል እመሠረተ ቤቱ።
ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ከቤቱ መሠረት ሳይናወጥ ከልዑል መንበሩ ወርዶ ጸጋንና ኃይልን አሳየ።
49. Priest : From His hosanna He showed grace and power, came down from His great throne without being moved from the foundation of His house.
፵፱፤ … ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም።
… ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም።
ይ.ሕ. ከማሁ።
እንደርሱ።
49. … Hosanna in the highest, hosanna in the highest, hosanna in the highest.
The people shall repeat his words.
፶፤ ይ.ካ. እምሆሣዕናሁ ወሀበ ፈልፈለ አንብዕ ለኃጥኣን ከመ ያጽድቆሙ ለጊጉያን ያንጽሖሙ ለርሱሓን ወይሚጦሙ ለስሑታን። ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም።
ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ለኃጥኣን የዕንባ ምንጭ ሰጠ። የበደሉትን ያጸድቃቸው ዘንድ፣ ያደፉትን ያነጻቸው ዘንድ፣ የሳቱትን ይመልሳቸው ዘንድ። ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም፤ ሆሣዕና በአርያም።
50. Priest : From His hosanna He granted the sinners a spring of tears so that He may justify the wicked and purify the filthy and bring back those who sinned through ignorance. Hosanna in the highest, hosanna in the highest, hosanna in the highest.
፶፩፤ ይ.ካ. እምሆሣዕናሁ ጸገወ ብርሃነ ለዕዉራን ዳግመ ዘኢይጠፍዕ ብርሃን ዘኢይክል ዓለም ነሢኦቶ።
ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ለዕዉራን ዳግመኛ የማይጠፋ ዓለም ሊቀበለው የማይቻለው ብርሃንን ሰጣቸው።
51. Priest : From His hosanna He granted the blind light which cannot be extinguished again and which the world cannot find.
፶፪፤ እምቅድመ ሕሊና የአምር ወእምቅድመ ሕሊና ይፈትን ወአልቦ ዘይትኀብኦ።
ከሕሊና አስቀድሞ ያውቃል ከአሳብም በፊት ይመረምራል፤ የሚሠወረውም የለም።
52. He knows before one thinks, examines before one thinks, and nothing is hidden from Him.
፶፫፤ ይ.ዲ. በእንተ ብፁዕ ወቡሩክ ወክቡር ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት አባ ….. ወብፁዕ ሊቀ ጳጳስነ አባ ….. ። አባ ቲቶ ወአባ ፊልሞና ወአባ እንድራኒቆስ ወአባ ባስሊቆስ። በእንተ እሉ አግብርቲከ አበዊነ ጳጳሳት ወአበዊነ ኤጲስቆጶሳት ወአበዊነ ካህናት ወአኀዊነ ዲያቆናት ርቱዓነ ሃይማኖት።
ብፁዕ ንዑድ ቡሩክና ክቡር ስለሚሆን ስለ ጳጳሳችን አለቃ ስለ አባ ….. ፤ ብፁዕ ስለሚሆን ስለ አባ ..… ። ስለ አባ ቲቶ፣ ስለ አባ ፊልሞና፣ ስለ አባ እንድራኒቆስ፣ ስለ አባ ባስሊቆስ። ባሮችህ ስለሚሆኑ ስለነዚህ አባቶቻችን ጳጳሳት፣ ስለ አባቶቻችን ኤጲስቆጶሳት፣ ሃይማኖታቸው ስለቀና አባቶቻችን ካህናት፣ ስለ ወንድሞቻችን ዲያቆናት።
53. Deacon : For the sake of the happy and blessed and honourable Patriarch Abba (_____) and the blessed Archbishop Abba (________), Abba Titus, Abba Philemon, Abba Andronicus, Abba Basilicos. For the sake of thy servants our fathers the Orthodox archbishops, our fathers the bishops, our fathers the priests, our brothers the deacons.
፶፬፤ ወለእሉ ሕዝብከ መሐሮሙ ወለኵሎሙ አዕርፍ ነፍሶሙ ወተሣሃሎሙ እወ እግዚኦ አምላክነ ኅድግ ሎሙ አበሳሆሙ ወኢትነጽር ምግባረ ኃጢአቶሙ። እለ ይቀርቡሂ ለነሢአ ሥጋከ ቅዱስ ወለእለሂ ኢይቀርቡሂ ይቅረቡ አዝዞሙ በትእዛዘ ቃልከሰ ኵሉ ይነጽሕ።
እሊህንም ወገኖችህን ማራቸው። የሁሉንም ነፍስ አሳርፍ ይቅርም በላቸው። አቤቱ አምላካችን በደላቸውን በእውነት ይቅር በላቸው። የኃጢአታቸውንም ሥራ አትመልከት። ቅዱስ ሥጋህን ለመቀበል የቀረቡትን ያልቀረቡትንም ይቀርቡ ዘንድ እዘዛቸው። በቃልህ ትእዛዝስ ሁሉ ይነጻል።
54. Have compassion upon these Thy people, rest the souls of them all, and have mercy upon them. Yea, Lord our God, forgive them their sins, do not look upon their sinful deeds, those who will draw near to receive Thy holy body. And those who will not draw near, order them to draw near with the commandment of Thy word ; and all of them will be clean.
፶፭፤ ለእሉኒ ወለኵሎሙ አዕርፍ ነፍሶሙ ወተሣሃሎሙ ውስተ ሕፅነ አብርሃም ይስሐቅ ወያዕቆብ ወበእንተ እለ ተድኅሩ ውስተ ዛቲ እምነ ቤተ ክርስቲያን መሐሮሙ ወተሣሃሎሙ ለኵሎሙ ለዓለመ ዓለም።
የእሊህንም የሁሉንም ነፍስ በአብርሃም በይስሐቅና በያዕቆብ አጠገብ አሳርፍ፤ ይቅርም በላቸው። ከዚህች ከእናታችን ከቤተ ክርስቲያን ወደ ኋላ ያሉትን ሁሉንም ማራቸው፤ ይቅርም በላቸው ለዘላለሙ።
55. To these and to all, grant rest to their souls and have mercy upon them in the bosom of Abraham, Isaac and Jacob; and those who have absented themselves from this church, our mother, pity them all and have mercy upon them, unto the ages of ages.
፶፮፤ይ.ካ. ንፍቅ፤ ህየንተ ጸሎተ ቡራኬ። (በጸሎተ ቡራኬ ፈንታ።)
ኦ ሥሉስ ቅዱስ አኃዜ ኵሉ ዓለም ዘገበርከ ዐቢየ ወመንክረ በሥልጣነ ቃልከ።
ልዩ ሦስት አቤቱ ዓለሙን ሁሉ የያዝህ፤ በቃልህ ሥልጣን ደገኛና ድንቅ ሥራን የሠራህ።
56. The assistant priest shall say the following instead of the Prayer of Benediction
O holy Trinity, Who holds the whole world, who has done great and wonderful deeds through the power of Thy word,
፶፯፤ ባርክ ምሥራቀ ወምዕራበ ሰሜነ ወደቡበ መስዐ ወአዜበ። ባርክ ሰማየ ወምድረ ወባሕረ ወአፍላገ ወአንቅዕተ ማያት ወኵሎ ዓይነ ማይ።
ምሥራቁንና ምዕራቡን ሰሜኑንና ደቡቡን፤ መስዑንና አዜቡን ባርክ፤ ሰማይንና ምድርን፤ ባሕሩንና ወንዞቹን የውኃውንም ፈሳሾች የውኃውንም ምንጭ ሁሉ ባርክ።
57. bless the east and the west, the north and the south, the north east and the south east, (the north west and the south west), bless the heaven, the earth, the sea, the rivers, the source of water, and all the springs of water.
፶፰፤ ባርክ ነፋሳተ ሰማይ ወዝናማተ። ባርክ ፀሓየ ወወርኀ ወከዋክብተ ባርክ አድባረ ወአውግረ ዕፀወ ወሰብለ ወፍሬያተ ምድር።
የሰማይን ነፋስ ዝናሙንም ባርክ። ፀሓይንና ጨረቃን ከዋክብትንም ባርክ። ተራራውንና ኮረብታውንም፤ ዕንጨቱንና ሰብሉን፤ የምድርንም ፍሬ ባርክ።
58. Bless the winds of the sky and the rains. Bless the sun, moon and stars. Bless the mountains and hills, the trees, herbs and the fruit of the earth.
፶፱፤ ባርክ እለ ሀለዉ በታሕተ ሰማይ ወእለሂ ሀለዉ በታሕተ ምድር። ክርስቶስ አምላክነ ምላዕ ውስተ ልቦሙ ፈሪሆተ ስምከ ወአስተናብር ሕይወቶሙ እስከ ለዓለም።
ከሰማይ በታች ያሉትን ከምድርም በታች ያሉትን ባርክ። አምላካችን ክርስቶስ ሆይ፤ በልቡናቸው ስምህን መፍራትን ምላ፤ አኗኗራቸውንም እስከ ዘላለሙ አከናውን።
59. Bless those that are under heaven and those that are under earth. O Christ our God, fill their hearts with the fear of Thy name and make their lives to prosper forever.
፷፤ ይ.ዲ. ንፍቅ፤ መሐሮሙ እግዚኦ ወተሣሃሎሙ ለሊቃነ ጳጳሳት ጳጳሳት ኤጲስቆጶሳት ቀሳውስት ወዲያቆናት ወኵሎሙ ሕዝበ ክርስቲያን።
አቤቱ፤ የጳጳሳቱን አለቆች ጳጳሳቱንና ኤጲስቆጶሳቱን ቀሳውስቱንና ዲያቆናቱን የክርስቲያንንም ወገኖች ሁሉ ማራቸው፤ ይቅርም በላቸው።
60. Asst. Deacon : Lord, pity and have mercy upon the patriarchs, archbishops, bishops, priests, deacons and all the Christian people.
፷፩፤ ይ.ካ. ለእሉኒ ወለኵሎሙ አግብርቲከ ወአእማቲከ አዕርፍ ነፍሳተ አበዊሆሙ ወአበዊነ ጳጳሳት ቅዱሳን። አቡነ ጴጥሮስ ወአቡነ ጳውሎስ
የነዚህንም የሁሉንም የወንዶችና የሴቶች ባሮችህን የአባቶቻቸውንና የቅዱሳን አባቶቻችንን የጳጳሳቱን ነፍስ አሳርፍ። አባታችን ጳውሎስና አባታችን ጴጥሮስ፤
61. Priest : To these and to all Thy servants and Thy handmaids grant rest; to the souls of their fathers also and our fathers the holy bishops ; our father Paul, and our father Peter,
፷፩፤ ይ.ካ. … ወአቡነ አባ ያዕቆብ ጳጳስ ወአቡነ ክቡር ጳጳስነ አባ ማቴዎስ። ዮሐንስ ወስምዖን ወያዕቆብ ወልደ እልፍዮስ ወያዕቆብ ሐዋርያ እኁሁ ለእግዚእነ ኤጲስቆጶስ ዘኢየሩሳሌም።
… አባታችን ጳጳሱ አባ ያዕቆብም ክቡር አባታችን ጳጳሱ አባ ማቴዎስም። ዮሐንስና ስምዖን የእልፍዮስ ልጅ ያዕቆብም የኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ የጌታችን ወንድም የሚሆን ሐዋርያው ያዕቆብም።
61. Priest : … our father Abba James the Bishop, and our father the honourable bishop Abba Matthew. John, Simon and James the son of Alphaeus and James the Apostle, brother of our Lord and Bishop of Jerusalem.
