ሉቃስ 17፡1-37
ጥያቄዎቹን ከመስራትዎ በፊት ለጥናት አመቺ ጊዜ መድበው በጸሎት የጥናቱን ክፍል እና ከላይ የቀረበውን ማብራሪያ በጥንቃቄ እንዲያነቡ እንመክራለን፡፡ ጥናቱን የሚያደርጉት በቡድን ከሆነ (Bible study group)፣ በማብራሪያው ውስጥ ያሉትን የውይይት ጥያቄዎች በመጠቀም ጥናቱን ይበልጥ ፍሪያማ ማድረግ ይቻላል፡፡ በጥያቄዎቹ ላይ አስተያየት ወይም ማሻሻያ ቢኖርዎ በሚከተለው የኢ-ሜይል አድራሻ ይጻፉልን፡፡ tsegaewnet@gmail.com መልካም የጥናት ጊዜ፡፡ ወንጌል በድረ-ገጽ አገልግሎት፡፡
Email address *
1 የበደለን ሰው መጸጸቱን ከመግለጽ በቀር የበደለንን ሰው ይቅር ለማለት ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ ሊኖረን አይገባም፡፡ *
1 point
2 የበደሉ መጠንና መደጋገም ይቅርታ ላለማድረግ ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡ *
1 point
3 ዋናው ጉዳይ የኢየሱስ ተከታዮች ተጨማሪ እምነት ማግኘታቸው ሳይሆን፣ እምነታቸውን በሥራ ላይ ማዋላቸው ነው። *
1 point
4 ኢየሱስ ላደረግንለት አገልግሎት እንደሚሸልመን ጥርጥር ባይኖረውም ዋጋ ለማግኘት ስንል መሥራት ኝ አይኖርብንም። *
1 point
5 በሥራ ሲጣደፍ የደከመ ባሪያ ጌታው ከመብላቱ በፊት ምግብ እንደማይቀርብለትና አንድ ጌታም ባሪያው ኃላፊነቱን ስለተወጣ ለማመስገን ኃላፊነት እንደሌለበት ሁሉ፣ እኛም ለክርስቶስ ባደረግንለት ነገር ከመመካት ይልቅ፥ የባሪያን ትሕትና ልንላበስ ይገባል። *
1 point
6 እግዚአብሔርን የምናገለግለው ለእርሱ እና ለሰዎች ካለን ፍቅር በመነሳት እንጂ ምስጋናውን ወይም ጥቅም በመፈለግ መሆን የለበትም። *
1 point
7 ኢየሱስ ክርስቶስ የጀመረው መንፈሳዊ መንግሥት የእግዚአብሔር መንግስት ተብሎ ተጠርቷል፡፡ *
1 point
8 ኢየሱስ እንደ ንጉሥ በሰዎች ሕይወት ወይም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚነግሥበት ጊዜ ሁሉ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት በዚያ ይገኛል። *
1 point
9 ፈሪሳውያን ታላቅና የሚታይ መንግሥት በመጠባበቅ ኢየሱስ ላመጣው ስውር መንፈሳዊ መንግሥት ትኩረት አልሰጡም። *
1 point
10 የኢየሱስ ዳግም ምጽአት፣ በኖኅ ዘመን እንደተከሰተው ጎርፍ ወይም በሎጥ ዘመን በሰዶምና በገሞራ ላይ እንደተከሰተው አደጋ ቅጽበታው ይሆናል። *
1 point
A copy of your responses will be emailed to the address you provided.
Submit
reCAPTCHA
This content is neither created nor endorsed by Google.