የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች እና ህፃናት ኮሚሽነር ለመጠቆም የወጣ
የህዝብ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በአዋጅ ቁጥር 210/1992 አንቀጽ 10(2)፣ 11 እና በአዋጅ ቁጥር
1224/2012 አንቀጽ 8/1/ መሠረት በተጓደሉ ኮሚሽነሮች ምትክ ለመሰየም እጩ አቅራቢ ኮሚቴ መቋቋም እንዳለበት ይደነግጋል፡፡
በዚህም መሰረት የሴቶች እና ህፃናት ኮሚሽነር በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ
ለማሾም ዕጩ አቅራቢ ኮሚቴው፤ ግልጽና ነፃ በሆነ መስፈርት እጩዎችን ለማቅረብ ይችል ዘንድ ይህን
ይፋ የእጩዎች ጥቆማ ጥሪ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያቀርባል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን
ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ.210/1992 /እንደተሸሻለ አዋጅ ቁ.1224/2012/ አንቀፅ 8/2/ መሰረት እጩ ተወዳዳሪዎች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. ዜግነቷ ኢትዮጵያዊ የሆነች፣
2. ለኢፌዲሪ ህገ መንግስት ተገዥ የሆነች፣
3. ለሰብአዊ መብቶች መከበር ተቆርቋሪ
የሆነች
4. በህግ ወይም አግባብ ባለው ሌላ ሙያ የሰለጠነች ወይም በልምድ ሰፊ ዕውቀት ያካበተች
5. ከማንኛውም ፖለቲካ ፓርቲ ገለልተኛ የሆነች፣
6. በታታሪነት ፣በታማኝነቱና በስነምግባሩ መልካም ስም ያተረፈች፣
7. ከደንብ መተላለፍ ውጪ በሌላ የወንጅል ጥፋት ተከሳ ያልተፈረደባት፣
8. የሚሰጠውን ከፍተኛ ሀላፊነት ለመሸከም የሚያስችል ከፍተኛ የአመራር ብቃት ያላት፣
9. ስራውን ለመስራት የሚያስችል ጤንነት ያላት፣
10. ዕድሜ ከ35 ዓመት በላይ የሆነች መሆን ይኖርባታል እነዚህን 1-8 ያሉትን አስገዳጅ
መስፈርቶች የምታሟላ እጩ ሆና መቅረብ ትችላለች፣
ጥቆማ አቅራቢዎች የሚከተሉትን የጥቆማ ማቅረቢያ መንገዶች በመጠቀም ጥቆማቸውን መላክ ይችላሉ፡፡
* በኢሜል አድራሻችን፦
HumanrightNC@hopr.gov.et
* በቴሌግራምና በዋትስ-አፕ ስልክ ቁጥር፡- 09-69-27-43-43
የመልዕክት
ሳጥን ቁጥር 80001
* በአካል ማቅረብ ለሚፈልጉ ፦ አራት ኪሎ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
የእንግዳ መቀበያ ቢሮ በተዘጋጀው ዝግ ሳጥን ውስጥ የጥቆማ ወረቀታቸውን ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጠቋሚዎች የዕጩዎቹን ዝርዝር መግለጫ በተዘጋጀው ቅፅ በመሙላት ጥቆማቸውን ከላይ በተመለከቱት
የጥቆማ መቅረቢያ ዘዴዎች በአንዱ ከሚያዚያ 07/2016 ዓ.ም እስከ
ሚያዚያ 22/2016 ዓ.ም እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ለመልማይ ኮሚቴው ማቅረብ ይችላሉ፡፡
·
ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ
+251111134999 / +251969274343
መደወል ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች
ኮሚሽን የሴቶች እና ህፃናት ኮሚሽነር እጩ መልማይ ኮሚቴ