፷፪፤ በእንተ እሉ አግብርቲከ ማርቆስ ወሉቃስ ቲቶ ፊልሞና ወቀሌምንጦስ ባስልዮስ ወአትናሲስ ወኤጲፋንዮስ ወኤጲስቆጶስ ወአባ ሕርያቆስ ወአቡነ ክቡር ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ
ባሮችህ ስለሚሆኑ ስለ ማርቆስና ሉቃስ ቲቶ ፊልሞና ስለ ቀሌምንጦስም ባስልዮስና አትናሲስ ኤጲፋንዮስና ኤጲስቆጶሱ አባ ሕርያቆስ፤ ክቡር የሚሆን ሊቀ ጳጳሱ አባ ዮሐንስ።
62. For the sake of thy servants Mark, Luke, Titus, Philemon, Clement, Basil, Athanasius, Epiphanius, and Abba Heryacos the bishop, and our honourable father the Patriarch Abba Yohannes,
፷፪፤ … ወአቡነ ጳጳስነ አባ ሲኖዳ። ከመ ታሠኒ ሎሙ ሕይወቶሙ ወታፄኑ ወትረ መዓዛ ዕጣኖሙ ወትምሐረነ ኪያነሂ በጸሎተ ዚአሆሙ ለዓለመ ዓለም።
… አባታችን ጳጳሱ አባ ሲኖዳም። አኗኗራቸውን ታቀና ዘንድ ዘወትርም የዕጣናቸውን መዓዛ ታሻትት ዘንድ እኛንም በነርሱ ጸሎት ትምረን ዘንድ ለዘላለሙ።
62. … and our father archbishop Abba Shenouda, beautify their lives and make the savour of their incense unfailing and pity us through their prayers, unto the ages of ages.
፷፫፤ መቅድመ አዕርፍ ነፍሳተ አበዊነ ጳጳሳት ወአበዊነ ኤጲስቆጶሳት እለ አዕረፉ ውስተ ዛቲ ቤተ ክርስቲያን ቀሳውስት ወዲያቆናት አናጕንስጢስ ወመዘምራን
አስቀድሞ በዚህች ቤተ ክርስቲያን ያረፉትን የአባቶቻችንን የጳጳሳቱንና ያባቶቻችንን የኤጲስቆጶሳቱን ነፍሳት የቀሳውስቱንና የዲያቆናቱን የአናጕንስጢስና የመዘምራኑንም፤
63. First rest the souls of our fathers the archbishops and our fathers the bishops who gained their rest in this church, the priests, deacons, anagnosts and singers
፷፫፤ … ወአፃውያነ ኅዋኅው ኅቡረ። እስመ አንተ እግዚኦ ማዕምረ ኅቡኣት አንሥኦሙ በትንሣኤከ ቅድስት።
… በር የሚዘጉትንም ነፍሳት በአንድነት አሳርፍ። አቤቱ አንተ የተሠወረውን የምታውቅ ነህና በቅድስት ትንሣኤህ አስነሣቸው።
63. … together with the door keepers, because Thou, Lord, knows that which is hidden raise them in Thy holy resurrection.
፷፬፤ ወለነሂ እለ ተጋባእነ ለነሢአ ሥጋከ ቅዱስ ወለሰትየ ደምከ ክቡር አቁመነ በየማንከ ምስለ እለ ገብሩ ፈቃደከ።
ቅዱስ ሥጋህን ለመቀበልና ክቡር ደምህን ለመጠጣት የተሰበሰብን እኛንም ፈቃድህን ከሠሩ ሰዎች ጋራ በቀኝህ አቁመን።
64. And cause us, who have gathered to take Thy holy body and drink Thy precious blood, to stand at Thy right hand with those who have fulfilled Thy will.
፷፭፤ አልሕቅ ሕፃናቲነ ወወራዙቲነ ወአንኅ መዋዕሊሆሙ እስከ ርስዓን፤ ወኢታንዲ ብዑላኒነ ወአብዕል ነዳያኒነ። ፈውስ ድዉያኒነ ወኢታድዊ ሕያዋኒነ፤ ተሣሃል ዘሞተ ወመሐር ዘሐይወ።
ሕፃናቶቻችንንና ጐልማሶቻችንን አሳድግ፤ ዕድሜያቸውንም አርዝም። እስከ እርጅና ባለጸጎቻችንንም ድሆች አታድርግ። ድሆችንም ባለጸጎች አድርግ። ድውያኑን አድን። ሕያዋኑንም ጠብቅልን፤ የሞተውን ይቅር በል፤ በሕይወት ያለውንም ማር።
65. Cause our children and our young men to grow and lengthen their days till old age, do not suffer our rich ones to be poor, enrich our poor, heal our sick, do not suffer our whole ones to be sick, have mercy upon the dead, and pity the living.
፷፮፤ ይ.ሕ. እግዚኦ መሐረነ እግዚኦ መሐከነ እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ማረን፤ አቤቱ ራራልን፤ አቤቱ ይቅር በለን።
66. People : Lord pity us, Lord spare us, Lord have mercy upon us.
፷፯፤ ይ.ካ. ባርክ ርእስየ። ወቀድስ ነፍስየ። ወአንጽሕ ሥጋየ። ለነሢአ ሥጋከ ማሕየዊ ወለሰትየ ደምከ ደመ ምሥጢር መለኮታዊ።
ራሴን ባርክ። ነፍሴንም አክብር። ሥጋዬንም አንጻ። ማሕየዊ ሥጋህን ለመቀበል የመለኮታዊ ምሥጢር ደም የሆነ ደምህንም ለመጠጣት።
67. Priest : Bless me and hallow my soul, and purify my body so that I may receive Thy lifegiving body and drink Thy blood, the mysterious divine blood.
፷፰፤ ይ.ዲ. በኵሉ ልብ ናስተብቍዖ ለእግዚአብሔር አምላክነ ኅበረተ መንፈስ ቅዱስ ሠናየ ከመ ይጸግወነ።
በፍጹም ልብ አምላካችንን እግዚአብሔርን እንማልደው። ያማረ የመንፈስ ቅዱስን አንድነት ይሰጠን ዘንድ።
68. Deacon : With all the heart let us beseech the Lord our God that He grant unto us the good communion of the Holy Spirit.
2
፷፱፤ ይ.ሕ. በከመ ሀሎ ህልወ ወይሄሉ ለትውልደ ትውልድ ለዓለመ ዓለም።
በፊት እንደ ነበረ ለዘላለሙ ለልጅ ልጅ ይኖራል።
69. People : As it was, is, and shall be unto generations of generations, unto unending ages.
2
፸፤ ይ.ካ. ደሚረከ ተሀቦሙ ለእለ ይነሥኡ እምኔሁ ይኩኖሙ ለሕይወት ወለመድኃኒት ዘለዓለም።
ከእርሱ ለሚቀበሉ ሰዎች አንድ አድርገህ ስጣቸው። የዘላለም ሕይወት መድኃኒት ይሆናቸው ዘንድ።
ይ.ሕ. አሜን።
70. Priest : Grant it together unto them that take of it that it may be unto them for life and salvation forever.
People : Amen.
2
፸፩፤ ይ.ካ. ሀበነ ንኅበር በዘዚአከ መንፈስ ቅዱስ ወፈውሰነ በዝንቱ ጵርስፎራ ከመ ብከ ንሕየው ዘለኵሉ ዓለም ወለዓለመ ዓለም።
የአንተ በሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አንድ እንሆን ዘንድ ስጠን። በዚህም ጵርስፎራ (በሥጋው በደሙ) አድነን። ለዓለሙ ሁሉ በምትሆን በአንተ ለዘላለሙ ሕያዋን እንሆን ዘንድ።
ይ.ሕ. … እንደርሱ።
71. Priest : Grant us to be united through Thy Holy Spirit and heal us by this oblation that we may live in Thee for ever.
The people shall repeat his words.
፸፪፤ ይ.ካ. ቡሩክ ስሙ ለእግዚአብሔር ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር ወይትባረክ ስመ ስብሐቲሁ ለይኩን ለይኩን ቡሩከ ለይኩን።
የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው። በእግዚአብሔር ስም የሚመጣውም ምስጉን ነው። የጌትነቱ ስም ይመስገን፤ ይሁን ይሁን የተመሰገነ ይሁን።
ይ.ሕ. ... እንደርሱ።
72. Priest : Blessed be the Name of the Lord, and blessed be He that comes in the name of the Lord, and let the name of His glory be blessed. So be it. So be it. So be it blessed.
The people shall repeat his words.
፸፫፤ ይ.ካ. ፈኑ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ላዕሌነ።
የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላክልን።
ይ.ሕ. ... እንደርሱ።
119. Priest : Send the grace of the Holy Spirit upon us.
The people shall repeat his words.
፸፬፤ ይ.ዲ. ተንሥኡ ለጸሎት። ... ለጸሎት ተነሡ።
74. Deacon : Arise for prayer.
ይ.ሕ. እግዚኦ ተሣሃለነ። ... አቤቱ ይቅር በለን።
People : Lord have mercy upon us.
ይ.ካ. ሰላም ለኵልክሙ። ... ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Priest : Peace be unto all of you.
ይ.ሕ. ምስለ መንፈስከ። ... ከመንፈስህ ጋራ።
People : And with your spirit.
፸፭፤ ይ.ካ. ጸሎተ ፈትቶ (የመፈተት ጸሎት።)
እግዚአብሔር ዘተናገረ ምስለ አቡነ አብርሃም በላዕለ ዕፀ ምንባር እንዘ ይብል ኦ አብርሃም ኦ አብርሃም ኦ አብርሃም አነ ውእቱ አምላክከ ወአምላከ አበዊከ ወኢኮንኩ ባዕደ አምላከ።
ከአባታችን አብርሃም ጋራ በተቀመጠበት ዕንጨት ላይ እንዲህ ብሎ የተነጋገረ እግዚአብሔር። አብርሃም ሆይ አብርሃም ሆይ አብርሃም ሆይ አምላክህና የአባቶችህ አምላክ እኔ ነኝ፤ ልዩ አምላክ አይደለሁም ብሎ።
75. Priest : Prayer of Fraction.
O Lord, Who spoke with our father Abraham, while he has sitting under the tree, saying, O Abraham, O Abraham, O Abraham, I am your God and your fathers’ God, I am not a strange God.
