ሐሳብዎን ያካፍሉን! Your Opinion Matters to Us!
Dear Friend of the Ethiopian Diaspora Trust Fund (EDTF),
Greetings from the Ethiopian Diaspora Trust Fund Secretariat in Addis Ababa!
On behalf of the people of Ethiopia, we would like to thank you for your generous contribution to EDTF.
We are committed and already at work to utilize 100% of your contribution to financing need based and people-focused social and economic development projects in Ethiopia. Currently, the secretariat is preparing to launch a call for project proposals. As part of this process, we would like to have your input and suggestions on the types of critical projects to fund for maximum outcome. We also want to get your recommendations on how to make EDTF a stronger Ethiopian Diaspora institution.

Please help us by completing this brief online questionnaire.
Your opinion matters to us!
The EDTF Secretariat Team

============================================================================

ለውድ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ (ኢ.ዳ.ት.ፈ.) ደጋፊዎች
አዲስ አበባ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት ሰላምታችን ይድረሳችሁ!
በመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም የ ‘በቀን አንድ ብር ለሀገር ፍቅር’ ጥሪያችንን ሰምተዉ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ለኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ላበረከቱት ድጋፍ ከልብ ልናመሰግንዎ እንወዳለን፡፡
እርስዎ የለገሱት ገንዘብ ሳይሸራረፍ እና ሳይጓደል የወገንዎን ችግር ለሚፈቱ ተቀዳሚ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ፕሮጀክቶች ላይ ለማዋል በስራ ላይ ነን፡፡ በአሁኑ ወቅት ጽ/ቤታችን ፕሮጀክቶችን ለመቀበልና ለመለየት የሚያስችለዉን የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ሂደት ዉስጥም ቀድሞ ቃል እንደገባነው የኢ.ዳ.ት.ፈ. ፕሮጀክቶችን ትኩረት እና ወሰን በተመለከተ የእርስዎን አስተያየት ለማዳመጥ እንፈልጋለን፡፡ በተጨማሪም የኢ.ዳ.ት.ፈ.ን ጠንካራ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ተቋም ለማድረግ የሚያግዙ ምክረ ሀሳቦችን እንዲለግሱን እንጠይቃለን፡፡ ለዚህ እንዲረዳን ያዘጋጀነዉን አጭር መጠይቅ ከታች ሊንኩን በመጫን እንዲመልሱልን በክብሮት እንጠይቃለን፡፡

ይህን አጭር መጠይቅ ለመመለስ ለሚሰጡን ጊዜ ከልብ እናመሰግናለን!
ከአክብሮት ሰላምታ ጋር
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ትረስት ፈንድ ጽ/ቤት

Next
Never submit passwords through Google Forms.
This content is neither created nor endorsed by Google. Report Abuse - Terms of Service