ማቴዎስ 19፡1-30
ጥያቄዎቹን ከመስራትዎ በፊት ለጥናት አመቺ ጊዜ መድበው በጸሎት የጥናቱን ክፍል እና ከላይ የቀረበውን ማብራሪያ በጥንቃቄ እንዲያነቡ እንመክራለን፡፡ ጥናቱን የሚያደርጉት በቡድን ከሆነ (Bible study group)፣ በማብራሪያው ውስጥ ያሉትን የውይይት ጥያቄዎች በመጠቀም ጥናቱን ይበልጥ ፍሪያማ ማድረግ ይቻላል፡፡ በጥያቄዎቹ ላይ አስተያየት ወይም ማሻሻያ ቢኖርዎ በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻ ይጻፉልን፡፡ tsegaewnet@gmail.com መልካም የጥናት ጊዜ፡፡
Email address *
1 ኢየሱስ፣ ፍሬ በሌላቸው ሥነ መለኮታዊ ክርክሮች ላይ ጊዜውን ለማሳለፍም ሆነ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ተግባራት ዝርዝር ለመስጠት ፈቃደኛ አልነበረም፡፡ *
1 point
2 ከሕይወታችን ጋር ስለማናዛምዳቸው ሥነ መለኮታዊ እውነቶች መከራከር ምንም ጥቅም የለውም፡፡ *
1 point
3 በኢየሱስ ጊዜ፣ የሃይማኖት መሪዎች ስለጋብቻ የነበራቸው አስተያየት ምን ነበር? (መልስ የሆነውን ሁሉ ይምረጡ) *
1 point
Required
4 ኢየሱስ ያለዝሙት ምክንያት መፋታት እንደማይቻል የሚያስተምረውን ቡድን አሳብ ቢቀበልም፥ በእግዚአብሔር ፍጹማዊ አሳብ ላይ ትኩረት አድርጓል። *
1 point
5 እግዚኣብሔር ጋብቻን የፈጠረው ሁለት ሰዎች በሥጋ፣ በአሳብ፥ በልብና በዓላማ አንድ ይሆኑ ዘንድ ነው። *
1 point
6 ኢየሱስ፣ ፍቅሩን ለልጆች ለማሳየት ጊዜ ልናጣ እንደማይገባ ያሰተማረበት ክፍል የት ይገኛል? *
1 point
7 በክርስትና ሕይወት ከሚያጋጥሙን ዐበይት አደጋዎች አንዱ ከክርስቶስ በላይ ሌላ ነገርን መውደድ ነው። *
1 point
8 ወደ ቤተ ክርስቲያን በመሄድ፥ በመዝሙር በማገልገል፥ በመጸለይና በመስበክ ጥሩ ግብረገባዊ ሕይወት ብንመራም፥ የገንዘብ፥ የሰው ወይም የትምህርት የመሳሰለ ሌላ ፍቅር ከልባችን ውስጥ ተሰውሮ ሊቀመጥ ይችላል። *
1 point
9 በ ማቴ. 19፡16-30 ውስጥ የተጠቀሰውና ኢየሱስን ለመከተል የፈለገ ሀብታም ወጣት ሹም፣ ግብረገባዊ ሕይወት ይመራ የነበረ ሰው ነበር፡፡ *
1 point
10 ኢየሱስን ለመከተል የፈለገውን ሀብታምና ወጣት ሹም ታሪክ በመጠቀም ኢየሱስ ሊያስተምረን የፈለገው ነገር ምንድን ነው? *
1 point
11 አንድ ነገር በጣም አስፈላጊ ቢሆንብንና ኢየሱስ ያንን «ተው» በሚለን ሰዓት ፈቃደኞች ባንሆን፥ ነገሩ ጣዖት ሆኖብናል ማለት ነው። *
1 point
12 አብርሃም፣ ልጁ ይስሃቅን ለመሰዋት በመስማማቱ፣ እግዚአብሔርን ከልጁ በላይ እንደሚወድና ይስሃቅ ጣኦቱ እንዳልሆነ በትግባር አስመስክሯል፡፡ *
1 point
13 ትክክል የሆነውን ሁሉ ይምረጡ፡፡ *
1 point
Required
A copy of your responses will be emailed to the address you provided.
Submit
reCAPTCHA
This content is neither created nor endorsed by Google.