፸፮፤ ወኩን ዐቃቤ ለትእዛዝየ ወለቃለ ዚአየ ዘነገርኩከ ወአነ እሁቦሙ ምድረ ለደቂቅከ ወአበዝኆሙ ለዘርዕከ ከመ ኮከበ ሰማይ ወከመ ኆፃ ዘድንጋገ ባሕር።
ትእዛዜን፤ የነገርሁህንም ቃሌን የምትጠብቅ ሁን፤ እኔም ለልጆችህ ምድርን እሰጣቸዋለሁ ዘርህንም እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛቸዋለሁ።
76. Keep My commandment and My word which I have spoken to you and I will grant the earth to your children and multiply your seed like the stars of heaven and the sand of the sea.
፸፯፤ ተንሥእ ኦ አብርሃም ወንሣእ መሶበ ኅብስት ወጻሕበ ወይን ወግበር ሐፂነ ወ፪ተ እምደቂቅከ ምስሌከ ወዕርግ ዲበ ደብረ ታቦር፤
አብርሃም ሆይ ተነሥ፤ ኅብስት ያለበትን መሶብና ወይን ያለበትን ፊቀን መቊረጭትም (መቀስ) አብጅ። ከብላቴኖችህም ሁለቱን ከአንተ ጋራ ይዘህ ወደ ተራራ ውጣ።
77. Stand up, O Abraham, and take a platter of bread and a vial of wine, make a pair of scissors, take with thee two of your household and mount the mountain
፸፯፤ … ወጸውዖ ለካህን ዘስሙ መልከ ጼዴቅ ወጸውዖ ፫ተ ጊዜ እንዘ ትብል ኦ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ኦ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ኦ ብእሴ እግዚአብሔር። ወሶቤሃ ይወጽእ ብእሲ ዘመፍርህ ጥቀ ወሶበ ርኢኮ ኢትፍራህ።
… ስሙ መልከ ጼዴቅ የሚባለውን ካህን የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ብለህ ሦስት ጊዜ ጥራው። ያን ጊዜ ፈጽሞ የሚያስፈራ ሰው ይወጣል፤ ባየኸውም ጊዜ አትፍራ።
77. … and call the priest who is called Melchisedec, call him three times saying, O man of God, O man of God, O man of God. At that time there will come a fearful man; when you see him do not be afraid.
፸፰፤ ወተንሥአ አብርሃም በከመ ነበቦ እግዚአብሔር ወነሥአ ምስሌሁ መሶበ ኅብስት ወጻሕበ ወይን ወክልኤተ እምደቂቁ። ወገብረ ሐፂነ ወዐርገ ዲበ ደብረ ታቦር
አብርሃምም ተነሣ፤ እግዚአብሔር እንደ ነገረው ኅብስት ያለበትን መሶቡንና ወይን ያለበትን ፊቀኑን ከብላቴኖቹም ሁለቱን ይዞ መቊረጭቱንም አበጀ፤ ወደ ተራራም ወጣ፤
78. Abraham stood up as God told him and took with him a platter of bread, a vial of wine and two of his household. He made a pair of scissors, mounted the mountain
፸፰፤ … ወጸርሐ እንዘ ይብል ኦ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ኦ ብእሴ እግዚአብሔር፥ ኦ ብእሴ እግዚአብሔር ፃእ። ወእምዝ ወፅአ ብእሲ ዘመፍርህ በሕቁ ወሶበ ርእዮ አብርሃም ወድቀ በገጹ ወኮነ ከመ ምውት።
…የእግዚአብሔር ሰው ሆይ፥ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ውጣ ብሎም ጮኸ። ከዚህ በኋላ ፈጽሞ የሚያስፈራ ሰው ወጣ። አብርሃምም ባየው ጊዜ በግንባሩ ወደቀ እንደ ሞተም ሆነ።
78. … and cried out saying, O man of God, O man of God, O man of God, come out. Then a very fearful man came out, and when Abraham saw him he fell on his face and became like a dead man.
፸፱፤ ወሰፍሐ እዴሁ መልከ ጼዴቅ ወአንሥኦ ወይቤሎ ተንሥእ ኦ አብርሃም ወኢትፍራህ እስመ እግዚአብሔር ዘፈነወከ ኀቤየ ውእቱ ይቤለኒ ይመጽእ ኀቤከ።
መልከ ጼዴቅም እጁን ዘርግቶ አነሣው። አብርሃም ሆይ ተነሥ አትፍራ አለው፤ ወደኔ የላከህ እግዚአብሔር እርሱ ወዳንተ ይመጣል ብሎ ነግሮኛልና።
79. And Melchisedec stretched forth his hands and raised him saying, “Stand up, O Abraham, and do not be afraid, because God Who sent you unto me, told me that you would come unto me.”
፹፤ ወተንሥአ አብርሃም ወተናገሩ ፪ሆሙ ዕበያቲሁ ለእግዚአብሔር አምላክነ።
አብርሃምም ተነሣ ሁለቱም የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ጌትነቱን ተነጋገሩ።
80. And Abraham stood up, and both spoke together about the greatness of the Lord our God.
፹፩፤ ይ.ዲ. ጸልዩ።
ይ.ሕ. አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻዕ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለ ዕለትን ሀበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ
አባታችን ሆይ በሰማይ የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ በደላችንንም ይቅር በለን፤ እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል።
81. Deacon : Pray ye.
People : Our Father Who art in heaven, hallowed be Thy name, Thy kingdom come, Thy will be done on earth as it is in heaven, give us this day our daily bread;
ይ.ሕ. … ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኵሉ እኩይ እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።
… አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ምስጋናም ለዘላለሙ።
… and lead us, lest we hap into temptation, but deliver us, rescuing us from all evil; for Thine is the kingdom, the power and the glory for ever and ever.
፹፪፤ ይ.ካ. ወተንሥአ አብርሃም ወነሥአ መቅረፀ ወቀረፀ አጽፋረ እደዊሁ ወእገሪሁ ወሥእርተ ርእሱ። ወተንሥአ መልከ ጼዴቅ ወነሥአ መሶበ ኅብስት ወጻሕበ ወይን ወአንሥአ አዕይንቲሁ ውስተ ሰማይ አእኰተ ባረከ ወፈተተ ወቀደሰ ወወሀቦሙ በረከተ ለአብርሃም ወለደቂቁ።
አብርሃምም ተነሥቶ መቊረጭቱን ይዞ የእጁንና የእግሩን ጥፍሮች ቈረጠ፤ የራሱንም ጠጕር። መልከ ጼዴቅም ተነሥቶ ኅብስት ያለበት መሶቡንና ወይን ያለበት ፊቀኑን ይዞ ዓይኖቹን ወደ ሰማይ አንሥቶ አመሰገነ። ባረከ ቈረሰም። ለአብርሃምና ለልጆቹ በረከትን ሰጣቸው።
82. Priest : Abraham stood up and took a pair of scissors and cut the nails of his hands and feet and the hair of his head. Melchisedec stood up and took the platter of bread and the vial of wine and raised his eyes towards heaven, gave thanks, blessed and broke and granted blessing to Abraham and his household.
፹፫፤ ኦ እግዚአብሔር አምላክነ ዘተወከፍከ ቊርባነ ዝኩ ጻድቅ ተወከፍ ኀቤከ ዘንተ መሥዋዕተነ ወአንጽሐነ በፍጹም ነፍስ ወሥጋ ወመንፈስ ወሕሊና ከመ በልብ ንጹሕ ወበፍርሃተ ነፍስ ንንብብ ዘእንበለ ጽርዓት ወኢፍርሃት ወከመ ንበል ኦ እግዚአብሔር አብ ቅዱስ አቡነ ዘበሰማያት።
የዚህን ጻድቅ ቊርባን የተቀበልህ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ ይህን መሥዋዕታችንን ወዳንተ ተቀበል። በፍጹም ነፍስና ሥጋ በመንፈስና በሕሊና አንጻን። በንጹሕ ልብና በነፍስ ፍርሃት ያለማቋረጥና ያለመፍራት እንናገር ዘንድ፤ በሰማይ ያለህ ቅዱስ አባታችን እግዚአብሔር ሆይ ብለንም እንጠራ ዘንድ።
83. O Lord our God, Who accepted the offering of this righteous one, accept this our sacrifice and purify us completely: soul, body, spirit and mind, so that, with pure heart and fear of soul, we may speak continually without fear and say, O holy God: Our Father who art in heaven . . .
፹፬፤ ናስተበቊዐከ ኦ አብ ቅዱስ ወኄር ዘያፈቅር ኂሩተ ኢታብአነ ውስተ መንሱት ወኢይቅንየነ ስሕተት አላ አድኅነነ እምኵሉ ምግባረ እኩይ ወእምሕሊናሁ ወጽርዓታቲሁ ወመናግንቲሁ ወሁከታቲሁ።
ቅዱስ አባት ሆይ፤ ቸርነትንም የምትወድ ቸር ሆይ እንማልድሃለን፤ ወደ ጥፋት እንዳታገባን፤ ስሕተትም እንዳይገዛን። ከክፉ ሥራ ሁሉ አድነን እንጂ፥ ከአሳቡ ከቦዘኑ ከተንኰሉ ከሁከቱም።
84. We beseech Thee, O holy kind Father, lover of good, lead us lest we wander into temptation. Let sin not have dominion over us, rather deliver us from every evil deed and from thought of it, even its opposition, its deceit and trouble.
፹፭፤ ወአብጥሎ ለዘያሜክረነ ወስድዶ እምኔነ ወገሥጽ ሁከታቲሁ ዘተከለ ዲቤነ ወብትክ እምኔነ ምክንያተ እንተ ትወስደነ ውስተ ኃጢአት ወባልሐነ በኃይልከ ቅዱስ በኢየሱስ ክርስቶስ እግዚእነ።
የሚፈታተነንን አጥፋው፤ ከእኛም አርቀው። በእኛ ላይ የተከለውን ሁከቱንም ገሥጽ፤ ወደ ኃጢአት የምትወስደንንም ምክንያት ከእኛ ቊረጥ። ጽኑ በሚሆን ኃይልህ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ አድነን።
85. Destroy our tempter, send him away from us, and rebuke the trouble which he planted into us, uproot from us the motives which thrust us into sin, and deliver us with Thy holy power through Jesus Christ our Lord.
