አዲስ የሰሜን መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጠሪያ ስያሜ ምርጫዎች
በ 19 – 20 የትምህርት ዓመት፣ በኩሌጅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Coolidge HS) ምድረ ግቢ 'New North MS' ወይንም 'Coolidge MS' በመባል ኦፊሴያላዊ ባልሆነ ስያሜ የሚጠቀስ አዲስ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚ ከፍት ሲሆን፣ ይህ ለብራይት ውድ (Brightwood) ፣ ለላሳል ባከስ (LaSalle-Backus)፣ ለታኮማ (Takoma) እና ለዊቲ የር (Whittier) ትምህርት ቤቶች ማኅበረሰቦች ለሚያገለግለ ትምህርት ቤት ኦፊሴሊያዊ የሆነ መጠሪያ ስም ለመሰይም ማኅ በረሰቡ ምርጫዎን እንዲያቀርብ ዲሲፒኤስ እየጠየቀ ነው። የኩሌጅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን (Coolidge HS) በሌላ ስም የመሰየም እቅድ እንደሌለ እባክዎን ልብ ይበሉ። ይህ የመሰየሚያ ቅጽ የራሱ ብቻ የሆነ ርእሠ መምህር እና መምህራን ለሚኖረው ለአዲሱ መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያገለግል ነው። የትምህርት ቤት ስያሜ በሰው ወይንም በቦታ ላይ የተመሠረተ ሊሆን ይችላል። ተጨማሪ መስፈርቶችን በሚከተሉት በዚህ የኦን ላይን ቅጽ ላይ ያገኛሉ።

ዲሲፒኤስ፣ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የተለያዩ በርካታ አስተያየቶችን ማካተት ጨምሮ እንዴት ውሳኔ እንዳደረገ፣ ስለትም ህርት ቤቱ መከፈት የበለጠ ለመረዳት እባክዎን የዲሲፒኤስ ትምህርት ቤት ብሎግን (DCPS school planning blog) ይቃኙ። https://goo.gl/MxvvRZ

የዲሲፒኤስ የትምህርት ቤት እቅድ ቡድን፣ ከዚህ በታች ያለውን ሂደት ከሰኔ (June) 2018 ጀምሮ እና ውሳኔም እንዲደረግ በኅዳር (November) 2018 በማጠናንቀቅ ሂደቱን ለመምራት ያስባል። ከዚህ በታች ያለውን ሙሉውን እባክዎን ይመል ከቱ። ዲሲፒኤስ የስያሚዎች ምርጫዎችን የሚሰበስቡበት ወቅት የመጀመሪያው እርምጃ ነው። ምንም እንኳን ምርጫዎችን የመስጫ የተወሰነ ጊዜ ባይኖርም፣ ከመጀመሪያው የትምህርት ቀን (8/20) እና በወዝ አደሮች ቀን ቀን (9/3) መካከል ባለው ጊዜ ይሆናል ብለን እንጠብቃለን። ይህ ከዚህ በታች እንደተመለከተው ለ 2 - 4 እርምጃዎች በኅዳር (November) ለመወ ሰን በቂ ጊዜ እንዲኖር ለማድረግ ይረዳል።

በዲሲፒኤስ የትምህርት ቤት መጠሪያ አሰያየም ፖሊሲ መሠረት፣ የትምህርት ቤት የእቅድ ቡድን ምርጫዎችን ከማኅበረሰቡ ጋር ለማሰባሰብ በጉጉት እየጠበቀ ነው። : https://goo.gl/DSKnmS.

አዲስ የሰሜን መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን የአሰያየም ሂደት።
Next
Never submit passwords through Google Forms.
This form was created inside of The District of Columbia. Report Abuse - Terms of Service - Additional Terms