፻፳፯፤ ይ.ዲ. ጸልዩ።
ይ. ሕ. አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእ መንግሥትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመ በሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለ ዕለትን ሀበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነ
127. Deacon : Pray ye.
People : Our Father Who art in heaven, hallowed be Thy name, Thy kingdom come, Thy will be done on earth as it is in heaven, give us this day our daily bread;
፻፳፯፤
ይ. ሕ. ... ከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰ ለነ ኢታብአነ እግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነ ወባልሐነ እምኵሉ እኩይ እስመ ዚአከ ይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመ ዓለም።
127... forgive us our debts as we forgive our debtors, and lead us, lest we hap into temptation, but deliver us, rescuing us from all evil; for Thine is the kingdom, the power and the glory for ever and ever.
፹፮፤ ይ.ሕ. ሠራዊተ መላእክቲሁ ለመድኃኔ ዓለም ይቀውሙ ቅድሜሁ ለመድኃኔ ዓለም። ወይኬልልዎ ለመድኃኔ ዓለም ሥጋሁ ወደሙ ለመድኃኔ ዓለም።
የመድኃኔ ዓለም የመላእክት ሠራዊት በመድኃኔ ዓለም ፊት ይቆማሉ።
መድኃኔ ዓለምን ያመሰግኑታል፤ የመድኃኔ ዓለም ሥጋውና ደሙ።
86. People : The angelic hosts of the Saviour of the world, stand before the Saviour of the world, and encircle the Saviour of the world even the body and blood of the Saviour of the world.
ይ.ሕ. … ወንብጻሕ ቅድመ ገጹ ለመድኃኔ ዓለም በአሚነ ዚኣሁ ለክርስቶስ ንገኒ።
ወደ መድኃኔ ዓለም ፊት እንቅረብ። እርሱን በማመን ለክርስቶስ እንገዛለን።
… Let us draw near the face of the Saviour of the world. In the faith which is of Him let us submit ourselves to Christ.
፹፯፤ ይ.ዲ. ንፍቅ፤ አርኅዉ ኆኃተ መኳንንት።
መኳንንት ደጆችን ክፈቱ።
87. Asst. Deacon : Open ye the gates, princes.
፹፰፤ ይ.ዲ. እለ ትቀውሙ አትሕቱ ርእሰክሙ።
የቆማችሁ ሰዎች ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ።
88. Deacon : Ye who are standing, bow your heads.
፹፱፤ ይ.ካ. መልዐ ሀብታተ ጸጋ፤ ወልድከ ዋሕድ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ወአመነ በሕማሙ ማሕየዊ ወዜነወነ ሞቶ ወአመነ በትንሣኤሁ በፍጹም ምሥጢር።
ያንድ ልጅህ የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጸጋው ሀብት መላ። ማሕየዊ በሚሆን ሕማሙ አምነናል፤ ሞቱን ተናገርን፤ በፍጹም ምሥጢር መነሣቱንም አምነናል።
89. Priest : The gift of the grace of Thine only-begotten Son, our Lord, God, and Saviour Jesus Christ has been completed. We have believed in His life-giving sufferings, proclaimed His death, and believed in His resurrection in a perfect mystery.
፺፤ ይ.ዲ. ስግዱ ለእግዚአብሔር በፍርሃት።
በፍርሃት ሁናችሁ ለእግዚአብሔር ስገዱ።
90. Deacon : Worship the Lord with fear.
ይ.ሕ. ቅድሜከ እግዚኦ ንሰግድ ወንሴብሐከ።
አቤቱ በፊትህ እንሰግዳለን እናመሰግንሃለንም።
People : Before Thee, Lord, we worship, and Thee do we glorify.
፺፩፤ ይ.ካ. ጸሎተ ንስሐ። (የንስሐ ጸሎት)
(ቅዳ. ሐዋ ቁ. ፸፪ - ፹፰)
Priest : Prayer of Penitence.
፺፪፤ ይ.ዲ. ነጽር።
ተመልከት።
Deacon : Give heed.
፺፫፤ ይ.ካ. ቅድሳት ለቅዱሳን።
Priest : Holy things for the holy.
ይ.ሕ. ፩ አብ ቅዱስ፤ ፩ ወልድ ቅዱስ፤ ፩ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ።
ቅዱስ አብ አንድ ነው። ቅዱስ ወልድ አንድ ነው። መንፈስ ቅዱስም አንድ ነው።
People : One is the holy Father, one is the holy Son, one is the Holy Spirit.
፺፬፤ ይ.ካ. እግዚአብሔር ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።
Priest : The Lord be with all of you.
ይ.ሕ. ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People : And with your spirit.
በዐቢይ ዜማ ካህናትና ሕዝቡ እየተቀባበሉ ይበሉ
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ (፫ተ ጊዜ)
አቤቱ ክርስቶስ ማረን (፫ ጊዜ)
Lord have compassion upon us
O! Christ!
፺፮፤ ይ.ዲ. እለ ውስተ ንስሓ ሀለውክሙ አትሕቱ ርእሰክሙ።
በንስሓ ውስጥ ያላችሁ ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ።
96. Deacon : Ye that are penitent, bow your heads.
፺፯፤ ወእመዝ ተመይጦ መንገለ ሕዝብ፤
ይ.ካ. እግዚአብሔር አምላክነ ነጽር ዲበ ሕዝብከ እለ ውስተ ንስሓ ሀለው … እስከ ተፍጻሜቱ።
ከዚህ በኋላ ወደ ሕዝቡ ተመልሶ፤
አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ በንስሓ ወዳሉት ወገኖችህ ተመልከት… እስከ መጨረሻው
(ቅዳ. ሐዋ ቁ. ፺፭ - ፻፴፰)
97. Then the priest shall turn to the people and say : Lord our God, look upon Thy people that are penitent . . .
(Anaphora of the Apostles, #95-138: pp. 49 - 53).
ይ.ካ. አምላካችን እዚአብሔር ሆይ በንስሐ ውስጥ ወዳሉት ወገኖች ተመልከት። እንደ ይቅርታህም ብዛት ይቅር በላቸው። እንደ ቸርነትህም ብዛት በደላቸውን አጥፋላቸው፤ ከክፉ ነገርም ሁሉ ጠብቃቸው ሰውራቸውም።
Lord our God, look upon your people that are penitent, and according to Thy great mercy have mercy upon them, and according to the multitude of your compasion blot out their iniquity, cover them and keep them from all evil.
የቀደመ ሥራቸውን ይቅር ብለህ በሰላም ነፍሳቸውን አድን፤ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ አንድ አድርጋቸው። ተቀዳሚ ተከታይ በሌለው ባንድ ልጅህ በጌታችንና በአምላካችን በመድኃኒታችንም በኢየሱስ ክርስቶስ፣
And redeem their souls in peace, forgive their former works. Join them with Your holy church: through the grace and compassion of your only-begotten Son our Lord and our God and our Saviour Jesus Christ,
በይቅርታውና በምሕረቱ ከቅድስት ቤተ ክርስቲያንህ ጨምራቸው። በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ለአንተ ይገባል፤ ከርሱ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ። አሜን።
through Whom to Thee with Him and with the Holy Spirit be glory and dominion, both now and ever and world without end. Amen.
ይ.ዲ.
ተንሥኡ ለጸሎት።
ለጸሎት ተነሡ።
Stand up for prayer..
ይ.ሕ.
እግዚኦ ተሣሃለነ።
አቤቱ ይቅር በለን።
Lord have mercy upon us.
ይ.ካ.
ሰላም ለኵልክሙ።
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን።
Peace be unto you all.
ይ.ሕ.
ምስለ መንፈስክ።
ከመንፈስህ ጋራ።
And with thy spirit.
ይ.ካ. ሥጋ ቅዱስ ዘበአማን ዝ ውእቱ እማሬ ዘእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘይትወሀብ ለሕይወት ወለመድኃኒት
በእውነት ክቡር የሚሆን የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ ይህ እማሬ ነው
This is the true holy body of our Lord and our God and our Saviour Jesus Christ,
ወለሥርየተ ኃጢአት ለእለ ይነሥኡ እምኔሁ በአሚን፤ ይ.ሕ. አሜን።
አምነው ከርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት የኃጢአት ማስተሥረያም ሊሆን የሚሰጥ፤ ይ.ሕ. አሜን።
Which is given for life and salvation and for remission of sin unto them that receive of it in faith.
People: Amen
ደም ክቡር ዘ በአማን ዝ ውእቱ እማሬ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘይትወሀብ
አምነው ከርሱ ለሚቀበሉ ሕይወትና መድኃኒት የኃጢአት ማስተሥረያም ሊሆን የሚሰጥ
This is the true Precious blood of our Lord and our God and our Saviour Jesus Christ
ለሕይወት ወለመድኃኒት ወለሥርየተ ኀጢአት ለእለ ይትሜጠው እምኔሁ በአሚን ይ.ሕ. አሜን።
የጌታችንና የአምላካችን የኢየሱስ ክርስቶስ ክቡር ደም ይህ ነው ይ.ሕ. አሜን።
Which is given for life and for salvation and for remission of sin unto those who drink of it in faith. Amen
እስመ ዝንቱ ውእቱ ሥጋሁ ወደሙ ለአማኑኤል አምላክነ ዘበአማን፤
ይ.ሕ. አሜን።
በእውነት የአምላካችን የአማኑኤል ሥጋውና ደሙ ይህ እማሬ ነው፤
ይ.ሕ. አሜን።
For this is the body and blood of Emmanuel our very God.
Amen
አአምን፣ አአምን፣ አአምን፣ ወእትአመን እስከ ደኃሪት እስትንፋስ ከመ ዝንቱ ውእቱ ሥጋሁ ወደሙ ለእግዚእነ
አምናለሁ፣ አምናለሁ፣ አምናለሁ፣ እስከ መጨረሻይቱም እስትንፋስ እታመናለሁ በሁለት ወገን ድንግል ከምትሆን ከሁላችን
I believe, I believe, I believe and I confess, unto my latest breath, that this is the body and blood of our Lord
ወአምላክነ ወመድኀኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘነሥአ እምእግዝእተ ኵልነ ቅድስት ድንግል በ፪ ማርያም። ወረሰዮ ፩ደ ምስለ
እመቤት፣ ከቅድስት ማርያም የነሳው የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋው ደሙ
and our God and our Saviour Jesus Christ, which He took from the Lady of us all, the holy Mary of two-fold
መለኮቱ ዘእንበለ ቱስሕት ወኢትድምርት ዘእንበለ ፍልጠት ወኢውላጤ ወኮነ ሰማዕት በስምዕ ሠናይ በመዋዕለ ጲላጦስ ጴንጤናዊ
ይህ እንደሆነ ያለመቀላቀልና ያለትድምርት ያለ መለወጥና ያለ መለየት ከመለኮቱ ጋር አንድ ያደረገው፤ በጴንጤናዊው በጲላጦስም
virginity, and made it one with His Godhead without mixture or confusion, without division or alteration; and He verily confessed with a good testimony
ወመጠዎ በእንቲአነ ወበእንተ ሕይወተ ኵልነ፤ አሜን።
ዘመን ባማረ ምስክርነት ምስክር የሆነ፤ ስለ እኛና ስለ ሁላችንም ሕይዎት አሳልፎ የሰጠው፤ አሜን።
in the days of Pontius Pilate and this body He gave up for our sakes and for the life of us all. Amen
አአምን፣ አአምን፣ አአምን ወእትአመን ከመ ኢተፈልጠ መለኮቱ እምትስብእቱ ኢአሐተ ሰዓተ ወኢከመ ቅጽበተ ዓይን
አምናለሁ አምናለሁ አምናለሁ። መለኮቱ ከሰውነቱ አንዲት ሰዓት ስንኳ እንዳልተለየም እታመናለሁ፤
I believe, I believe, I believe and I confess, that His Godhead was not separated from His manhood, not for an hour nor for the twinkling of an eye, but
አላ መጠዎ በእንቲአነ ለሕይወት ወለመድኃኒት ወለሥርየተ ኃጢአት ለእለ ይትሜጠው እምኔሁ በአሚን። አሜን
ለሕይወትና ለመድኃኒት ለኃጢአትም ማስተሥረያ ሊሆን አምነው ለሚቀበሉ ሰዎች ስለኛ አሳልፎ ሰጠው እንጂ። አሜን።
He gave it up for our sakes for life and for salvation and for remisssion of sin unto them that partake of it in faith. Amen
አአምን አአምን አአምን ወእትአመን ከመ ዝንቱ ውእቱ ሥጋሁ ወደሙ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ
አምናለሁ፣ አምናለሁ፣ አምናለሁ። የጌታችንና የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክረስቶስ ሥጋው ደሙ ይህ እንደሆነ እታመናለሁ
I believe, I believe, I believe and I confess, that this is the body and blood of our Lord and our God and our Saviour Jesus Christ,
ዝ ውእቱ ዘሎቱ ይደሉ ክብር ወስብሐት ወስግደት ምስለ አቡሁ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስ ቅዱስ ማሕየዊ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም፤ አሜን።
ክብርና ምስጋና ስግደትም ቸር ከሚሆን ከሰማያዊ አባቱ ጋራ ማሕየዊ ከሚሆን ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ የሚገባው ይህ ነው፤ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።
and that to Him are rightly due honour and glory and adoration with His kind heavenly Father and the Holy Spirit, the life giver, both now and ever and world without end. Amen
ይ.ካ. ቡሩክ እግዚአብሔር አብ አኃዜ ኵሉ ዓለም አምላክነ።
ይ.ሕ. አሜን
ዓለሙን ሁሉ የያዘ እግዚአብሔር አብ ቡሩክ ነው።
ይ.ሕ. አሜን
Blessed be the Lord, Almighty Father, our God.
People: Amen.
ወቡሩክ ወልድ ዋሕድ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ መድኃኒነ።
ይ.ሕ. አሜን
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወልድ ዋሕድም ቡሩክ ነው።
ይ.ሕ. አሜን
Blessed be the only Son, our Lord and Saviour Jesus Christ.
People: Amen.
ወቡሩክ መንፈስ ቅዱስ ጰራቅሊጦስ መጽንዒ ወመንጸሔ ኵልነ።
ይ.ሕ. አሜን
ሁላችንን የሚያነጻ የሚያጸና መንፈስ ቅዱስም ቡሩክ ነው።
ይ.ሕ. አሜን
And Blessed be the Holy Spirit, the Paraclete, the comforter and cleanser of us all. Amen.
ይ.ሕ. አምላኬ እግዚአብሔር ሆይ ደስ የሚያሰኝህ መሥዋዕት የልጅህ ሥጋ እነሆ። በዚህም ኃጠአቴን ሁሉ አቃልልኝ ስለ እኔ አንድ ልጅህ ሞቷልና።
Lord my God, behold the sacrifice of Thy
Son’s body which pleaseth Thee. Through it blot out all my sins because Thy only-begotten Son died for me.
ስለ እኔ በቀራንዮ የፈሰሰ ንጹሕ የሚሆን የመሢህም ደም እነሆ ስለ እኔ ይጮኻል። ይህ የሚናገር ደም የእኔን የባሪያህን ኃጢአት የሚያስተሠርይ ይሁን።
And behold the pure blood of Thy Messiah, which was shed for me upon Calvary, cried aloud in my stead. Grant that this speaking blood may be the forgiver of me thy servant.
ስለ እነርሱም ልመናዬን ተቀበል ወዳጅህ ስለ እኔ ጦርንና ቅንዋትን ተቀብሏልና፤ ደስ ያሰኝህም ዘንድ ታመመ። ከዳንሁም በኋላ ሰይጣን ወደ ልቡናዬ ተመልሶ በፍላፆቹ ወጋኝ፤ አቤቱ ምሕረትህን ስጠኝ ጽኑ ከሳሽ ነውና።
And accept my prayers for its sake, because Thy beloved accepted the spear and the nails for my sake and suffered to please Thee. But after I was saved, Satan returned to my heart and pierced me through with his darts. Grant me, Lord, Thy mercy, because he is a powerful accuser.
ኃጢአትንም ምክንያት (ሥንቅ) አድርጎ ገደለኝ፤ እኔን ከሕይወቴ ማሳትን በቃኝ ከማይል ደፋር አድነኝ። አቤቱ ንጉሤና አምላኬ መድኃኒቴም የምትሆን አንተ የእኔን የባሪያህን የነፍሴንና የሥጋዬን ቊስል አድርቅልኝ።
And by the provision of sin he slew me. Avenge me of the audacious one who is not satisfied with my being led astray from my life. Thou, Lord, my King and my God and my Savior, bind up the wounds of the soul and body of me thy servant.
በኅብረት የሚባል
አቤቱ ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ርኵሰት ከሆነች ከቤቴ ጠፈር በታች ትገባ ዘንድ የሚገባኝ አይደለም እኔ አሳዝኜሃለሁና በፊትህም ክፉ ሥራ ሠርቻለሁና፤ በአርኣያህና በአምሳልህ የፈጠርኸው ሥጋዬንና ነፍሴን ትእዛዝህን በማፍረስ አሳዴፌአለሁና፤ ሥራም ምንም ምንየለኝምና።
O my Lord Jesus Christ, it in no wise beseemeth Thee to come under the roof of my polluted house, for I have provoked Thee to wrath, and have done evil in Thy sight, and through the transgression of Thy Commandment have polluted my soul and my body which Thou didst create after Thy image and Thy likeness, and in me dwelleth no good thing.
ነገር ግን ስለ መፍጠርህና እኔን ለማዳን ሰው ስለ መሆንህ፤ ስለ ክቡር መስቀልህም፤ ማሕየዊት ስለምትሆን ስለ ሞትህ፤ በሦስተኛው ቀን ስለ መነሣትህም ጌታዬ ሆይ ከበደልና ከመርገም ሁሉ ከኃጢአትና ከርኵሰትም ሁሉ ታነጻኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ እማልድሃለሁም።
But for the sake of Thy contrivance and Thy
incarnation for my salvation, for the sake of
Thy precious cross and Thy life-giving death,
for the sake of Thy resurrection on the third
day, I pray Thee and beseech Thee, O my
Lord, that Thou wouldest purge me from all guilt and curse and from all sin and defilement .
የቅድስናህንም ምስጢር በተቀበልሁ ጊዜ ለወቀሳ ለመፈራረጃ አይሁንብኝ፤ ማረኝ ይቅርም በለኝ እንጂ። የዓለም ሕይወት ሆይ በርሱ የኃጢአቴን ሥርየት የነፍሴንም ሕይወት ስጠኝ እንጂ።
And when I have received Thy holy mystery let it not be unto me for judgment nor for
condemnation, but have compassion upon me and have mercy upon me; O life of the world, through it grant me remission of my sin and life for my soul.
በሁለት ወገን ድንግል በምትሆን በወለደችህ በእመቤታችን በቅድስት ማርያም በመጥምቁ በዮሐንስም አማላጅነት፤ ክቡራን በሚሆኑ በመላእክትም በሰማዕታትና ለበጎ ነገር በሚጋደሉ በጻድቃንም ሁሉ ጸሎት፤ እስከ ዘላለሙ ድረስ አሜን።
Through the petition of our Lady, the holy
Mary of twofold virginity Thy mother, and of John the Baptist, and through the prayer of all holy angels and all the martyrs and righteous who have fought for the good, world without end. Amen.
አባታችን ሆይ
አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀድስ መንግሥትህ ትምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን። የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ። በደላችንንም ይቅር በለን፤ እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል። አቤቱ ወደፈተናም አታግባን ከክፉ ሁሉ እድነን እንጂ። መንግሥት ያንተ ናትና፤ ኃይል ክብር ምስጋና ለዘላለሙ አሜን።
እመቤቴ ማርያም ሆይ
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመላኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንልሻለን። በሐሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። የአሸናፊው የእግዚአብሔር እናት ሆይ ሰላምታ ላንቺ ይገባሻል። ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽ። የማኅፀንሽም ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ ልዑል እግዚአብሔር ካንቺ ጋራ ነውና። ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታንና ምሕረትን ለምኝልን፤ ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘላለሙ አሜን።
ይ.ካ.
ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ ማርያም እምነ ናስተበቊዓኪ።
ሰላም ላንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን፤ እናታችን ማርያም ሆይ እንማልድሻለን።
Peace be unto you, while bowing
unto you, our mother Mary, we ask
for your prayers.
ይ.ሕ.
እምአርዌ ነዓዊ ተማሕጸነ ብኪ በእንተ ሐና እምኪ ወኢያቄም አቡኪ ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ።
ከአዳኝ አውሬ ታድኚን ዘንድ ተማጽነንብሻል፤ ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽም ስለ ኢያቄም ብለሽ ድንግል ሆይ አንድነታችንን ዛሬ ባርኪልን
Protect us from evil beasts. For the
sake of thy mother, Hanna, and your
father, Iyakem, O! Virgin bless this day.
ይ.ካ.
ናዛዚትነ እምኀዘን ወኃይለ ውርዙትነ እምርእሳን በማኅፀንኪ ተጸውረ ብሉየ መዋዕል ሕፃን
ይ.ሕ.
ኦ ማርያም ተስፋ ለቅቡጻን በጊዜ ጸሎት ወዕጣን ወበጊዜ ቅዱስ ቊርባን ለናዝዞትነ ንዒ ኀበ ዝ መካን።
ይ.ካ.
ወላዲተ አምላክ ማርያም እንበለ ሰብሳብ ወሩካቤ በይነ ዘአቅረብኩ ለኪ ንስቲተ ቃለ ይባቤ።
ይ.ሕ.
ፈትቲ እሙ በረከተ አፉኪ መዓዛ ከርቤ ለነዳይ ብእሲ ወለዘረከቦ ምንዳቤ ኅብስተከ ፈትት ኢሳይያስ ይቤ።
ይ.ካ.
ይወርድ መንፈስ ቅዱስ በላዕለ ኅብስቱ ወወይኑ ሶበ ይብል ካህን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ፈኑ።
ካህኑ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ላክ ባለ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ በኅብስቱና በወይኑ ላይ ይወርዳል።
As the priest says let the Holy Spirit
descend, on this revered Holy of Holies.
ይ.ሕ.
ማዕከለ ዛቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኑ ይዌልጦሙ በቅጽበት አባላተ ክርስቶስ ይኩኑ በኃይለ ጥበቡ መንክር ወዕፁብ ኪኑ።
አስደናቂ በሚሆን የጥበቡ ኃይልና በአስገራሚ ብልሃቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያኑ መካከል የክርስቶስ አባሎች ይሆኑ ዘንድ በቅጽበት ይለውጣቸዋል።
The Holy Spirit will descend upon the
bread and wine, His special Spirit will
transform them in an instant with His
wisdom towards the Flesh and Blood.
ይ.ካ.
ሰላም ለክሙ ጻድቃን ወሰማዕት እለ አዕረፍክሙ በሃይማኖት።
በሃይማኖት ያረፋችሁ ጻድቃን ሰማዕታት ሰላም ለናንተ ይሁን።
martyrs, who have died for the faith.
ይ.ሕ.
መዋዕያነ ዓለም አንትሙ በብዙኅ ትዕግሥት ሰአሉ ቅድመ ፈጣሪ በኵሉ ሰዓት፤ እንበለ ንስሓ ኪያነ ኢይንሥአ ሞት።
በብዙ ትዕግሥት ዓለምን ድል የነሳችሁ እናንተ፤ ለንስሐ ሳንበቃ ሞት እንዳይወስደን በየሰዓቱ በፈጣሪ ፊት ቆማችሁ ለምኑልን።
Ye who have conquered the world by patience, pray for us day and night standing in front of our Creator, so that death will not take us before we have repented.
ይ.ካ.
ሰላም ለክሙ ጻድቃነ ዛቲ ዕለት ኵልክሙ ዕድ ወአንስት በበአስማቲክሙ።
በዚች ዕለት ጻድቃን ሁላችሁ ሰላም ለናንተ ይሁን ወንዶችም ሴቶችም በየስማችሁ።
Peace be unto you, all those blessed
on this day, men and women
according to your name.
ይ.ሕ.
ቅዱሳነ ሰማይ ወምድር ማኅበረ ሥላሴ አንትሙ፤ ዝክሩነ በጸሎትክሙ በእንተ ማርያም እሙ፤ ተማሕጸነ ለክርስቶስ በሥጋሁ ወደሙ።
በሰማይና በምድር የከበራችሁ የሥላሴ ወገኖች፣ ስለ እናቱ ስለ ማርያም ብላችሁ በጸሎታችሁ አስቡን በክርስቶስ ሥጋና ደም ተማጸንባችሁ።
Ye that are glorified in heaven and on earth, friends of the Holy Trinity; remember us in your prayers for the sake of Mary and for the sake of Christ's flesh and blood, we beseech you.
በመቀባበል
እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ (፫ ጊዜ)
አቤቱ ክርስቶስ ሆይ ማረን።
Lord have compassion upon us,
O! Christ, Lord. (3 times)
በእንተ ማርያም መሐረነ ክርስቶስ (፫)
ክርስቶስ ሆይ ስለ ማርያም ማረን
For the sake of Mary, have compassion
upon us, O! Christ, Lord. (3 times)
ይ.ካ.
ሰአሊ ለነ ማርያም፣ ምሕረተ ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ።
ማርያም ሆይ! የልጅሽን ምሕረት ለምኝልን ይቅርታውን ያደርግልን ዘንድ።
O Mary, pray for our mercy, so that
He may forgive us.
ይ.ዲ.
ጸልዩ በእንቲአነ ወበእንተ ኵሎሙ ክርስቲያን እለ ይቤሉነ ግበሩ ተዝካሮሙ በሰላም ወበፍቅረ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብሑ ወዘምሩ።
ስለ እኛና አስቡን ስላሉን ስለ ክርስቲያኖች ሁሉ ጸልዩ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና ፍቅር አመስግኑ ዘምሩም።
Pray ye for us and for all Christians who bade us to make mention of them. Praise ye and sing in the peace and love of Jesus Christ.
በቁርባን ሰዓት በኅብረት
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሥሉስ ዘኢይትነገር፣ ሀበኒ ከመ እንሣዕ ለሕይወት ዘንተ ሥጋ ወደመ ዘእንበለ ኵነኔ።
የማይነገር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ሦስት
የምትሆን ይህንን ሥጋና ደም ሕይወት
ሊሆንኝ ሳይፈረድብኝ እቀበል ዘንድ ስጠኝ።
Holy! Holy! Holy! Trinity ineffable, grant me to receive this Body and this Blood for life and not for condemnation. ...
ሀበኒ እግበር ፍሬ ዘያሠምረከ ከመ አስተርኢ በስበሐቲከ ወእሕየው ለከ እንዘ እገብር ዘዚአከ ፈቃደ፤
በጌትነትህ እንድገለጽ ደስ የሚያሰኝህን ፍሬ እሠራ ዘንድ ስጠኝ፤ የአንተንም ፈቃድ እየሠራሁ እኖርልህ ዘንድ ስጠኝ፤
Grant me to bring forth fruit that shall be well pleasing unto Thee, to the end that I may appear in Thy glory and live unto Thee
doing Thy will.
በተአምኖ እጼውዐከ አብ ወእጼው መንግሥተከ ይትቀደስ እግዚኦ ስምከ በላዕሌነ፤ እስመ ኃያል አንተ እኵት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም።
በማመን አባት ብዬ እጠራሃለሁ፣ አቤቱ ስምህ በኛ ላይ ይመስገን፤ ምስጉን ክቡር የምትሆን ኃያል አንተ ነህና ለአንተ ክብር ይገባሃል ለዘላለሙ።
In faith, I call upon Thee, Father, and call upon Thy Kingdom; hallowed, Lord, be Thy name upon us, for mighty art Thou, praised and glorious, and to Thee be glory, world without end.
በቊርባን ሰዓት በኅበረት የሚደጋገም
እስመ ኀያል አንተ እኵት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም።
ኃያል አንተ ነህና ለአንተ ክብር ይገባሃል ለዘላለሙ።
… for Mighty art Thou, praised and
glorious, and to Thee be Glory, for ever and ever.
ይህ ቊርባን ክቡር ነው
ይህ ቍርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ (፪)
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ (፪)
ዋ! ምን አፍ ነው የሚቀበለው
ዋ! ምን ጥርስ ነው የሚያላምጠው
ዋ! ምን ሆድ ነው የሚሸከመው
ነበልባል ያለበት የሚያቃጥል ነው
በንጽሕና ሆኖ ላልተቀበለው
የሚያፍገመግም የሚጎዳ ነው
ይህ ቍርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ (፪)
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ (፪)
አምላካችን ሆይ አንተ ይቅር ባይ
እንደ ቸርነትህ በደለን አትይ(፪)
አሜን አሜን ብለን ተቀብለናል
ቀርበን በፍርሃት ሳንከለከል (፪)
ይህ ቍርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ (፪)
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ (፪)
መቃርዮስ በልቶ ሥጋህን በተስፋ
ስድሳ ዓመት ሆኖታል ምራቁን ሳይተፋ(፪)
ቃልህን አክብሮ ለተቀበለው
ሥጋውን ፈውሶ ነፍሱን አዳነው (፪)
ይህ ቍርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ (፪)
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ (፪)
ማክበር ገባናል በንጽሕና ሆነን
ደፍረን አናቅለው እንዳይቃጥለን(፪)
እንደምታዩት ይህ ቊርባን ፈራጅ ነው
እንደሌላው ሳይሆን የተቀደሰ ነው (፪)
ይህ ቍርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ (፪)
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ (፪)
ሱራፌል ኪሩቤል ፀወርተ መንበር
ለመያዝ ያልቻሉት ፈርተውት በክብር (፪)
እኛ ተመገብነው አገኘን ድኅነት
ለነፍስ ለሥጋችን ሆነልን ሕይወት (፪)
ኑ እንቅረብ
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (፪)
ሥጋውን እንብላ (፫) ደሙንም እንጠጣ
የቀራንዮ በግ የአምላክ ሥጋው
ተሠውቶልናል እንመገበው
እድፉን ኃጢአታችን በንስሐ አጽድተን
እንቀበል አምነን በልጅነታችን
መቅረብ ወደ ጌታ በእውነት የሚገባው
በስተርጅና አይደለም በወጣትነት ነው
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (፪)
ሥጋውን እንብላ (፫) ደሙንም እንጠጣ
ጨረቃና ፀሐይ ደም የለበሱልት
ከዋክብተ ሰማይ የተነጠፉለት
ይኸው ተፈተተ እሳተ መለኮት
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (፪)
ሥጋውን እንብላ (፫) ደሙንም እንጠጣ
ቅድስት እናታችን ቤተ ክርስቲያን
ትጋብዘናለች ሥጋና ደሙን
የአማኑኤል ሥጋው ይኸው ተዘጋጀ
ከግብዣው ተጠራን አዋጁ ታወጀ
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (፪)
ሥጋውን እንብላ (፫) ደሙንም እንጠጣ
መጥቁ ተደወለ እንቅረብ በዕልልታ
በኋላ አይረባንም ዋይታና ጫጫታ
ይህችን ዕድል ፈጥነን እንጠቀምባት
ዓለምን አልያዝንም ብዙ ልንቆይባት
ኑ እንቅረብ መጠራት ሳይመጣ (፪)
ሥጋውን እንብላ (፫) ደሙንም እንጠጣ
አሁኑን ቅረቡ ታውጇል አዋጁ
የይለፍ ደብዳቤ ስንቅን አዘጋጁ
ይህ ዓለም ጠፊ ነው በሀብት አትመኩ
ብሏል አምላካችን ተስፋችሁን እንኩ
በቊርባን ሰዓት በኅበረት የሚደጋገም
እስመ ኀያል አንተ እኵት ወስቡሕ ወለከ ስብሐት ለዓለመ ዓለም።
ኃያል አንተ ነህና ለአንተ ክብር ይገባሃል ለዘላለሙ።
… for Mighty art Thou, praised and
glorious, and to Thee be Glory, for ever and ever.
ይ.ዲ.
ነአኵቶ ለእግዚአብሔር ቅድሳቶ ነሢአነ፤ ከመ ለሕይወተ ነፍሰ ይኩነነ ፈውሰ ዘተመጦነ ንስእል ወንትመሐፀን እንዘ ንሴብሖ ለእግዚአብሔር አምላክነ።
ሥጋውን ደሙን ተቀብለን እግዚአብሔርን እናመሰግነዋልን፤ ለነፍሳችን አኗኗር መድኃኒት ይሆን ዘንድ የተቀበልን እኛ አምላካችንን እግዚአብሔርን እያመሰገን እንለምናለን፤ አደራም እንላለን።
We thank God for that we have partaken
of His Holy things; we pray and trust
that that which we have received may be
healing for the life of the soul while we
glorify the Lord our God.
ይ.ካ.
አሌዕለከ ንጉሥየ ወአምላኪየ ወእባርክ ለስምከ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።
ንጉሤና ፈጣሪዬ ሆይ! ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ፤ ቅዱስ ስምህንም ለዘለዓለሙ አመሰገናለሁ።
I will extol Thee, my King and my
God, and I will bless Thy name for
ever and ever.
ይ.ሕ.
Our Father Thou art in heaven,
lead us not, Lord, into temptation.
ይ.ዲ.
ተመጦነ እምሥጋሁ ቅዱስ ወእምደሙ ክቡር ለክርስቶስ።
ከክርስቶስ ከቅዱስ ሥጋውና ከክቡር ደሙ ተቀበልን።
We have received of the Holy Body
and the precious Blood of Christ.
ይ.ካ.
ኵሎ አሚረ እባርከከ ወእሴብሕ ለስምከ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።
ዘወትር አከብርሃለሁ፤ ቅዱስ ስምህን ለዘለዓለሙ አመሰግናለሁ።
Every day will I bless Thee, and I will
praise Thy name for ever and ever.
ይ.ሕ.
Our Father Thou art in heaven,
lead us not, Lord, into temptation.
ዲያቆን
ወናእኵቶ ይደልወነ ከመ ንሳተፍ ምሥጢረ ክብርተ ወቅድስተ
ክብርት ቅድስት የምትሆን ምሥጢርን እንሳተፍ ዘንድ ስለበቃን ልናመሰግነው ይገባናል።
And let us give thanks unto Him that make us meet to communicate in the precious and holy mystery.
ካህን
ስብሐተ እግዚአብሔር ይነግር አፉየ ወኵሉ ዘሥጋ ይባርክ ለስሙ ቅዱስ፤ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም።
አንደበቴ የእግዚአብሔርን ምሥጋና ይናገራል። የሥጋ ፍጥረትም ሁሉ ቅዱስ የሚሆን ስሙን ያመሰግናል፤ ለዘላለሙ።
My mouth shall speak the praise of the Lord, and let all flesh bless His Holy name for ever and ever.
ይ.ሕ.
Our Father Thou art in heaven,
lead us not, Lord, into temptation.
፺፰፤ ወእምድኅረ ተመጠዉ። (ከተቀበሉም በኋላ።)
ይ.ካ. ኀዳፌ ነፍስ።
ወካዕበ ናስተበቊዖ ለዘኵሎ ይእኅዝ እግዚአብሔር አብ ለእግዚእነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
ዳግመኛ ሁሉን የሚይዝ የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አባት እግዚአብሔር አብን እንማልዳለን።
98. After receiving the holy Communion:
Priest : “Pilot of the Soul”
Again we supplicate God the almighty, Father of our Lord and Saviour Jesus Christ.
፺፱፤ እስመ ዘአፍቀርከ ትሕትናሁ ለእጓለ እመሕያው እምዕበዮሙ ለመላእክት። ኦ ዘአፍቀርከ ንዴተ ዚኣሁ ለአዳም እመዛግብቲሆሙ ለነገደ አብርሃም።
ከመላእክት ገናንነት ይልቅ የሰውን ትሕትና የወደድህ። ከነገደ አብርሃም መዛግብት ይልቅ የአዳምን ንዴት የወደድህ አቤቱ።
99. O Thou Who loved the humility of man more than the greatness of angels, O Thou Who loved the poverty of Adam more than the treasuries of the tribe of Abraham.
፻፤ ኦ ዘፈተውከ ሥነ ላህዩ ለዳዊት እመልክዐ ገጹ ለኤልያብ ወልደ ኢያቡሳዊት።
ኦ ዘለከ አፍቅሮተ ሰብእ እንዘ አምላክ አንተ እግዚአብሔር አምላክነ።
ከኢያቡሳዊት ልጅ ከኤልያብ ፊት መልክ ይልቅ የዳዊትን የመልኩን ደም ግባት የወደድህ ሆይ።
አምላክ ስትሆን ሰውን መውደድ ያለህ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ።
100. O Thou Who loved the beauty of David more than the beauty of Eliab the son of the Jebusite: O Thou Who loves man, while Thou art God, Thou art the Lord our God:
፻፩፤ ይ.ዲ. ጸልዩ።
101. Deacon : Pray ye.
፻፪፤ ይ.ካ. ኀድፍ ነፍሰነ ወሥጋነ ኦ ኀዳፊ።
ኦ አምላክ መስተሣህል አቡሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
የምታነጻ ሆይ ሥጋችንና ነፍሳችንን አንጻ። የጌታችን የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት፤ ይቅር ባይ አምላክ ሆይ።
102. Priest : O purifier, purify our souls and bodies, O merciful God, Father of our Lord, God and Saviour Jesus Christ.
፻፫፤ ቶሳሕከ ማየ ምስለ ወይን ነፋሰ ምስለ እሳት ወማየሂ ዘምስለ መሬት ከማሁ ቶስሕ ድካመ ዚአነ ውስተ ጽንዐ መለኮትከ። ወደምር ካዕበ ሕማመ ዚአነ ውስተ ሕማመ መስቀልከ።
ውኃን ከወይን ጋራ ቀላቅለህ ነፋስንም ከእሳት ጋራ፤ ውኃውንም ከመሬት ጋራ ቀላቀልህ። እንዲሁ የእኛን ድካም ከመለኮትህ ጽንዕ ጋራ ጨምር። ዳግመኛም የእኛን መከራ ከመስቀልህ መከራ ጋራ አንድ አድርግ።
103. Thou mixed water with wine, wind with fire, water with earth, likewise unite our weakness with the power of Thy divinity. Unite also our sufferings with the sufferings of Thy cross.
፻፬፤ ኀቤከ ንስእል ኀቤከ ናስተበቊዕ ኀቤከ ንትመሀለል ለዓለመ ዓለም።
ወዳንተ እንለምናለን ወዳንተ እንማልዳለን ወዳንተ እንማለላለን ለዘላለሙ።
104. Unto Thee we offer our prayers, Thee we supplicate and Thee we entreat, unto the ages of ages.
ይ.ሕ. አሜን።
People : Amen.
አባታችን ሆይ የምትኖር በሰማይ (፪)
መንግሥትህ ትምጣልን ክብርህን እንድናይ
ፈቃድህ በሰማይ ሕይወት እንደሆነ
እንዲሁም በምድር ሰላምን ስጠን
ABATACHIN HOY YEMTINOR BESEMAY
MENGISTIH TIMTALIN KIBRIHIN ENDINAY
FEQADIH BESEMAY HIYWOT ENDEHONE
ENDIHUM BEMIDIR SELAMIN SITEN
ስጠን ለዛሬ የዕለት ምግባችንን
በደላችንንም ይቅር እንድትለን
ጌታ ሆይ አታግባን ከክፉ ፈተና
አንተ ካልረዳኸን ኃይል የለንምና
SITEN LEZARE Y’ELET MIGBACHININ
BEDELACHININIM YIQIR ENDITILEN
GETA HOY ATAGIBAN KEKIFU FETENA
ANTE KALREDAHEN HAYL YELENIMINA
ኃይልና ምስጋና መንግሥትም ያንተው ናት
አሜን ለዘላለም ይሁንልን ዕረፍት
HAYLINA MISGANA MENGISTIM YANTEW NAT
AMEN LEZELALEM YIHUNLIN EREFT
እመቤቴ ማርያም ሆይ (፪)
በመልአኩ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንዳለሽ
ሰላም እንላለን እኛም ልጆችሽ
በሐሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋም ድንግል ነሽ
EMEBETIE MARIAM HOY
BEMEL’AKU GEBRIEL SELAMTA
SELAM ENDALESH
SELAM ENLALEN EGNAM LIJOCHISH
BEHASABISH DINGIL NESH
BESIGAM DINGIL NESH
የልዑል እናቱ ደግሞም የአሸናፊ
ማኅበራችንን በምልጃሽ ደግፊ
ከሴቶች ሁሉ አንቺ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ
ቡሩክ ከሚባለው ከማኅፀንሽ ፍሬ
YEL’UL ENATU DEGIMOM YASHENAFI
MAHIBERACHININ B’EMNET DEGFI
KESETOCH HULU ANCHI TELEYTESH
YETEBAREKISH NESH
BURUK KEMIBALEW KEMAHITSENISH FRIE
ጸጋን እንዲያድለን ለምኚልን ዛሬ
ጸጋንና ክብርን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ!
ያወርድ የነበረው ለእስራኤል መና
ቸሩ ፈጣሪያችን ከአንቺ ጋር ነውና
TSEGAN ENDIYADLEN LEMIGNILIN ZARIE
TSEGANINA KIBRIN YETEMELASH HOY
DES YIBELISH!
YAWERD YENEBEREW L’ISRAEL MENA
CHERU FETARIYACHIN KANCHI GAR NEWUNA
ለምኚ ኢየሱስን ይቅር እንዲለን በደላችንን
የኃጢኣት ባርነት ከእኛ እንዲጠፋ
ተማፅነንብሻል እንድትሆኚን ተስፋ
አሜን።
LEMIGNI IYESUSIN YIQIR ENDILEN
BEDELACHININ
YEHATIAT BARINET KEGNA ENDITEFA
TEMATSINENBISHAL ENDITIHOGNIN TESFA
AMEN።
አባታችን ሆይ የምትኖር በሰማይ (፪)
መንግሥትህ ትምጣልን ክብርህን እንድናይ
ፈቃድህ በሰማይ ሕይወት እንደሆነ
እንዲሁም በምድር ሰላምን ስጠነ
ስጠን ለዛሬ የዕለት ምግብችንን
በደላችንንም ይቅር እንድትለን
ጌታ ሆይ አታግባን ከክፉ ፈተና (፪)
አንተ ካልረዳኸን ኃይል የለንምና
ኃይልና ምስጋና መንግሥትም ያንተው ናት
አሜን ለዘላለም ይሁንልን ሕይወት።
እመቤቴ ማርያም ሆይ (፪)
በመላኩ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እንዳለሽ
ሰላም እንላለን እኛም ልጆችሽ (፪)
በሐሳብሽ ድንግል ነሽ (፪)
በሥጋም ድንግል ነሽ
የልዑል እናቱ ደግሞም ያሸናፊ
ማኅበራችንን በእምነት ደግፊ (፪) ።
ከሴቶች ሁሉ አንቺ ተለይተሽ (፪)
የተባረክሽ ነሽ
ቡሩክ ከሚባለው ከማኅፀንሽ ፍሬ
ጸጋን እንዲያድለን ለምኝልን ዛሬ (፪)
ጸጋንና ክብርን የተመላሽ ሆይ (፪)
ደስ ይበልሽ
ያወርድ የነበረው ለእስራኤል መና
ቸሩ ፈጣሪያችን ካንቺ ጋር ነውና (፪)
ለምኝ ኢየሱስን ይቅር እንዲለን (፪)
በደላችንን
የኃጢአት ባርነት ከእኛ እንዲጠፋ
ተማጽነንብሻል እንድትሆኝን ተስፋ (፪)
አሜን።
፻፭፤ ይ.ካ. አንብሮ እድ።
እግዚአብሔር አምላክነ ባርክ አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ ፃመዉ ወመጽኡ ቤተ መቅደስከ ኀበ የኀድር ብዕለ ስብሐቲከ። ባርክ እደ ወአንስተ አዕሩገ ወሕፃናተ።
አምላካችን እግዚአብሔር የጌትነትህ ብዕል ወደሚያድርበት ቤተ መቅደስህ ደክመው የመጡትን ባሮችህን ባርክ። ወንዶቹንና ሴቶቹን ሽማግሌዎቹንና ሕፃናቱን ባርክ።
105. Priest : “The Laying on of the Hand”
Lord our God, bless Thy servants and Thy handmaids who have taken the trouble to come to Thy sanctuary where the greatness of Thy glory dwells. Bless men and women, old and babies.
፻፮፤ ወኪያነሂ ደምር በኃይለ መላእክቲከ ቅዱሳን ወክድነነ በመንጦላዕተ ብርሃንከ፤ ወሠውረነ በዕፀ መስቀልከ፤ ወአግኅሠነ እምኵሉ ምግባረ እኩይ።
እኛንም በቅዱሳን መላእክትህ ኃይል አንድ አድርግ። በብርሃንህ መጋረጃ ጋርደን፤ በዕፀ መስቀልህም ሠውረን፤ ከክፉ ሥራም ሁሉ አርቀን።
106. Unite us with the power of Thy holy angels, cover us with the curtain of Thy light, hide us with the tree of Thy cross and keep us apart from every evil deed.
፻፯፤ ወአኅድረነ ውስተ ማኅበሮሙ ለቅዱሳን እለ ያዐርጉ ጸሎተ በኵሉ ጊዜ ወበኵሉ ሰዓት እለ በላዕነ ሥጋከ ወእለ ሰተይነ ደመከ ይኩነነ ለሥርየተ ኃጢአት ወለሕይወት ዘለዓለም።
በጊዜው ሁሉና በሰዓቱ ሁሉ ጸሎትን ከሚያሳርጉ ቅዱሳን መላእክት ማኅበር ውስጥ አሳድረን፤ የበላነው ሥጋህ የጠጣነውም ደምህ ለኃጢአት ማስተሥረያና ለዘላለም ሕይወት ይሁነን።
106. Make us to dwell in the congregation of the saints who offer up prayer at every time and every hour. And to us who have eaten Thy body and drunk Thy blood, let them be for the remission of sin and for eternal life,
፻፯፤ … በ፩ዱ ወልድከ ዘቦቱ ለከ ምስሌሁ ወምስለ ቅዱስ መንፈስ ስብሐት ወእኂዝ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለመ ዓለም።
… ባንድ ልጅህ በርሱ ያለ ክብር ጽንዕ ላንተ ይገባል። ከርሱ ጋራ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ፤ አሜን።
106. … through Thine only-begotten Son through Whom to Thee, with Him and with the Holy Spirit, be glory and dominion, both now and ever and unto the ages of ages. Amen.
ይ.ዲ.
አድንኑ አርእስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ በእደ ገብሩ ካህን ከመ ይባርክሙ።
በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ራሳችሁን ዝቅ ዝቅ አድርጉ፤ አገልጋዩ በሚሆን በካህኑ እጅ ይባርካችሁ ዘንድ።
Bow your heads in front of the Lord our God, that He may bless you at the hand of His servant the priest.
ይ.ሕ.
አሜን እግዚአብሔር ይባርከነ ወይሣሃለነ
አሜን እግዚአብሔር ይባርከን ይቅርም ይበለን
People:
Amen, may He bless us at the hand of His servant the priest.
ይ.ካ.
ኦ እግዚኦ አድኅን ሕዝበከ ወባርክ ርስተከ ረኣዮሙ ወአልእሎሙ እስከ ለዓለም፤ ወዕቀባ ለቤተ ክረስቲያንከ ቅድስት እንተ
አቤቱ ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ እስከ ዘላለሙ ጠብቃቸው፤ ከፍ ከፍም አድርጋቸው፤
O Lord, save thy people and bless thy inheritance. Feed them, lift them up for ever,
አጥረይካ ወቤዘውካ በደሙ ክቡር ለዋህድ ወልድከ እግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ። ወጸዋእካ ትኩን ማኅደረ ለነገሥት ወለመኳንንት
በአንድ ልጅህ በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በክቡር ደሙ የዋጀሃት፤ ቤዛም የሆንሃት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንህንም ጠብቃት። ለነገሥታትና ለመኳንንት ለንጹሕ ወገንና
and keep thy church which thou didst purchase and ransom with the precious blood of thy only-begotten Son, our Lord and our God and our Saviour Jesus Christ.
ለዘመድ ንጹሕ ወለሕዝብ ቅዱስ እለ መጻእክሙ ወእለ ተጋባእክሙ ወለእለ ጸለይክሙ ውስተ ዛቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እለ በላዕክሙ ሥጋሁ ቅዱሰ
ቅዱስ ለሆነ ሕዝብ ማደሪያ ትሆን ዘንድ የጠራሃት፤ በዚች ቅድሰት ቤተ ክርስቲያን መጥታችሁ ተሰብስባችሁ የጸለያችሁ
and which thou hast called to be the dewelling-place for kings and rulers, for pure kindred and holy people, you who have come and gathered and prayed in this holy church,
ወእለ ሰተይክሙ ደሞ ክቡረ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ይስረይ ለክሙ ኃጢአተክሙ ዘገበርክሙ እመሂ በአእምሮ አው በኢያእምሮ።
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን የበላችሁ፤ ክቡር ደሙን የጠጣችሁ፤ በማወቅ ወይም ባለማወቅ የሠራችሁትን ኃጢአታችሁን ይቅር ይበላችሁ።
and you who have eaten the holy body and drunk the precious blood of our Lord Jesus Christ. May he forgive your sins which you have committed wittingly or unwittingly.
በዘኀለፈ ይምሐርክሙ ወበዘይመጽእ ይዕቀብክሙ በእንተ ሥጋሁ ሥጋ መለኮት ወበእንተ ደሙ ደመ ሕግ ወሥርዓት፤
ሥጋ መለኮት ስለሚባል ሥጋው የሕግና የሥርዓት ደም ስለሚሆን ደሙ የአሸናፊ የእግዚአብሔር ልጅ በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ሕሊናም ኅትምት የምትሆን የማርያም ልጅ፤
May he forgive you your past sins and keep you from future ones, for the sake of his body, the divine body, and for the sake of his blood, the blood of the covenant
ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ጸባዖት ወወልደ ማርያም ንጽሕት በድንግልና ሕሊና ወበድንግልና ሥጋ ኅትምት ለዓለመ ዓለም አሜን።
ኢየሱስ ክርስቶስ ባለፈው ይቅር ይበላችሁ፤ በሚመጣውም ይጠብቃችሁ ለዘላለሙ አሜን።
of Jesus Christ the Son of the Lord of hosts, and the Son of pure Mary, who has sealed the virginity of her conscience and body, world without end. Amen.
ይ.ካ. እግዚአብሔር የሀሉ ምስለ ኵልክሙ።
እግዚአብሔር ከሁላችሁ ጋራ ይሁን።
Priest : The Lord be with you all.
ይ.ሕ. ምስለ መንፈስከ።
ከመንፈስህ ጋራ።
People : And with your spirit.
አሜን እግዚአብሔር ይባርከነ ለአግብርቲሁ በሰላም ሥርየተ ይኩነነ ዘተመጦነ ሥጋከ ወደምከ አብሐነ በመንፈስ ንኪድ ኵሎ ኃይሎ ለጸላዒ።
አሜን እግዚአብሔር እኛን አጋለጋዮቹን በሰላም ይባርከን፤ የተቀበልነውን ሥጋህና ደምህ ለሥርየት ይሁነን፤ የጠላትን ኀይል ሁሉ በመንፈስ እንረግጥ ዘንድ አሠልጥነን።
Amen. May God bless us, his servants, in peace. Remission be unto us who have receiv-ed thy body and thy blood. Enable us by the Spirit to tread upon all the power of the enemy.
በረከተ እዴከ ቅድስት እንተ ምልዕተ ምሕረት፤ ኪያሃ ንሴፎ ኵልነ እምኵሉ ምግባረ እኩይ አግኅሠነ ወውስተ ኵሉ ምግባረ ሠናይ ደምረነ።
ምሕረትን የተመላች ክብርት የምትሆን የእጅህን በረከት ሁላችን ተስፋ እናደርጋለን፤ ከክፉ ሁሉ ሥራ አርቀን፤ በበጎውም ሥራ ሁሉ አንድ አድርገን። ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን የሰጠን ብሩክ ነው።
We all hope for the blessing of thy holy hand which is full of mercy. From all evil works keep us apart, and in all good works unite us.
ጸጋ ነሣእነ ወሕይወተ ረከብነ በኀይለ መስቀሉ ለኢየሱስ ክርስቶስ። ኪያከ እግዚኦ ነአኵት ነሢአነ ጸጋ ዘእመንፈስ ቅዱስ።
ጸጋን ተቀበልን፤ ደኅንነትንም በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ አገኘን። አቤቱ ከመንፈስ ቅዱስ የተገኘ ጸጋን ተቀብለን አንተን እናመሰግናለን።
Blessed be he that hath given us his holy body and his precious blood. We have received grace and we have found life by the power of the cross of Jesus Christ. Unto thee, Lord, do we give thanks, for that we have received grace from the Holy Spirit.
ይ.ዲ.
እትዉ በሰላም
በሰላም ግቡ
Go ye in peace.